የኢያን እና ላሪሳ ታሪክ
-
0:43 - 0:47ኢያን እና ላሪሳ ጥቂት ጥቅሶችን እንዳነብላቸው ጠየቁኝ
-
0:47 - 0:49ስማቸው ጆን ፓይፐር ከሚባሉት ሰው ትምህርት ላይ
-
0:49 - 0:51እርሳቸውም በጣም የሚታወቁ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ናቸው
-
0:51 - 0:54እናም ስለ ጋብቻ እያስተማሩ ነበረ
-
0:54 - 0:58ይህም የጋብቻ ሚስጢር ስለ ክርስቶስና ቤተክርስቲያን እንዴት እንደሚያመላክት ያስተምሩ ነበር
-
0:58 - 1:00እናም እንዲህ አሉ
-
1:00 - 1:05"ጋብቻ በዋናነት ስለ በምጣኔ ሃብት ስለ መበልጸግ አይደለም"
-
1:05 - 1:10ጋብቻ ኪዳን ጠባቂነት ያለበት ፍቅርን ስለ ማሳየት ነው
-
1:10 - 1:14በክርስቶስ እና በቤተክርስቲያን መካከል
-
1:16 - 1:20ሲናገሩም "ክርስቶስን ማወቅ
-
1:20 - 1:22ኑሮን ከማሳካት የበለጠ ጠቃሚ ነገር ነው
-
1:22 - 1:26ክርስቶስን ኃብት ማድረግ
-
1:26 - 1:28ልጆችን ከመውለድ የበለጠ ጠቃሚ ነገር ነው
-
1:30 - 1:34በየትኛውም መንገድ ቢሆን፣ ነገሩ አጭር ነው
-
1:34 - 1:36ጋብቻ በርካታ ብሩህ ቀናት ሊኖሩት ይችላል
-
1:36 - 1:39ወይም በደመናዎች የተሸፈነ ሊሆን ይችላል
-
1:39 - 1:43ሆኖም ግን ጋብቻችንን ለመስራት ፊታችንን ብናዞር
-
1:43 - 1:46እርሱንም በዋናነት እግዚአብሔር እንደሚፈልገው አድርገን ብንሰራው
-
1:46 - 1:51ምንም አይነት ኃዘንም ሆነ አደጋ የሆነ ነገር በመንገዳችን ላይ ሊቆም አይችልም
-
1:51 - 1:55የትኛቸውም ቢሆኑ ለስኬታችን እንቅፋት አይሆኑም
-
1:55 - 1:57ነገር ግን የስኬት ጎዳና ይሆኑልናል
-
2:10 - 2:14በክርስቶስ እና በቤተክርስቲያን መካከል ያለው
-
2:14 - 2:16ኪዳንን የሚጠብቀው ፍቅር ውበት
-
2:16 - 2:23ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን ራሱ ክርስቶስ ሲደግፈው ብሩህ ሆኖ ያበራል
-
2:29 - 2:33ኢያን እና እኔ መጀመሪያ የተዋወቅነው በ2005 ኮሌጅ ውስጥ ነበር
-
2:33 - 2:37እርስ በእርሳችንም የምንተዋወቅበት የአስር ወራት የሚያስደስት ቆይታ ነበረን
-
2:37 - 2:40አጥልቄ እመለከት ነበርና በጣም ከምወዳቸውን አንደኛውን ፎቶ ግራፍ አገኘሁት
-
2:40 - 2:42ይሄም ፎቶ ከደረሰበት አደጋ ጥቂት ቀደም ብሎ የተነሳው ይመስለኛል
-
2:42 - 2:45በሦስት እግሮች የሚቆመውን ካሜራ አስተካከለ
-
2:45 - 2:47እናም ያ በእርግጥ ድሮም የማውቀው የኢያን ፊት ነበር
-
2:47 - 2:51ያ፣ ለእኔ፣ እርሱ ማን መሆኑን ጠቅለል አድርጎ ያስቀምጥልኛል
-
2:51 - 2:52ለአስር ወራት ያክል በመጠናናት ፍቅር አሳልፈናል
-
2:52 - 2:55እናም እርሱ ተጨማሪ ሥራ በአባቱ ተቀጥሮ ይሠራ ነበር
-
2:55 - 2:58ፒትስበርግ አቅራቢያ ወዳለው ሥራው እየሄደ ነበር
-
2:58 - 3:01ከዚያም አደጋ እንደ ደረሰበት የሚነግረን የስልክ ጥሪ ደረሰን
-
3:01 - 3:03እርሱም ወደ ሥራ ቦታው እንደ ደረሰ ይሁን
-
3:03 - 3:04ወይም በመንገድ ላይ ሳለ የደረሰበት ይሁን አላወቅንም ነበር
-
3:04 - 3:07ስለዚህ ወደ ፒትስበርግ ወረድን
-
3:07 - 3:09እኔም ጉዟችንን ሙሉ በመኪና ውስጥ ሆኜ ስጸልይ ነበርኩ
-
3:09 - 3:10የምጸልየውም አእምሮው ተጎድቶ እንዳይሆን ነበር
-
3:10 - 3:12ለጥቂት ሰዓታት በሆስፒታል ከቆየን በኋላ
-
3:12 - 3:14አንድ ነገር ተረዳን
-
3:14 - 3:17ለጥቂት ሰዓታት የአእምሮ ቀዶ ጥገና እንደ ነበረው ተነገረን
-
3:17 - 3:21ከፍተኛ ህመም ያለው የአእምሮ ጉዳት ደርሶበት ተሰቃየ
-
3:21 - 3:23እግዚአብሔር ፈጽሞ ህይወቱን አዳነው
-
3:23 - 3:26አንድ ሌሊት ከአምስት የአእምሮ ተግባራት ፈተና ውስጥ አራቱን ሳያልፍ ቀረ
-
3:26 - 3:29ከዚያ በሚቀጥለው ማለዳ ደህና ሆኖ ተገኘ
-
3:29 - 3:32አእምሮው እንደገና ምላስ መስጠት እየጀመረ ነበር
-
3:37 - 3:39ከአደጋው በኋላ ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ውስጥ ዘለቅሁ
-
3:39 - 3:41ከዚህ የተነሳ በህክምናው ውስጥ የእውነት እንድሳተፍ ብዬ ነበር
-
3:41 - 3:45ከዚያም ህይወቱን የደስታ ለማድረግ ማድረግ የምችለውን ሁሉ አደረግሁኝ
-
3:45 - 3:47ፍቅረኝነታችንን ለመቀጠል ተያይዘን እንወጣ ነበር፣ ከቀድሞው ጋር ሲተያይ ግን እንግዳ ነገር ነበር
-
3:47 - 3:49ምክንያቱም እርሱ ማውራት አይችልም ነበር
-
3:49 - 3:51እንዲሁም መመገብ አይችልም ነበር
-
3:51 - 3:54ስለዚህ እኛ በፍቅር ህይወት ላይ ያሉ ፍጹም ወፈፌዎች እንመስል ነበር
-
3:54 - 3:57ነገር ግን አስደሳች ስሜት ነበረንና ሁልጊዜም የማወራለት እኔ ነበርኩ
-
4:00 - 4:03ኢያን ላይ ከደረሰው አደጋ በፊት እርሱ በጣም ኮስታራ እንደነበረ አውቅ ነበር
-
4:03 - 4:05ይህም ኮስታራነት ስለ ጋብቻ ሲሆን ቀለበት ልንገዛ ነበር
-
4:05 - 4:07ስለዚህ የት ጋር እንደነበረ አውቅ ነበር
-
4:07 - 4:09ያም ደግሞ
-
4:09 - 4:11ማውራት ወደማይችልበት ደረጃ ከደረሰ በኋላ በእጅጉ ረድቶኛል
-
4:11 - 4:13እንደሚያፈቅረኝ አውቅ ነበር
-
4:13 - 4:16ግንኙነታችን የት እንዲሄድ እንደሚፈልግ አውቅ ነበር
-
4:16 - 4:19ምክኒያቱም በፍቅር እየተጠናናን የምናሳልፈው ሆነ ብለን በዓላማ ነበር
-
4:19 - 4:21ጋብቻችን አንድ ቀን እንዲከናወን ጸልየናል
-
4:21 - 4:23ሁሉም ጓደኞቻችን ሲጋቡ
-
4:23 - 4:25ቤተሰብም ሲኖራቸው አይተናል
-
4:25 - 4:26ያም ደግሞ እኛን ወጥሮ የያዘን ነገር ነበር
-
4:26 - 4:28ነገር ግን ተስፋን አጥብቀን ለመያዝ ሞከርን
-
4:28 - 4:31እርሱም እኛም አንድ ቀን እንደነርሱ እንድንበቃ ነበር
-
4:35 - 4:38ይሄ የእኛ አመስጋኝነት ልክ ነው
-
4:38 - 4:40ስለዚህ እኛ የትኛውንም ብቅ የሚል ሰው ሁሉ
-
4:40 - 4:42የሚያመሰግኑበትን አንዳች ነገር እንዲጽፉ እናበረታታለን
-
4:42 - 4:44በእውነት ትንሽ የምትሉት ነገር ሊሆን ይችላል
-
4:44 - 4:46የእኔ እንደው የቅዳሜ ማለዳዎች ነው
-
4:46 - 4:50በራሱ መልካም መንገድ የሆነው
-
4:50 - 4:53እንዲያው ማመስገንን መለማመዳችን ነው
-
4:53 - 4:58ኢያን፣ ከፊል የሆነውን ንግግርን አስባለሁ፣ "ሚስትዬ"
-
4:58 - 4:59አዎን
-
4:59 - 5:00ይሄ በእርግጥም ይመቻል
-
5:00 - 5:02አዎን
-
5:05 - 5:08በእርግጥም
-
5:08 - 5:09ጋብቻን እንደ አማራጭ አድርገን ማሰብ እንደማንችል ወሰንን
-
5:09 - 5:11ያም ደግሞ ኢያን መግባባት እስኪችል ድረስ ነበር
-
5:11 - 5:12ነገር ግን እርሱ ከእኔ ጋር መግባባት ከቻለ
-
5:12 - 5:14ያኔ ጋብቻን ልናደርግ እንችላለን
-
5:14 - 5:17የእውነት የተለየ ነገር መሆኑን አውቀን ማለት ነው
-
5:17 - 5:19ነገር ግን ኢያን ሊያናግረኝ እስከ ቻለ ድረስ
-
5:19 - 5:21ያኔ የሚቻል ነገር እንዲሆን እናደርገዋለን
-
5:21 - 5:24ስለዚህ ኢያን አንዴ መግባባት ከጀመረ
-
5:24 - 5:26መጋባት በጥቂትም ቢሆን የሚቻል ነገር ይሆናል
-
5:26 - 5:29ከዚያም የኢያንን መሻሻል እያየነው እንሄዳለን
-
5:30 - 5:32ሰላም፣ ባሌ!
-
5:32 - 5:34ሰላም፣ ሚስትዬ!
-
5:34 - 5:36እንዴት ነህ?
-
5:36 - 5:38ደህና፣ እንዴት ነሽ?
-
5:38 - 5:39ምነው?
-
5:39 - 5:41እንዴት ነህ?
-
5:41 - 5:43ደህና ነኝ፣ አንቺን ማየቴ መልካም ነው
-
5:43 - 5:46ቀንህ እንዴት ነበር? መልካም?
-
5:46 - 5:47አዎን መልካም ነበር
-
5:48 - 5:50ከአባቱ ጋር የነበረኝ ውይይት ነበር
-
5:50 - 5:51ከውይይቶቹ አንዱ ያ ነበር
-
5:51 - 5:53ይሄ ሊሆን እንደሚችል ባስተዋልኩበት
-
5:53 - 5:57በዚያው የነሐሴ ወር አባቱ በአእምሮ ነቀርሳ እንደተያዘ በህክምና ታወቀ
-
5:57 - 6:01እናም በዚያ ነጥብ ላይ የአባቱ ትልቁ ስጋት የኢያን እና የእኔ ጉዳይ ሆነ
-
6:01 - 6:04እርሱም እንጋባ እንደሆን
-
6:04 - 6:06ወይም እንለያይ እንደሆነ እያሰቡ የሚጨነቁበት ነበር
-
6:06 - 6:08ህይወታችንን ወደ አንድ አቅጣጫ እንድንመራ
-
6:08 - 6:11ውሳኔ እንድናደርግ ይፈልጉ ነበር
-
6:12 - 6:15መተጫጨታችንን ማየት ከመቻላቸው በፊት ህይወታቸው አለፈች
-
6:15 - 6:22መተጫጨታችንን እንድንፈልገው ያደረገን የሚገፋፋን ነገር ያ ሁኔታ ነበር
-
6:28 - 6:29እርሱም በቅድመ-ጋብቻ የምክር አገልግሎት ሁሉ የሆነ ነበር።
-
6:29 - 6:33ይህንን ለአጭር ጊዜ የሆነ ጋብቻ ተጠቀምን
-
6:33 - 6:35በጣም ጠቃሚ ነበር፤ ምክኒያቱም ጆን ፓይፐር ስለዚህ ነገር ብዙ አስተምረው ነበር
-
6:35 - 6:38ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች እና ተከታይ ነገሮች በማለት
-
6:38 - 6:40ይሄም ደግሞ የእውነት ለእኛ ጠቃሚ ነበር
-
6:40 - 6:45ምክኒያቱም ጋብቻችንን ተግባራዊ በሆነ መልኩ እያስኬድነው ነበር
-
6:45 - 6:48ኢያን እንደ መስራት ያሉ ተከታይ ነገሮችን ማድረግ አይችልም
-
6:48 - 6:50ወይም ለእኔ ምግብ እንደ ማብሰል አይነቶቹን ነገሮች
-
6:50 - 6:52ይልቅ ሊያደርገው ይችል የነበረው ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር
-
6:52 - 6:54በመንፈሳዊ ነገር እኔን መምራቱ ነበር
-
6:54 - 6:55ኢያን ሁልጊዜ
-
6:55 - 6:58እግዚአብሔር ማነው ወደሚለው መሰረታዊ እውነት ይመለስ ነበር
-
6:58 - 7:00እናም እኔን ካለሁበት ስሜቶቼ ወደ ኋላ መለስ ያደርገኛል
-
7:00 - 7:02ያ ደግሞ በጣም ጠቃሚ የሆነው ነገር ነበር
-
7:03 - 7:07አብረናቸው መጽሐፍ የምናጠና ሁለት ጓደኞች ነበሩን
-
7:07 - 7:09እነርሱ በጥናቱ አንዳች ነገር እንዲያዩ ልንረዳቸው ችለናል ብዬ አስባለሁ
-
7:09 - 7:13ያም የሚደሰቱባቸው ጥቂት ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ
-
7:13 - 7:15ስለ ጋብቻ ልንደሰትባቸው የሚያስፈልገን ተገቢ ነገሮች
-
7:15 - 7:20ነገር ግን እነርሱ በጥቅሉ ፍጻሜ አይደሉም፣ ደግሞም የጋብቻቸው ሁሉም ነገር አይደሉም
-
7:21 - 7:24ነገር ግን እኛ ብዙ ነገር የምንማረው አለን
-
7:24 - 7:26ያንንም ከእነርሱ እየተማርነው ነው
-
7:26 - 7:27ደግሞም እነርሱ ከሚያካፍሉን ነገሮች
-
7:27 - 7:29ምክኒያቱም ግንኙነቶቻችን የተለዩ ናቸው
-
7:29 - 7:33አንዳችንም ከሌላችን የተለያዩ ነገሮችን እናገኛለን
-
7:33 - 7:36አንዳችን ለሌላችንን ይህንን መሰጠት
-
7:36 - 7:37እንድናደርግ የረዳን የሚመስለኝ አንድ ነገር
-
7:37 - 7:38ቢያንስ ለእኔ
-
7:38 - 7:40ኢያን እኔን ያልተወኝ መሆኑ ነው
-
7:40 - 7:43ሚናዎቹ የተቆጠቡ ቢሆኑ ኖሮ
-
7:43 - 7:46እናም እኛ እርስ በእርስ ብንዋደድ
-
7:46 - 7:50እናም እግዚአብሔር በጋብቻችን ውስጥ ታማኝ እንደሆነ ብናውቅ
-
7:51 - 7:53እርስ በእርሳችን ለመዋደድ እንችላለን
-
7:53 - 7:55ያም፣ እንደሚመስለኝ ከሆነ፣ የክርስቶስን በሚመስል ፍቅር ነው
-
7:55 - 7:57ምክኒያቱም ኢያን ከደረሰበት አካል ጉዳተኝነት የተነሳ
-
7:57 - 7:59እናም ያንን ፎቶ ተረዳሁት
-
7:59 - 8:01ጤናማ ከምትሆኑ ይልቅ በትንሹ ጤና ያላቸው ብትሆኑ
-
8:01 - 8:03ትስማማላችሁ?
-
8:03 - 8:04አዎን
-
8:05 - 8:09እግዚአብሔር ደስተኛ የምትሆኑበት ትዳር እንዲኖራችሁ ቢያደርግስ?
-
8:09 - 8:11ታውቃላችሁ...
-
8:11 - 8:11ምን?
-
8:11 - 8:13እርሱ አስደናቂ ነው!
-
8:13 - 8:14እርሱ አስደናቂ ነው?
-
8:14 - 8:16አዎን
-
8:29 - 8:33"በነፍሴ ዙሪያ ያሉት ሁሉ ተወት ሲያደርጉኝ እንግዲያውስ ተስፋዬ እና መቆያዬ ሁሉ የሚሆነው እርሱ ነው"
-
8:34 - 8:38ዲዛየሪንግ ጋድ የተሠኘው የማስተማር አገልግሎት የተመሰረተው
-
8:38 - 8:42እኛ በእርሱ በእጅጉ ስንረካ እግዚአብሔር በእጅጉ ይከብርብናል የሚለውን እውነት ለማስፋፋት ነው።
- Title:
- የኢያን እና ላሪሳ ታሪክ
- Description:
-
http://www.desiringgod.org/blog/posts/the-story-of-ian-larissa
የ ሲቲጌት ፊልም ዝግጅት
ቅንብር፣ ዝግጅት እና ጽሑፍ በ ካሮሊን ማክኩሌ
የፎቶግራፍ ዳይሬክቶር፡ ሚካኤል ሃርትኔት
ተጨማሪ ካሜራ፡ ሼፐርድ አለርስ፣ አንድሪው ላፓራ
የቦታ ድምጽ፡ ስቴፋን ግሪን
የዝግጅት አማካሪ፡ ዴቪድ አልትሮጌ
ዋናው ሙዚቃ በሮጀር ሆፐር
አርትኦት በ ሱዛን ቴይለር
ተጨማሪ አርትኦት በ፡ ስቴፋን ግሪን፣ አንድሪው ላፓራ
የድምጽ ቅንብርና ንድፍ በ ዳላስ ቴይለር፣ ሲኤኤስኮፒ ራይት 2011 ዲዛየሪንግ ጋድ
- Video Language:
- English
- Duration:
- 08:54