< Return to Video

ባንከር ሮይ: ከቤርፉት እንቅስቃሴ እንማር

  • 0:00 - 0:04
    ወደ ሌላ ዓለም ልወስዳቹ እፈልጋለው ።
  • 0:04 - 0:06
    ማካፈል መፈለገው ነገርም አለ ።
  • 0:06 - 0:10
    እሱም የ45 ዓመት የ ፍቅር ታሪክነው ።
  • 0:10 - 0:13
    ከድህነት ጋር ያለ ፍቅር
  • 0:13 - 0:16
    በ ቀን ከ 1 ዶላር በታች መኖር ።
  • 0:18 - 0:22
    የተማርኩት ከዲታ ጋር ነው
  • 0:22 - 0:26
    የህንድ ሀገር ሃብታም ትመሀርት ቤት
  • 0:26 - 0:29
    ነገር ገን ያ ሊገለኝ ነበር ።
  • 0:31 - 0:33
    ሁሉ ነገር ተዘጋጅቶልኝ ነበር ።
  • 0:33 - 0:36
    ዲፕሎማት፣ መምህር፣ሐኪም ለመሆን ።
  • 0:36 - 0:40
    ሁሉ ነገር ተስተካክሎልኝ ነበር ።
  • 0:40 - 0:43
    ከሱም ጭምር፤ አይመስልም አንጂ የ ህንድ ሃገር ናሽናል ቻምፒዮን ነበርኩኝ
  • 0:43 - 0:45
    ለ 3 ዓመት ።
  • 0:45 - 0:47
    (ሣቅታ)
  • 0:47 - 0:50
    ዓለም ባጠቃላይ ተሰታኝ ነብር ።
  • 0:50 - 0:52
    ሁሉ ነገር በእጄ ውስጥ ነበር ።
  • 0:52 - 0:55
    ምንምን ቢሆን ልበላሽ ኣልችልም ።
  • 0:55 - 0:57
    ነገር ግን የሆነ ጉጉት ያዘኝ
  • 0:57 - 0:59
    አስቲ ሄጄ ገጠር መስራት ልሞክር
  • 0:59 - 1:01
    አዛ መኖር ምን አንደሚመስል እስቲ ሊየው ።
  • 1:01 - 1:03
    ስለዚህ በ 1965 (አ/አ)
  • 1:03 - 1:07
    ህንድ ውስጥ የነበረው ሃይለኛው የቢሀርን ቸነፈር ለማይት ሄድኩኝ ።
  • 1:07 - 1:10
    ረሀብና ሞትን አየው ።
  • 1:10 - 1:13
    ለመጀመሪያ ግዜ ሰው በረሀብ ሲሞት አየው ።
  • 1:13 - 1:16
    ሂወቴን ቀየረው ።
  • 1:16 - 1:18
    ቤት ተመልሼ
  • 1:18 - 1:20
    አናቴን
  • 1:20 - 1:23
    ገጠር ኖሬ መስራት ፈልጋለው ኣልኳት ።
  • 1:23 - 1:25
    አናቴ ኮማ ውስጥ ገባች ።
  • 1:25 - 1:28
    (ሣቅታ)
  • 1:28 - 1:30
    ምን ማለት ነው ይሄ?
  • 1:30 - 1:33
    ዓለም ሁሉ በእጅህ ነው ያለው፣ የፈለከውን ስራ መስራት ትችላለህ፣
  • 1:33 - 1:35
    ያ ሁሉ አያለህ ገጠር ልስራ ትላለህ አንዴ?
  • 1:35 - 1:37
    ትንሽ አሞሃል አንዴ?
  • 1:37 - 1:39
    አንዲ ብዬ መለስኩላት፥ "ኣይ፦ ምርጥ ትመህርት አለኝ
  • 1:39 - 1:41
    አሳሰበኝና
  • 1:41 - 1:44
    የደረሰኝን እድል መመለስ ፈልጋለው
  • 1:44 - 1:46
    በራሴ መንገድ ።"
  • 1:46 - 1:48
    "ገጠር ምን ልታረግ ነው?
  • 1:48 - 1:50
    ስራ የለ፣ ገንዘብ የለ...
  • 1:50 - 1:52
    ማረጋገጫ የለ፣ ፍንኦት የለ ።"
  • 1:52 - 1:54
    አኔም አንዲህ አልኳት ፥ "መኖር ፈልጋለው
  • 1:54 - 1:57
    ለ 5 ዓመት መቆፈር ፈልጋለው ።"
  • 1:57 - 1:59
    "ለ 5 ዓመት መቆፈር ፈልጋለው?" አለች::
  • 1:59 - 2:02
    "ህንድ ውስጥ ካሉት ውድ ትምሀርት ቤትና ኮሌጅ ተመረሀ
  • 2:02 - 2:04
    ለ 5 ዓመት መቆፈር ፈልጋለው ትላለህ?"
  • 2:04 - 2:08
    ለ ብዙ ጊዜ ኣላናገረቺኝም::
  • 2:08 - 2:11
    ምክንያቱም ቤተሰቤን ቅር ያሰኘው ነው የመሰላት::
  • 2:13 - 2:15
    ነገር ገን
  • 2:15 - 2:18
    ልዩ እውቀትና ሞያ ተማርኩኝ
  • 2:18 - 2:20
    እጅግ በጣም ደሃ የሆኑ ሰዎች የሚያውቁት
  • 2:20 - 2:23
    እድባዊ ትምህርት መቼም የማይሆን
  • 2:23 - 2:25
    መቼም ያልተ ከበረ፣ ስም ያለተሰጠው
  • 2:25 - 2:27
    ውይም በትልቁ ያልታየ ።
  • 2:27 - 2:29
    ያኔ ነው ቤርፉት (Barefoot) ኮሌጅን ልጀምር ያልኩት
  • 2:29 - 2:31
    የድሃ ብቻ ኮሌጅ ።
  • 2:31 - 2:33
    የ ድሃ ሐሳብ የሚከበርበት
  • 2:33 - 2:36
    ኮሌጅ እንዲሆን ።
  • 2:37 - 2:39
    ለመጀመሪያ ግዜ የ ገጠር መንደር ውስጥ ሄድኩ ።
  • 2:39 - 2:41
    አዛውንቶች ወደኔ መተው፤
  • 2:41 - 2:43
    "ከ ፖሊስ እያመለጥክ ነው?" አሉኝ።
  • 2:43 - 2:45
    "አይደለም" አልኩኝ
  • 2:45 - 2:48
    (ሣቅታ)
  • 2:49 - 2:51
    "ፈተና ወደክ?" ብለው ጠየቁኝ
  • 2:51 - 2:53
    "አይደለም" አልኩኝ
  • 2:53 - 2:56
    "የመንግስት ስራ አጣህ?" አሁንም ፥ አይደለም፣ አልኩኝ
  • 2:56 - 2:58
    " እዚህ ምንታረጋለህ ታድያ
  • 2:58 - 3:00
    ለምን መጣህ?
  • 3:00 - 3:02
    የህንድ ሃገር ትምህርት
  • 3:02 - 3:05
    ወደ ፓሪስ፣ ኒው ዴሊህና ዙሪክ ነው ሊወስድህ የሚገባው
  • 3:05 - 3:07
    እዚህ ባላገር ውስጥ ምን ትሰራለህ?
  • 3:07 - 3:10
    የደበከን ነገር ኣለ አንዴ?"
  • 3:10 - 3:13
    "ኣይ ፤ ኮሌጅ መክፈት ነው ምፈልገው
  • 3:13 - 3:15
    ለ ድሃ ብቻ የሚሆን ኮሌጅ ።
  • 3:15 - 3:18
    የድሃ ሐሳብ የሚከበርበትና የሚገለጽበት ።"
  • 3:18 - 3:22
    አዛውንቶቹም ይሄን ሰምተው ትልቅ መክር ሰጡኝ
  • 3:22 - 3:24
    አንዲህ ኣሉኝ፥ "እባክህን...
  • 3:24 - 3:27
    ዲግሪና ዲፕሎማ ያለውን ሰው እንዳታመጣብን
  • 3:27 - 3:29
    እዚህ ኮሌጅ ውስጥ ።"
  • 3:29 - 3:32
    ስለዚህ ይሄ ኮሌጅ ብቻ ነው ህንድ ውስጥ
  • 3:32 - 3:35
    ዶክቶሬት ወይም ማስትሬት ካላቹ
  • 3:35 - 3:37
    ማይቀበላቹ ።
  • 3:37 - 3:42
    ያልተሳካላቹ፣ ያልተሟላላቹ፣ ወይም ከትምህርት ቤት ያቇረጣቹ
  • 3:42 - 3:45
    መሆን አለባቹህ ኮሌጅ ውስጥ ለመግባት ።
  • 3:45 - 3:47
    የእጅ ስራ ማወቅ እለባቹ ።
  • 3:47 - 3:49
    የስራ ክብር እንዲኖራች ያስፈለጋል ።
  • 3:49 - 3:52
    ለማኅበረሰቡ ጥበብ እንዳላቹ ማሳየት አለባቹ
  • 3:52 - 3:55
    አናም ለዚህ ማኅበረሰብ አገልግሎት ማሳየት ይገባቿል ።
  • 3:55 - 3:58
    ስለዚህ ቤርፉት ኮሌጅን ከፈትን
  • 3:58 - 4:00
    ሞያን ኣዲስ ስም ሰጠነው ።
  • 4:00 - 4:02
    ማነው ባለሞያ?
  • 4:02 - 4:04
    ባለሞያ ሰው ማለት
  • 4:04 - 4:06
    ችሎታ ያለውና
  • 4:06 - 4:09
    በራሱ የሚተማን ነው ።
  • 4:09 - 4:12
    ውሃ ኣስገኚ (water diviner) ባለሞያ ነው ።
  • 4:12 - 4:14
    ባህላዊ አዋላጅ ፤
  • 4:14 - 4:16
    ባለሞያ ናት ።
  • 4:16 - 4:19
    ባህላዊ ወጌሻ ባለሞያ ነው ።
  • 4:19 - 4:21
    እነዚህ ዓለም ውስጥ ባጠቃላይ ባለሞያ ናቸው ።
  • 4:21 - 4:25
    የትም ገጠር ውስጥ ልታገኟቸው ትችላላቹ ።
  • 4:25 - 4:28
    ስለዚህ አነዚህ ሰዎች ወደ መደበኛ ሂወት መምጣት ይገባቿል ብለን አሰብን
  • 4:28 - 4:31
    ያላቸው እውቀትና ሞያ
  • 4:31 - 4:33
    አቀፋዊ ነው ።
  • 4:33 - 4:35
    መጠቀም አለበት፣ ተግባር ላይ መዋል አለበት ።
  • 4:35 - 4:37
    ዓለም ሁሉ ማወቅ አለበት
  • 4:37 - 4:39
    እነዚህ እውቀቶችና ሞያዎች
  • 4:39 - 4:43
    አግባብ እንዳላቸው ዛሬ ።
  • 4:43 - 4:45
    ስለዚህ ኮሌጁ
  • 4:45 - 4:49
    የ ማሕትማ ጋንዲን አኗኗርና አሰራርን የሚከተል ነው ።
  • 4:49 - 4:53
    መሬት ላይ ትበላለህ፣ መሬት ላይ ትተኛለህ፣ መሬት ላይ ትሰራለህ ።
  • 4:53 - 4:55
    ውል (contract) ኣይጻፍም ።
  • 4:55 - 4:58
    ለ 20 ዓመት መቅረት ትችላልለህ ውይም ነገ መሄድ ትችላልለህ ።
  • 4:58 - 5:01
    ደሞም፣ ማንም ከ100 ዶላር በላይ አያገኝም በውር ።
  • 5:01 - 5:04
    ለገንዘብ ከመጣህ ቤርፉት ኮሌጅ ላንተ አይደለም ።
  • 5:04 - 5:06
    ለስራና ለፍልምያ ነው ምትመጠው
  • 5:06 - 5:08
    ያኔ ቤርፉት ኮሌጅ ላንት ነው ።
  • 5:08 - 5:11
    ታድያ የፈለጋቹትን ሐሳብ ማቅረብ ትችላላቹ እዚህ ።
  • 5:11 - 5:13
    ማንኛውም ሐሳብ ሲኖራቹ መታቹ ሞክሩት ።
  • 5:13 - 5:15
    ባይሳካ ምንም ኣይደለም ።
  • 5:15 - 5:18
    ወድቃቹ ፣ ቆስላቹ ፣ ድጋሚ መሞከር ነው ።
  • 5:18 - 5:21
    አስተማሪ ተማሪ የሆነበትና
  • 5:21 - 5:24
    ተማሪ አስተማሪ የሆነበት ኮሌጅ ይሄ ብቻ ነው ።
  • 5:24 - 5:27
    ደሞም፣ ይሄ ኮሌጅ ብቻ ነው ሰርቲፊኬት የማይሰጥበት ።
  • 5:27 - 5:30
    ባገለገልከው መሐበር ውስጥ ነው ምስጋና የሚደርስህ ።
  • 5:30 - 5:32
    መሃንዲስ መሆንህን የሚያሳውቅ
  • 5:32 - 5:35
    ግድግዳ ላይ ወረቀት መስቀል አያስፈለግህም ።
  • 5:37 - 5:39
    አንደዛ ስላቸው
  • 5:39 - 5:42
    "እንደሱ ከሆነ አስቲ ኣሳየን እንደሚቻል? በለው ጠየቁኝ ።
  • 5:42 - 5:46
    ወሬ ብቻ ምን ያረጋል ተግባር ካልታየ?" አሉኝ ።
  • 5:46 - 5:49
    ስለዚህ የመጀመሪያውን ቤርፉት ኮሌጅን ገነባን።
  • 5:49 - 5:52
    በ 1986 (አ/አ)
  • 5:52 - 5:54
    ሁለት ባዶ እግራቸው የሆኑ የህንፃ ነዳፊዎች ናቸው የገነቡት
  • 5:54 - 5:56
    ማንበብና መጻፍ የማይችሉ
  • 5:56 - 5:59
    በ ሜትር ካሬ 0.13 ሳንቲም ብቻ (ዶላር)
  • 5:59 - 6:03
    150 ሰዎች እዛ ይኖሩ ነበር፤ ይሰሩ ነበር ።
  • 6:03 - 6:06
    በ 2002 (አ/አ) የ ህንፃ ነዳፊ ኣጋ ካን (Aga Khan) ሽልማትን ተሸለሙ ።
  • 6:06 - 6:09
    ነገር ግን ሌላ የእውነተኛ የህንፃ ነዳፊ ነው የሰራው ብለው ጠረጠሩ ።
  • 6:09 - 6:11
    "አዎ ፕላኑን ሰርተዋል" ፤ አልኳቸው
  • 6:11 - 6:15
    "ግን፤ የቤርፉት ህንፃ ነዳፊዎች ናቸው ኮሌጁን የገነቡት ።"
  • 6:16 - 6:19
    የ 50 000 ዶላር ሽልማቱን አስመለሱን ፣ ለመጀመሪያ ግዜ በአጋካን ታሪክ
  • 6:19 - 6:21
    ስላላመኑን
  • 6:21 - 6:25
    ይሄ ታድያ በ ቲሎኒያ የህንፃ ነዳፊዎች
  • 6:25 - 6:28
    ጎጂ ትችት የደረሰባቸው መስሎን ነበር ።
  • 6:28 - 6:30
    የ ጫቃ ኣዋቂ ጠየኩኝ
  • 6:30 - 6:33
    ታዋቂ ዲፕሎማ ያለውና ባለሙያ የተባለው
  • 6:33 - 6:36
    እንዲህ ኣልኩት፥ "እዚህ መሬት ላይ መን መገንባት ትችላለህ?"
  • 6:36 - 6:38
    አየት አረገውና፥ "ባክህ ተስፋ የለውም፣ ምንም ኣይሰራም አዚህ ላይ
  • 6:38 - 6:40
    መሞከርም አያስፈልግም" ብሎ መለሰልኝ ።
  • 6:40 - 6:42
    "ውሃ የለው ፤ መሬቱ ድንጋያማ"
  • 6:42 - 6:44
    እንዲህ ሲለኝ ገረመኝ ።
  • 6:44 - 6:46
    እሺ፣ እንግዲያውስ ገጠር ሄጄ አንዱን ሽማግሌ
  • 6:46 - 6:49
    ልጠይቀው፥ "እዚህ መሬት ላይ መን ምን ልዝራ?"
  • 6:49 - 6:51
    ፀጥ ብሎ ኣየኝና እንዲህ አለኝ፥
  • 6:51 - 6:53
    "ይሄንን፤ ያንን፤ ይሄንን፤ ስራና ሁሉም ይሳካል ።"
  • 6:53 - 6:56
    ዛሬ ይሄንን ይመስላል ።
  • 6:57 - 6:59
    ጣራ ላይ ስወጣ
  • 6:59 - 7:01
    ሴቶቹ፥ "ዞር በል!" አሉኝ ።
  • 7:01 - 7:04
    "ወንዶ ሁሉ ይሂዱልን ከዚህ፣ ይሄን ሙያ ማሳየት አንፈልግም ።
  • 7:04 - 7:06
    ይሄ ጣራዉ ውስጥ ውሃ እንዳይገ የሚደረግ ስልት ነው ።
  • 7:06 - 7:08
    (ሣቅታ)
  • 7:08 - 7:11
    የሆነ ስኳር መሳይ ማጣበቂያ፤ የሆነ ዕንጨት ... ምናምን
  • 7:11 - 7:13
    ሌላም ነገሮች ነበሪት ...ብቻ እኔጃ ።
  • 7:13 - 7:15
    ግን ምንም ውሃ አያሳልፍም ።
  • 7:15 - 7:18
    ከ1986 (አ/አ) አስካሁን ድርስ አንድም ውሃ ጠብ አላለም ።
  • 7:18 - 7:21
    ይሄንን ሙያ ሴቶቹ ከወንዶቹ ጋር ማካፈል አልፈለጉም ።
  • 7:21 - 7:24
    (ሣቅታ)
  • 7:24 - 7:26
    በዓለም ላይ ያኛ ኮሌጅ ብቻ ነው
  • 7:26 - 7:30
    በ ፀሐይ ኀይል ኤሌክትሪኩ የሚሰራው ።
  • 7:30 - 7:32
    ሁልም ሃይሉ ከ ፀሐይ ነው የሚመጣው ።
  • 7:32 - 7:34
    45 ኪሎዋት አለ ጣራው ላይ ።
  • 7:34 - 7:36
    ሁሉ ነገር በደንብ ነው የሰራው ለ 25 ዓመት ።
  • 7:36 - 7:38
    ፀሐይ እስካለች
  • 7:38 - 7:40
    ምንም የኤሌክትሪት ችግር ኣይኖረንም ።
  • 7:40 - 7:42
    ከሁሉም ደስ የሞለው ግን
  • 7:42 - 7:45
    ይሄ የፀሐይ ሃልይ የተሰራው
  • 7:45 - 7:48
    በ አንድ ቄስ ነው ፤ ሂንዱ ቄስ
  • 7:48 - 7:51
    የመጀመሪያ ደረጃ ብቻ ትምህርት የተማረ ሰው
  • 7:51 - 7:54
    ሌላም ኣልተማረም ኮሌጅም አልሄደም ።
  • 7:54 - 7:56
    ስለ ፀሐይ ሃይል
  • 7:56 - 8:00
    ከማውቀው ሰው ሁሉ በላይ ያውቃል ።
  • 8:02 - 8:04
    ለምሳሌ ቤርፉት ኮሌጅ ከመጣቹ ምግብ የሚሰራው
  • 8:04 - 8:07
    በ ፀሐይ ሃይል ነው ።
  • 8:07 - 8:10
    ይ ሄንን የፀሐይን ማብሰያ የሰሩት
  • 8:10 - 8:13
    ሴቶች ናቸው
  • 8:13 - 8:15
    ያልትመሩ ሴቶች፣
  • 8:15 - 8:17
    ይሄንን የረቀቀ
  • 8:17 - 8:19
    በ ፀሐይ ሃይል የሚሰራ ማብሰያ የፈጠሩት ።
  • 8:19 - 8:22
    የ Scheffler የፀሐይ ሥነ መላ ማብሰያ ነው ።
  • 8:25 - 8:29
    በሚያሳዝን ሁኔታ ግማሽ ጀርመን ናቸው
  • 8:29 - 8:31
    በጣም በትክክሉ ከመሰራታቸው የተነሳ ።
  • 8:31 - 8:33
    (ሣቅታ)
  • 8:33 - 8:36
    እንደነዚህ ያሉ ጠንቃቃ የህንድ ሴቶች የትም አታገኙም ።
  • 8:37 - 8:39
    አስከመጨረሻው ድረስ
  • 8:39 - 8:41
    ይሄንን ማብሰያ በትክክል አርገው የሰሩታል ።
  • 8:41 - 8:43
    በቀን ሁለቴ 60 ምግብ እናቀርባለን
  • 8:43 - 8:45
    በዚህ የፀሐይ ማብሰያ ።
  • 8:45 - 8:47
    የጥርስ ሐኪም አለን ፤
  • 8:47 - 8:50
    አያት ናቸው፣ ያልተማሩ፣ የጥርስ ሐኪም ።
  • 8:50 - 8:52
    የ 7000 ልጅ ጥርስ
  • 8:52 - 8:55
    ያክማሉ ።
  • 8:56 - 8:58
    የቤርፉት ሥነ መላ ፥
  • 8:58 - 9:01
    በ1986 (አ/አ)፥ መሐንዲስ የለ፤ የህንፃ ነዳፊ የለ፤
  • 9:01 - 9:04
    ነገር ግን ከጣራላይ የዝናብ ውሃ እያጠራቀምን ።
  • 9:04 - 9:06
    በጣም ትንሽ ውሃ ነው የምናባክነው ።
  • 9:06 - 9:08
    ጣራዎቻችን በሞላ መሬት ስር ካሉት
  • 9:08 - 9:10
    የ 400 ሺህ ሊትር ታንኮች የተገናኙ ናቸው
  • 9:10 - 9:12
    ምንም ውሃ ኣይባክንም ።
  • 9:12 - 9:15
    የ4 ዓመት ድርቅ ቢመጣ በቂ ውሃ አለን ለዛ ሁሉ ግዜ
  • 9:15 - 9:17
    ምክንያቱም የዝናብ ውሃ እናጠራቅማለን ።
  • 9:17 - 9:20
    60 % ልጆች ትምህርት ቤት ኣይሄዱም
  • 9:20 - 9:22
    ምክንያቱም እረኛ ናቸው ፥
  • 9:22 - 9:24
    በግ፣ ፍየል ይጠባሉ ።
  • 9:24 - 9:26
    ውይም የቤት ዕለታዊ ሥራ መስራት ይኖርባችዋል ።
  • 9:26 - 9:29
    ስለዚህ የማት ትምህርትቤት
  • 9:29 - 9:31
    ለመስራት አቀድን ለልጆቹ ።
  • 9:31 - 9:33
    ምክንያቱም ይሄ የማታ ቲሎንያ (Tilonia) ትምህርትቤት ውስጥ
  • 9:33 - 9:36
    75,000 ልጆች ተምረውበታል ።
  • 9:36 - 9:38
    ለልጆቹ ምቾት እንጂ ፤
  • 9:38 - 9:40
    ለ አስተማሪዎች ምቾት አይደለም ።
  • 9:40 - 9:42
    ታድያ ምንድነው የምናስተምረው?
  • 9:42 - 9:44
    ዴሞክራሲ ፤ ዜግነት ፤
  • 9:44 - 9:47
    መሬት አንዴት እንደሚለካ ፤
  • 9:47 - 9:49
    በፖሊስ ከተያዙ ምን ማረግ እንዳለባቸው ፤
  • 9:49 - 9:53
    ከብቶቻቸው ከታመሙ ምን ማረግ እንዳለባቸው ።
  • 9:53 - 9:55
    ይሄንን ነው ምናስተምረው ያማታ ትምህርቤታችን ውስጥ ።
  • 9:55 - 9:58
    ትምህርትቤቶቹ ሁሉ ከፀሐይ በመጣው ሃይል የበሩ ናቸው ።
  • 9:58 - 10:00
    በየ 5 ዓመቱ
  • 10:00 - 10:02
    ምርጫ እናካሄዳለን ።
  • 10:02 - 10:06
    ከ 6 አስከ 14 ዓመት ያሉ ልጆች
  • 10:06 - 10:09
    በዴሞክራሲ በተካሄደ ምርጫ
  • 10:09 - 10:13
    ጠቅላይ ሚኒስቴር ይመርጣሉ ።
  • 10:13 - 10:16
    ያሁንዋ ጠቅላይ ሚኒስቴር 12 ዓመትዋ ነው ።
  • 10:17 - 10:19
    ቀን ላይ 20 ፍየሎችን ትጠብቃለች ፣
  • 10:19 - 10:22
    ማታ ላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነች ።
  • 10:22 - 10:24
    የመንግስት ካብኔ አላት ፣
  • 10:24 - 10:27
    የትምህርት ሚኒስቴር ፣ የ መብራት ኃይል ሚኒስቴር ፣ የጤና ሚኒስቴር ።
  • 10:27 - 10:29
    150 ትምህርት ቤትና 7000 ልጆችን
  • 10:29 - 10:32
    ይቆጣጠራሉ ።
  • 10:34 - 10:36
    የዛሬ 5 ዓመት የዓለምን የልጆች ሽልማትን ተሸለመች ።
  • 10:36 - 10:38
    ከዛም ስዊድን ሀገር ተጋበዘች ።
  • 10:38 - 10:40
    ለመጀመሪያ ግዜ ከመንደርው ወጣች ።
  • 10:40 - 10:43
    ስዊድንን አይታ አታውቅም ነበር ።
  • 10:43 - 10:45
    ነገሮች ምንም አልደነቋትም ነበር ።
  • 10:45 - 10:47
    የስዊድን ንግስት ስትተዋወቃት
  • 10:47 - 10:50
    እንዲህ ብላ ጠየቀችኝ፥ "ልብዋ እንዲህ የሞላው እንዴት ሆኖ ነው? ብለህ ጠይቅልኝ" አልቺኝ ።
  • 10:50 - 10:52
    "12 ዓመትዋ ብቻ ነው ፣
  • 10:52 - 10:55
    ና ምንም ነገር የደነቃት ወይም ያስፈራት ኣይመስልም ።"
  • 10:55 - 10:58
    በስተግራዋ ቆማ የነበረችው ልጅትዋም
  • 10:58 - 11:01
    የንግስትዋን ዓይን በደንብ እያየች እንዲህ አለቻት፥
  • 11:01 - 11:04
    "እባኮን ጠቅላይ ምንስቴር ነኝ ብለው ይንገሩልኝ ።"
  • 11:04 - 11:06
    (ሣቅታ)
  • 11:06 - 11:14
    (ጭብጨባ)
  • 11:14 - 11:18
    ማንበብ ለማይችሉ
  • 11:18 - 11:21
    በአሻንጉሊት እናስተምራለን ።
  • 11:21 - 11:24
    ምንነጋገረው በአሻንጉሊት ነው ።
  • 11:30 - 11:33
    ለምሳሌ ፣ ጆኪም ቻቻ አለ
  • 11:33 - 11:37
    እድሜው 300 ዓመት ነው ።
  • 11:37 - 11:40
    የአእምሮ ሀኪሜ ነው ፣ አስተማሪኤ ነው ።
  • 11:40 - 11:42
    ሀኪሜ ነው ፣ጠበቃኤ ነው ።
  • 11:42 - 11:44
    ለጋሼ ነው ።
  • 11:44 - 11:46
    ገንዘብ ሁሉ ይሰበስብልናል
  • 11:46 - 11:49
    ንትርክ ይፈታልናል ፣
  • 11:49 - 11:52
    መንደራችን ውስጥ ያለውን ችግር ሁሉ ይፈታልናል ።
  • 11:52 - 11:54
    ጥላቻ ከተፈጠረ መንደራችን ውስጥ ፤
  • 11:54 - 11:56
    ተማሪዎች ትምህርት ቤት መምጣት ከቀነሱ ፤
  • 11:56 - 11:58
    አስተማሪውችና ቤተሰቦች ካልተስማሙ ፤
  • 11:58 - 12:01
    አሻንጉሊቱ ሁሉንም ኣስተማሪና ቤተሰብን ጠርቶ
  • 12:01 - 12:03
    ተጨባበጡ ፣
  • 12:03 - 12:05
    ተማሪዎቻችን መማር መቀጠል አለባቸው ፣ ይላችዋል ።
  • 12:07 - 12:09
    እነዚህ አሻንጉሊቶች
  • 12:09 - 12:11
    በ ውርልድ ባንክ ትርፍራፊ ወረቀቶች የተሰሩ ናቸው ።
  • 12:11 - 12:13
    (ሣቅታ)
  • 12:13 - 12:20
    (ጭብጨባ)
  • 12:20 - 12:24
    ይሄ ከባድና የማይቻል የመሰለ የ ፀሐይ ሥነ መላ ፥
  • 12:24 - 12:26
    በየመንደሩ አለ ።
  • 12:26 - 12:28
    ህንድ ሀገርን በሞላ አድርሰናል
  • 12:28 - 12:31
    ከ ላዳክ (Ladakh) እስከ ቡታን (Bhutan)
  • 12:33 - 12:35
    መንደሮቹ ሁሉ በ ፀሐይ ሃይል በርተዋል
  • 12:35 - 12:38
    እድሜ ለ ተማሪዎቻችን ስልጠና ።
  • 12:39 - 12:41
    ላዳክ ሄድንና
  • 12:41 - 12:43
    አንድዋን ሴትዮ እንዲህ ብለን ጠየቅናት ፥
  • 12:43 - 12:46
    በነገራችን ላይ ፣ ቅዝቃዜው -40 ፣ነገር ግን
  • 12:46 - 12:49
    ደጅ መውጣት ነበረብን ምክንያቱም በረዶ በየበኩሉ ነበር ፣
  • 12:49 - 12:51
    ሴትያዋን እንዲህ ብለን ጠየቅናት ፥
  • 12:51 - 12:53
    "ምን ጠቀማቹ ይሄ የ ፀሐይ ሃይል
  • 12:53 - 12:55
    ኤለክትሪክ በመኖሩ?"
  • 12:55 - 12:57
    ለ አንድ ደቂቃ አሰበችና እንዲህ አለች፥
  • 12:57 - 13:01
    ለመጀመርያ ግዜ በክረምት ወቅት የባለቤቴን ፊት ማየት ቻልኩኝ።
  • 13:01 - 13:04
    (ሣቅታ)
  • 13:04 - 13:06
    አፍጋኒስታንም ሄድን ።
  • 13:06 - 13:11
    ከህንድ የተማርነው አንድ ነገር ፤
  • 13:11 - 13:15
    ወንዶች ምንም አይሰለጥኑም ።
  • 13:15 - 13:19
    (ሣቅታ)
  • 13:19 - 13:21
    ወንዶች አርፈው መቀመጥ አይችሉም ፤
  • 13:21 - 13:23
    ወንዶች ታታሪ ናቸው ፤
  • 13:23 - 13:26
    ወንዶች ብዙ መነቃነቅ ይወዳሉ ፤
  • 13:26 - 13:28
    ደግሞም ሁሉም ሰርተፊኬት ይፈልጋሉ ።
  • 13:28 - 13:30
    (ሣቅታ)
  • 13:30 - 13:33
    የዓለም ወንዶች ሁሉ ያቺን
  • 13:33 - 13:35
    ሰረተፊኬት የፈልጓታል ።
  • 13:35 - 13:38
    ለምን? ምክንያቱም ከገጠር መውጣት ይፈለጋሉ
  • 13:38 - 13:41
    ወደ ከታማ ሰራ መፈለግ ይሻላችዋል ።
  • 13:41 - 13:44
    ስለዚህ ጥሩ መፍትሄ አቀረብን ፥
  • 13:44 - 13:46
    የሴት አያቶችን ማሰልጠን ።
  • 13:48 - 13:50
    ዘንድሮ ዓለም ላይ ዋና የወሬ
  • 13:50 - 13:52
    ማሰራጫ ምንድን ነው?
  • 13:52 - 13:54
    ቴሌቪዥን? አይደለም
  • 13:54 - 13:56
    ቴሌግራፍ? አይደለም
  • 13:56 - 13:58
    ስልክ? አይደለም
  • 13:58 - 14:00
    ለሴት ማናገር ።
  • 14:00 - 14:03
    (ሣቅታ)
  • 14:03 - 14:07
    (ጭብጨባ)
  • 14:07 - 14:09
    እንድግዲህ፣ ለመጀመሪያ ግዜ አፍጋኒስታን ሄድን
  • 14:09 - 14:11
    3 ሴቶችን ለመውሰድ ተዘጋጀን
  • 14:11 - 14:13
    እንዲም አልን፥ "ህንድ ሀገር ልንወስዳቸው እንፈለጋለን ።"
  • 14:13 - 14:15
    "በተዓምር አይሆንም፣ ከቤታቸውም አይወጡም ፣
  • 14:15 - 14:17
    እንኯን ህንድ ሊሄዱ ።"
  • 14:17 - 14:19
    እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩላቸው "ባለቤቶቻቸውንም እንወስዳለን" ።
  • 14:19 - 14:21
    ስለዚህ፣ ባለቤቶቻቸውም መጡ ።
  • 14:21 - 14:24
    በእርግጥ ሰቶቹ ከወንዶቹ ይበልጥ ብልህ ነበሩ ።
  • 14:24 - 14:26
    በ 6 ወር ውስጥ
  • 14:26 - 14:29
    እንዴት ነው ሴቶቹን የምናሰለጥነው?
  • 14:29 - 14:31
    በምልክት መነጋገር ።
  • 14:31 - 14:34
    ፅሁፍን አለመጠቀም ።
  • 14:34 - 14:36
    ንግግርን አለመጠቀም ።
  • 14:36 - 14:39
    የምልክት ቋንቋ ብቻ ።
  • 14:39 - 14:41
    በ 6 ወር ውስጥ
  • 14:41 - 14:45
    የ ፀሐይ ኀይል መሃንዲስ ይሆናሉ ።
  • 14:45 - 14:48
    ሀገራቸው ገብተው የ ፀሐይ ኀይል ኤሌክትሪክን ያስገባሉ ።
  • 14:48 - 14:50
    ይቺህ ሴትዮ ሄዳ
  • 14:50 - 14:53
    የመጀመሪየውን መንደር በፀሐይ ኀይል አበራችው ፣
  • 14:53 - 14:55
    (ስልጠና አዘጋጅታ)
  • 14:55 - 14:58
    በ አፍጋኒስታን ውስጥ የመጀመሪየው መንደር በ ፀሐይ ኀይል የሰራው
  • 14:58 - 15:01
    ዕድሜ ለነዚህ 3 ሴቶች ነው ::
  • 15:01 - 15:03
    ይቺህ ሴትዮ
  • 15:03 - 15:05
    ልዩ አያት ናት ።
  • 15:05 - 15:10
    በ 55 ዓመቷ 200 ቤቶችን አፍጋኒስታን ውስጥ በ ፀሐይ ኀይል አብርታለች ።
  • 15:10 - 15:13
    እስካሁን ምንም አልተበላሹም ።
  • 15:13 - 15:16
    እንደውም የአፍጋኒስታን ምሕንድስና መምሪያ ሄዳ ንግ ግር አርጋለች
  • 15:16 - 15:18
    ዋናውን ኀላፊ
  • 15:18 - 15:20
    የACና የDCን ልዮነት አስተማረችው ።
  • 15:20 - 15:22
    አያቅም ነበረ ።
  • 15:22 - 15:25
    እነዚ 3 ሴቶች ሌላ 27 ሴቶችን አሰልጥነዋል ።
  • 15:25 - 15:28
    100 መንደሮችን በ ፀሐይ ኀይል አብርተዋል ።
  • 15:28 - 15:31
    አፍሪካ ሄድን ፣
  • 15:31 - 15:33
    አንዳይነት ነገር አደረግን ።
  • 15:33 - 15:36
    ከ 8 ፣ 9 የተልየያዩ ሀገሮች የመጡ ሴቶች ቁጭ በለው ነበር ።
  • 15:36 - 15:39
    ሁሉም የተለያዪ ቋንቋ ስለሚናገሩ አይግባቡም ነበር
  • 15:39 - 15:41
    ግን እንደምንም ይነጋገሩ ነበር ።
  • 15:41 - 15:43
    የምልክት ንግግራቸው ይበቃቸው ነበር ለመግባባት ።
  • 15:43 - 15:45
    ዕርስ በዕርስ እየተነጋገሩ ፣
  • 15:45 - 15:47
    የ ፀሐይ ኀይል መሃንዲስ ሆነዋል ።
  • 15:47 - 15:50
    ስዬራ ሌዎን ሄድኩኝና
  • 15:50 - 15:53
    በምሽቱ መኪና የሚነዳ ቄስ ነበር
  • 15:53 - 15:55
    መንደሩ ውስጥ ገቡ።
  • 15:55 - 15:58
    ተመልሰው ወጡና እንዲህ አለን፥ "እንዴት ነው ነገሩ?
  • 15:58 - 16:00
    እነዚህ አዝውንቶች...
  • 16:00 - 16:03
    አያቶች?" ቄሱ ማመን አልቻሉም ነበር ።
  • 16:03 - 16:06
    ከዛም የት ሄዱ? ህንድ ሃገር ሄደው ተመለሱ ።
  • 16:06 - 16:08
    ቀጥታ ፕሬዝዳንቱ ጋር ሄዱ ።
  • 16:08 - 16:10
    እንዲህ አለው፥ "ስዬራ ሌዎን ውስጥ በፀሃይ ሃይል የሚሰሩ መብራቶች እንዳሉ ታቃለህ?"
  • 16:10 - 16:13
    "አይ" አለ ። በንግታው ግማሹ የ ካብኔው አባላቶቹ አያቶቹን ለማየት ሄዱ ።
  • 16:13 - 16:15
    "እንዴት ነው ነገሩ?"
  • 16:15 - 16:19
    አስጠራኝና እንዲህ ብሎ ጠየቀኝ ፥ "150 አያቶች ልታሰለጥንልኝ ትችላለህ?"
  • 16:19 - 16:21
    እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩኝ ፥ "አልችልም አቶ ፕሬዝዳንት ።"
  • 16:21 - 16:23
    እነሱ ግን ይችላሉ። አያቶቹ ራሳቸው ።"
  • 16:23 - 16:26
    ስዬራ ሌዎን ውስጥ የመጀመሪያውን ቤርፊት ኮሌጅ ከፈተልኝ ።
  • 16:26 - 16:30
    150 አዛውንቶች ሰልጥነዋል እዚህ ኮሌጅ ውስጥ ።
  • 16:30 - 16:32
    ጋምቢያ ፥
  • 16:32 - 16:35
    ጋምቢያ ሄደን አያቶችን ለመምረጥ።
  • 16:35 - 16:37
    መንደር ውስጥ ሄድን
  • 16:37 - 16:39
    የምፈልገውን አዛውንቶች የቶቹ እንደሆኑ አውቅ ነበር።
  • 16:39 - 16:42
    ማኅበረሰቡ ግን ሌላዎችን አያቶችን መርጠው ነበር፥ "እነዚህ" አሉኝ ።
  • 16:42 - 16:44
    "አይ እነዚህን ነው ምፈልገው" አልኳቸው።
  • 16:44 - 16:46
    "ለምን" አሉኝ "ቋንቋ አትችልም ይቺ ፣ አታውቃትም"
  • 16:46 - 16:49
    እኔም እንዲህ አልኩኝ ፥ "አኳሗኗን ወድጄዋለው ። አወራርዋን ወድጄዋለው ።"
  • 16:49 - 16:51
    "አይሆንም። ባለቤቷ አስቸጋሪ ነው።"
  • 16:51 - 16:53
    ባለቤቷን አስጠራሁት ። መጣ ።
  • 16:53 - 16:56
    ፖለቲካ ውስጥ የታወቀ ሰውዬ ነበር "አይሆንም" አለ።
  • 16:56 - 16:59
    "ለምን?" አልኩት ። "እንዴአት እንደምታምር እይ እስቲ"
  • 16:59 - 17:01
    "አዎን" አልኩት፣ "በጣም ታምራለች ።"
  • 17:01 - 17:03
    " ከ አንዱ ህንድ ጋር ብትጠፋስ?"
  • 17:03 - 17:05
    ይሄንን ነበር ከሁሉ የሚፋራው።
  • 17:05 - 17:08
    እንዲህ አልኩት፥ "ደስ ነው ሚላት፤ ሞባይልህ ላይ ትደውልልሃለች።"
  • 17:08 - 17:11
    አያት የነበረችዋ ሴትዮ
  • 17:11 - 17:13
    ነብር ሆና ተመለሰች።
  • 17:13 - 17:15
    ከ አውሮፕላን ውስጥ ወታ
  • 17:15 - 17:18
    ጋዘጠኛ ፊት ሁሉ ንግግር አደረገች ልክ ልምድ እንዳለው ሰው ።
  • 17:18 - 17:21
    ለ ሀገራዊው ጋዘጠኛ በስነስረዓት መለሰች ና
  • 17:21 - 17:23
    ታዋቂ ኮኮብ ሆነች።
  • 17:23 - 17:26
    ከ 6 ወር በኋላ ሄጄ ሳገኛት ፥ "ባለበቤትሽ የት አለ?" ብዬ ስጠይቃት ፣
  • 17:26 - 17:28
    "እኔንጃ አንዱ ጋር ፣ ግድ የለም።"
  • 17:28 - 17:30
    (ሣቅታ)
  • 17:30 - 17:32
    ይሄ ነው የተሳካ ሂወት ማለት ።
  • 17:32 - 17:34
    (ሣቅታ)
  • 17:34 - 17:37
    (ጭብጨባ)
  • 17:37 - 17:43
    እንዲህ ብዬ ልጨርስ ፥
  • 17:43 - 17:47
    መፍትሄ ውጭ አይደለም የሚገኘው ።
  • 17:47 - 17:49
    ከውስጥ ፈልጉት ።
  • 17:49 - 17:52
    ሰውን አዳምጡ ። መፍትሄውን ይሰጧቿል ።
  • 17:52 - 17:54
    ዓለም ውስጥ ሁሉ አሉ ።
  • 17:54 - 17:56
    አትጨነቁ ።
  • 17:56 - 17:59
    ውርልድ ባንክን (World Bank) አታዳምጡ ፤ ካጠገባቹ ያሉትን ሰዎች አዳምጡ ።
  • 17:59 - 18:02
    የዓለም መፍትሄ በእጃቸው ውስጥ ነው ።
  • 18:02 - 18:05
    ማህትማ ጋንዲን ጠቅሼ ልጨርስ ፥
  • 18:05 - 18:07
    "በመጀመሪያ ይገልሏቿል ፤
  • 18:07 - 18:09
    ከዛም ይስቁባቿል፤
  • 18:09 - 18:11
    ከዛም ይዋጏቿል ፤
  • 18:11 - 18:13
    በመጨረሻም ታሸንፋላቹ ።"
  • 18:13 - 18:15
    አመሰግናለሁ ።
  • 18:15 - 18:46
    (ጭብጨባ)
Title:
ባንከር ሮይ: ከቤርፉት እንቅስቃሴ እንማር
Speaker:
Bunker Roy
Description:

ራጃስትሃን፣ህንድ ሀገር ፥ ምርጥ ትምህርት ቤት አለ ። ማንበብ የማይችሉትን የገጠር ሴቶችንና ወንዶችን የሚያሰለጥን ። በመንደራቸው ውስጥ የፀሀይ ሃይል መሃንዲስ፤ የስነ ጥበብ ሰው፤ የጥርስ ሐኪም እንዲሆኑ የሚየርግ ። ቤርፉት ኮሌጅ (Barefoot College) ይባላል ። መሥራቹ ባንከር ሮይ (Bunker Roy) እንዴት እንደሚሰራ ያስረዳናል።

more » « less
Video Language:
English
Team:
closed TED
Project:
TEDTalks
Duration:
18:47

Amharic subtitles

Revisions