ግራ የገባው ወይስ ለየት ያለ?
-
0:00 - 0:04በአሜሪካ የትኛውም መንገድ ላይ ቆማችሁ ራሳችሁን አስቡት
-
0:04 - 0:07እና ጃፓናዊ ሰውዬ መጥቶ እንዲ ቢላቹ
-
0:07 - 0:09‹ይቅርታ! ይሄ ብሎክ ምን ይባላል›
-
0:09 - 0:13እርሶ ሲመልሱ ‹ይሄ! ኦክ መንገድ ይባላል ያ ደሞ ኤልም መንገድ ይባላል
-
0:13 - 0:15ይሄ 26ኛ ያ ደሞ 27ኛ ነው›
-
0:15 - 0:17እሱም እሺ በማለት ‹እሺ! ያኛው ብሎክስ ምን ይባላል?›
-
0:17 - 0:20እርሶም ‹እንግዲ! ብሎኮች ስም የላቸውም፡፡
-
0:20 - 0:22መንገዶች ናቸው ስም ያላቸው፤
-
0:22 - 0:24ብሎኮች በመንገዶች መሀከል ስም አልባ የሆኑ ቦታዎች ናቸው›
-
0:24 - 0:28እሱም ትንሽ ግራ በመጋባት አዝኖ ይሄዳል
-
0:28 - 0:31አሁን ደሞ በጃፓን የትኛውም መንገድ ላይ ቆመው እንዳሉ ያስቡ
-
0:31 - 0:33ከጎን ወደላው ሰው ይዞራሉ እና ምን ይላሉ
-
0:33 - 0:35ይቅርታ! ይሄ መንገድ ምን ተብሎ ነው ሚጠራው?
-
0:35 - 0:39እነሱም ‹እንግዲ ያ ብሎክ 17፤ ይሄ ደሞ ብሎክ 16›
-
0:39 - 0:42እርሶም ‹እሺ ግን የመንገዱ ስም ምንድን ነው?›
-
0:42 - 0:44እነሱም ምን ብለው ይመልሳሉ ‹መንገዶች ስም የላቸውም
-
0:44 - 0:46ብሎኮች ስም አላቸው
-
0:46 - 0:50ጎግል ካርታ ላይ ይመልከቱ፡፡ ያሉት ብሎኮች 14፣ 15፣ 16፣ 17፣ 18፣ 19
-
0:50 - 0:52እነዚ ብሎኮች በሙላ ስም አላቸው
-
0:52 - 0:56መንገዶች በብሎኮች መሀከል የሚገኙ ስም አልባ የሆኑ ቦታዎች ናቸው›
-
0:56 - 0:59እርሶም ምን ይላሉ ‹እሺ! የቤትዎን አድራሻ እንዴት ያውቃሉ?›
-
0:59 - 1:02እሱም ምን ይመልሳል ‹ቀላል ነው! ይሄ ቀጠና ስምንት፤
-
1:02 - 1:05ያ! ብሎክ 17፤ የቤት ቁጥር አንድ›
-
1:05 - 1:07እርሶም ሲመልሱ ‹እሺ! በሰፈር ውስጥ ስንቀሳቀስ
-
1:07 - 1:09የቤት ቁጥሮቹ በተርታ ይደለም የተቀመጡት›
-
1:09 - 1:12እሱም ሲመልስ ‹በተርታ ይሄዳሉ፡፡ ተገንብተው ባለቁበት ጊዜ ነው የሚሰየሙት፡፡
-
1:12 - 1:15በብሎክ ውስጥ መጀመሪያ የተገነባው ቤት ቁጥር አንድ ነው፡፡
-
1:15 - 1:18ሁለተኛ የተገነባው የቤት ቁጥሩ ሁለት ነው
-
1:18 - 1:20ሶስተኛ የተገነባው ቁጥር ሶስት ነው፡፡ ቀላል እናም ግልፅ ነው፡፡
-
1:20 - 1:23ስለዚ አንዳንዴ ደስ ይለኛል
-
1:23 - 1:25የዓለምን ተቃራኒ ቦታ መሄድ
-
1:25 - 1:27የራሳችን አመለካከት እንዳለን ለማወቅ
-
1:27 - 1:30እናም ከኛ ተቃራኒ አመለካከት እንዳለ ለመረዳት
-
1:30 - 1:32ለምሳሌ በቻይና ሐኪሞች አሉ
-
1:32 - 1:35ስራቸው የናንተን ጤና መጠበቅ እንደሆነ የሚያምኑ
-
1:35 - 1:37እናም ጤነኛ ሆነው ባሳለፉት ወራት ይከፍሏቸዋል
-
1:37 - 1:39ሲታመሙ ደሞ አይከፍሏቸውም ምክንያቱም ስራቸውን በአግባብ ስላልተወጡ
-
1:39 - 1:41ሀብታም የሚሆኑት እርስዎ ጤናኛ ሲሆኑ ነው እንጂ እርስዎ ሲታመሙ አይደለም
-
1:41 - 1:44(ጭብጨባ)
-
1:44 - 1:46በብዙ ሙዚቃ ውስጥ፤ ‹አንድን› እናስባለን
-
1:46 - 1:50የሙዚቃ አጀማመርን ስናይ አንድ ፣ ሁለት ፣ ሶስተ ፣ አራት
-
1:50 - 1:52ግን በምዕራብ አፍሪካ ሙዚቃ፤ ‹አንድ›
-
1:52 - 1:54የመጨረሻ እንደሆነ ነው ሚታሰበው
-
1:54 - 1:56ለልክ ከአረፍተ ነገር መጨረሻ አራት ነጥብ እንደሚገባው
-
1:56 - 1:58በሙዚቃው አሰራር ብቻ ሳይሆን የምትሰሙት፤ ሙዚቃውንም የሚጨርሱበት አካሄድ ነው
-
1:58 - 2:01ሁለት ፣ ሶስት ፣ አራት ፣ አንድ
-
2:01 - 2:04እና ይሄ ካርታ እራሱ ልክ ነው
-
2:04 - 2:06(ሳቅ)
-
2:06 - 2:09የሆነ አባባል አለ ስለህንድ የሚያነሱት ማንኛውም እውነታ
-
2:09 - 2:11ተቃራኒውም እውነት ነው
-
2:11 - 2:13ስለዚ እንዳንረሳ በቴድም ሆነ ሌላ ቦታ
-
2:13 - 2:16ማንኛውም ምርጥ ሀሳብ ቢያነሱም ወይም ቢሰሙም
-
2:16 - 2:18ተቃራኒውም እውነት ሊሆን ይችላል
-
2:18 - 2:20(ጃፓንኛ) በጣም ነው ማመሰግነው!
- Title:
- ግራ የገባው ወይስ ለየት ያለ?
- Speaker:
- ዴሬክ ሲቨርስ ዴሬክ ሲቨርስ
- Description:
-
‹ለሁሉም ነገር ተቃራኒ መልስ አለው› ይባላል እናም በ2 ደቂቃ ውስጥ፤ ዴሬክ ሲቨርስ በማትጠብቁት መንገድ ምን ያህል እውነት እንደሆነ ያሳየናል፡፡
- Video Language:
- English
- Team:
- closed TED
- Project:
- TEDTalks
- Duration:
- 02:21
Dimitra Papageorgiou approved Amharic subtitles for Weird, or just different? | ||
dagim zerihun accepted Amharic subtitles for Weird, or just different? | ||
Ahmed Omer edited Amharic subtitles for Weird, or just different? | ||
Ahmed Omer edited Amharic subtitles for Weird, or just different? | ||
Ahmed Omer edited Amharic subtitles for Weird, or just different? | ||
dagim zerihun declined Amharic subtitles for Weird, or just different? | ||
Dimitra Papageorgiou rejected Amharic subtitles for Weird, or just different? | ||
dagim zerihun accepted Amharic subtitles for Weird, or just different? |