ወደ ሌላ ዓለም ልወስዳቹ እፈልጋለው ። ማካፈል መፈለገው ነገርም አለ ። እሱም የ45 ዓመት የ ፍቅር ታሪክነው ። ከድህነት ጋር ያለ ፍቅር በ ቀን ከ 1 ዶላር በታች መኖር ። የተማርኩት ከዲታ ጋር ነው የህንድ ሀገር ሃብታም ትመሀርት ቤት ነገር ገን ያ ሊገለኝ ነበር ። ሁሉ ነገር ተዘጋጅቶልኝ ነበር ። ዲፕሎማት፣ መምህር፣ሐኪም ለመሆን ። ሁሉ ነገር ተስተካክሎልኝ ነበር ። ከሱም ጭምር፤ አይመስልም አንጂ የ ህንድ ሃገር ናሽናል ቻምፒዮን ነበርኩኝ ለ 3 ዓመት ። (ሣቅታ) ዓለም ባጠቃላይ ተሰታኝ ነብር ። ሁሉ ነገር በእጄ ውስጥ ነበር ። ምንምን ቢሆን ልበላሽ ኣልችልም ። ነገር ግን የሆነ ጉጉት ያዘኝ አስቲ ሄጄ ገጠር መስራት ልሞክር አዛ መኖር ምን አንደሚመስል እስቲ ሊየው ። ስለዚህ በ 1965 (አ/አ) ህንድ ውስጥ የነበረው ሃይለኛው የቢሀርን ቸነፈር ለማይት ሄድኩኝ ። ረሀብና ሞትን አየው ። ለመጀመሪያ ግዜ ሰው በረሀብ ሲሞት አየው ። ሂወቴን ቀየረው ። ቤት ተመልሼ አናቴን ገጠር ኖሬ መስራት ፈልጋለው ኣልኳት ። አናቴ ኮማ ውስጥ ገባች ። (ሣቅታ) ምን ማለት ነው ይሄ? ዓለም ሁሉ በእጅህ ነው ያለው፣ የፈለከውን ስራ መስራት ትችላለህ፣ ያ ሁሉ አያለህ ገጠር ልስራ ትላለህ አንዴ? ትንሽ አሞሃል አንዴ? አንዲ ብዬ መለስኩላት፥ "ኣይ፦ ምርጥ ትመህርት አለኝ አሳሰበኝና የደረሰኝን እድል መመለስ ፈልጋለው በራሴ መንገድ ።" "ገጠር ምን ልታረግ ነው? ስራ የለ፣ ገንዘብ የለ... ማረጋገጫ የለ፣ ፍንኦት የለ ።" አኔም አንዲህ አልኳት ፥ "መኖር ፈልጋለው ለ 5 ዓመት መቆፈር ፈልጋለው ።" "ለ 5 ዓመት መቆፈር ፈልጋለው?" አለች:: "ህንድ ውስጥ ካሉት ውድ ትምሀርት ቤትና ኮሌጅ ተመረሀ ለ 5 ዓመት መቆፈር ፈልጋለው ትላለህ?" ለ ብዙ ጊዜ ኣላናገረቺኝም:: ምክንያቱም ቤተሰቤን ቅር ያሰኘው ነው የመሰላት:: ነገር ገን ልዩ እውቀትና ሞያ ተማርኩኝ እጅግ በጣም ደሃ የሆኑ ሰዎች የሚያውቁት እድባዊ ትምህርት መቼም የማይሆን መቼም ያልተ ከበረ፣ ስም ያለተሰጠው ውይም በትልቁ ያልታየ ። ያኔ ነው ቤርፉት (Barefoot) ኮሌጅን ልጀምር ያልኩት የድሃ ብቻ ኮሌጅ ። የ ድሃ ሐሳብ የሚከበርበት ኮሌጅ እንዲሆን ። ለመጀመሪያ ግዜ የ ገጠር መንደር ውስጥ ሄድኩ ። አዛውንቶች ወደኔ መተው፤ "ከ ፖሊስ እያመለጥክ ነው?" አሉኝ። "አይደለም" አልኩኝ (ሣቅታ) "ፈተና ወደክ?" ብለው ጠየቁኝ "አይደለም" አልኩኝ "የመንግስት ስራ አጣህ?" አሁንም ፥ አይደለም፣ አልኩኝ " እዚህ ምንታረጋለህ ታድያ ለምን መጣህ? የህንድ ሃገር ትምህርት ወደ ፓሪስ፣ ኒው ዴሊህና ዙሪክ ነው ሊወስድህ የሚገባው እዚህ ባላገር ውስጥ ምን ትሰራለህ? የደበከን ነገር ኣለ አንዴ?" "ኣይ ፤ ኮሌጅ መክፈት ነው ምፈልገው ለ ድሃ ብቻ የሚሆን ኮሌጅ ። የድሃ ሐሳብ የሚከበርበትና የሚገለጽበት ።" አዛውንቶቹም ይሄን ሰምተው ትልቅ መክር ሰጡኝ አንዲህ ኣሉኝ፥ "እባክህን... ዲግሪና ዲፕሎማ ያለውን ሰው እንዳታመጣብን እዚህ ኮሌጅ ውስጥ ።" ስለዚህ ይሄ ኮሌጅ ብቻ ነው ህንድ ውስጥ ዶክቶሬት ወይም ማስትሬት ካላቹ ማይቀበላቹ ። ያልተሳካላቹ፣ ያልተሟላላቹ፣ ወይም ከትምህርት ቤት ያቇረጣቹ መሆን አለባቹህ ኮሌጅ ውስጥ ለመግባት ። የእጅ ስራ ማወቅ እለባቹ ። የስራ ክብር እንዲኖራች ያስፈለጋል ። ለማኅበረሰቡ ጥበብ እንዳላቹ ማሳየት አለባቹ አናም ለዚህ ማኅበረሰብ አገልግሎት ማሳየት ይገባቿል ። ስለዚህ ቤርፉት ኮሌጅን ከፈትን ሞያን ኣዲስ ስም ሰጠነው ። ማነው ባለሞያ? ባለሞያ ሰው ማለት ችሎታ ያለውና በራሱ የሚተማን ነው ። ውሃ ኣስገኚ (water diviner) ባለሞያ ነው ። ባህላዊ አዋላጅ ፤ ባለሞያ ናት ። ባህላዊ ወጌሻ ባለሞያ ነው ። እነዚህ ዓለም ውስጥ ባጠቃላይ ባለሞያ ናቸው ። የትም ገጠር ውስጥ ልታገኟቸው ትችላላቹ ። ስለዚህ አነዚህ ሰዎች ወደ መደበኛ ሂወት መምጣት ይገባቿል ብለን አሰብን ያላቸው እውቀትና ሞያ አቀፋዊ ነው ። መጠቀም አለበት፣ ተግባር ላይ መዋል አለበት ። ዓለም ሁሉ ማወቅ አለበት እነዚህ እውቀቶችና ሞያዎች አግባብ እንዳላቸው ዛሬ ። ስለዚህ ኮሌጁ የ ማሕትማ ጋንዲን አኗኗርና አሰራርን የሚከተል ነው ። መሬት ላይ ትበላለህ፣ መሬት ላይ ትተኛለህ፣ መሬት ላይ ትሰራለህ ። ውል (contract) ኣይጻፍም ። ለ 20 ዓመት መቅረት ትችላልለህ ውይም ነገ መሄድ ትችላልለህ ። ደሞም፣ ማንም ከ100 ዶላር በላይ አያገኝም በውር ። ለገንዘብ ከመጣህ ቤርፉት ኮሌጅ ላንተ አይደለም ። ለስራና ለፍልምያ ነው ምትመጠው ያኔ ቤርፉት ኮሌጅ ላንት ነው ። ታድያ የፈለጋቹትን ሐሳብ ማቅረብ ትችላላቹ እዚህ ። ማንኛውም ሐሳብ ሲኖራቹ መታቹ ሞክሩት ። ባይሳካ ምንም ኣይደለም ። ወድቃቹ ፣ ቆስላቹ ፣ ድጋሚ መሞከር ነው ። አስተማሪ ተማሪ የሆነበትና ተማሪ አስተማሪ የሆነበት ኮሌጅ ይሄ ብቻ ነው ። ደሞም፣ ይሄ ኮሌጅ ብቻ ነው ሰርቲፊኬት የማይሰጥበት ። ባገለገልከው መሐበር ውስጥ ነው ምስጋና የሚደርስህ ። መሃንዲስ መሆንህን የሚያሳውቅ ግድግዳ ላይ ወረቀት መስቀል አያስፈለግህም ። አንደዛ ስላቸው "እንደሱ ከሆነ አስቲ ኣሳየን እንደሚቻል? በለው ጠየቁኝ ። ወሬ ብቻ ምን ያረጋል ተግባር ካልታየ?" አሉኝ ። ስለዚህ የመጀመሪያውን ቤርፉት ኮሌጅን ገነባን። በ 1986 (አ/አ) ሁለት ባዶ እግራቸው የሆኑ የህንፃ ነዳፊዎች ናቸው የገነቡት ማንበብና መጻፍ የማይችሉ በ ሜትር ካሬ 0.13 ሳንቲም ብቻ (ዶላር) 150 ሰዎች እዛ ይኖሩ ነበር፤ ይሰሩ ነበር ። በ 2002 (አ/አ) የ ህንፃ ነዳፊ ኣጋ ካን (Aga Khan) ሽልማትን ተሸለሙ ። ነገር ግን ሌላ የእውነተኛ የህንፃ ነዳፊ ነው የሰራው ብለው ጠረጠሩ ። "አዎ ፕላኑን ሰርተዋል" ፤ አልኳቸው "ግን፤ የቤርፉት ህንፃ ነዳፊዎች ናቸው ኮሌጁን የገነቡት ።" የ 50 000 ዶላር ሽልማቱን አስመለሱን ፣ ለመጀመሪያ ግዜ በአጋካን ታሪክ ስላላመኑን ይሄ ታድያ በ ቲሎኒያ የህንፃ ነዳፊዎች ጎጂ ትችት የደረሰባቸው መስሎን ነበር ። የ ጫቃ ኣዋቂ ጠየኩኝ ታዋቂ ዲፕሎማ ያለውና ባለሙያ የተባለው እንዲህ ኣልኩት፥ "እዚህ መሬት ላይ መን መገንባት ትችላለህ?" አየት አረገውና፥ "ባክህ ተስፋ የለውም፣ ምንም ኣይሰራም አዚህ ላይ መሞከርም አያስፈልግም" ብሎ መለሰልኝ ። "ውሃ የለው ፤ መሬቱ ድንጋያማ" እንዲህ ሲለኝ ገረመኝ ። እሺ፣ እንግዲያውስ ገጠር ሄጄ አንዱን ሽማግሌ ልጠይቀው፥ "እዚህ መሬት ላይ መን ምን ልዝራ?" ፀጥ ብሎ ኣየኝና እንዲህ አለኝ፥ "ይሄንን፤ ያንን፤ ይሄንን፤ ስራና ሁሉም ይሳካል ።" ዛሬ ይሄንን ይመስላል ። ጣራ ላይ ስወጣ ሴቶቹ፥ "ዞር በል!" አሉኝ ። "ወንዶ ሁሉ ይሂዱልን ከዚህ፣ ይሄን ሙያ ማሳየት አንፈልግም ። ይሄ ጣራዉ ውስጥ ውሃ እንዳይገ የሚደረግ ስልት ነው ። (ሣቅታ) የሆነ ስኳር መሳይ ማጣበቂያ፤ የሆነ ዕንጨት ... ምናምን ሌላም ነገሮች ነበሪት ...ብቻ እኔጃ ። ግን ምንም ውሃ አያሳልፍም ። ከ1986 (አ/አ) አስካሁን ድርስ አንድም ውሃ ጠብ አላለም ። ይሄንን ሙያ ሴቶቹ ከወንዶቹ ጋር ማካፈል አልፈለጉም ። (ሣቅታ) በዓለም ላይ ያኛ ኮሌጅ ብቻ ነው በ ፀሐይ ኀይል ኤሌክትሪኩ የሚሰራው ። ሁልም ሃይሉ ከ ፀሐይ ነው የሚመጣው ። 45 ኪሎዋት አለ ጣራው ላይ ። ሁሉ ነገር በደንብ ነው የሰራው ለ 25 ዓመት ። ፀሐይ እስካለች ምንም የኤሌክትሪት ችግር ኣይኖረንም ። ከሁሉም ደስ የሞለው ግን ይሄ የፀሐይ ሃልይ የተሰራው በ አንድ ቄስ ነው ፤ ሂንዱ ቄስ የመጀመሪያ ደረጃ ብቻ ትምህርት የተማረ ሰው ሌላም ኣልተማረም ኮሌጅም አልሄደም ። ስለ ፀሐይ ሃይል ከማውቀው ሰው ሁሉ በላይ ያውቃል ። ለምሳሌ ቤርፉት ኮሌጅ ከመጣቹ ምግብ የሚሰራው በ ፀሐይ ሃይል ነው ። ይ ሄንን የፀሐይን ማብሰያ የሰሩት ሴቶች ናቸው ያልትመሩ ሴቶች፣ ይሄንን የረቀቀ በ ፀሐይ ሃይል የሚሰራ ማብሰያ የፈጠሩት ። የ Scheffler የፀሐይ ሥነ መላ ማብሰያ ነው ። በሚያሳዝን ሁኔታ ግማሽ ጀርመን ናቸው በጣም በትክክሉ ከመሰራታቸው የተነሳ ። (ሣቅታ) እንደነዚህ ያሉ ጠንቃቃ የህንድ ሴቶች የትም አታገኙም ። አስከመጨረሻው ድረስ ይሄንን ማብሰያ በትክክል አርገው የሰሩታል ። በቀን ሁለቴ 60 ምግብ እናቀርባለን በዚህ የፀሐይ ማብሰያ ። የጥርስ ሐኪም አለን ፤ አያት ናቸው፣ ያልተማሩ፣ የጥርስ ሐኪም ። የ 7000 ልጅ ጥርስ ያክማሉ ። የቤርፉት ሥነ መላ ፥ በ1986 (አ/አ)፥ መሐንዲስ የለ፤ የህንፃ ነዳፊ የለ፤ ነገር ግን ከጣራላይ የዝናብ ውሃ እያጠራቀምን ። በጣም ትንሽ ውሃ ነው የምናባክነው ። ጣራዎቻችን በሞላ መሬት ስር ካሉት የ 400 ሺህ ሊትር ታንኮች የተገናኙ ናቸው ምንም ውሃ ኣይባክንም ። የ4 ዓመት ድርቅ ቢመጣ በቂ ውሃ አለን ለዛ ሁሉ ግዜ ምክንያቱም የዝናብ ውሃ እናጠራቅማለን ። 60 % ልጆች ትምህርት ቤት ኣይሄዱም ምክንያቱም እረኛ ናቸው ፥ በግ፣ ፍየል ይጠባሉ ። ውይም የቤት ዕለታዊ ሥራ መስራት ይኖርባችዋል ። ስለዚህ የማት ትምህርትቤት ለመስራት አቀድን ለልጆቹ ። ምክንያቱም ይሄ የማታ ቲሎንያ (Tilonia) ትምህርትቤት ውስጥ 75,000 ልጆች ተምረውበታል ። ለልጆቹ ምቾት እንጂ ፤ ለ አስተማሪዎች ምቾት አይደለም ። ታድያ ምንድነው የምናስተምረው? ዴሞክራሲ ፤ ዜግነት ፤ መሬት አንዴት እንደሚለካ ፤ በፖሊስ ከተያዙ ምን ማረግ እንዳለባቸው ፤ ከብቶቻቸው ከታመሙ ምን ማረግ እንዳለባቸው ። ይሄንን ነው ምናስተምረው ያማታ ትምህርቤታችን ውስጥ ። ትምህርትቤቶቹ ሁሉ ከፀሐይ በመጣው ሃይል የበሩ ናቸው ። በየ 5 ዓመቱ ምርጫ እናካሄዳለን ። ከ 6 አስከ 14 ዓመት ያሉ ልጆች በዴሞክራሲ በተካሄደ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይመርጣሉ ። ያሁንዋ ጠቅላይ ሚኒስቴር 12 ዓመትዋ ነው ። ቀን ላይ 20 ፍየሎችን ትጠብቃለች ፣ ማታ ላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነች ። የመንግስት ካብኔ አላት ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ፣ የ መብራት ኃይል ሚኒስቴር ፣ የጤና ሚኒስቴር ። 150 ትምህርት ቤትና 7000 ልጆችን ይቆጣጠራሉ ። የዛሬ 5 ዓመት የዓለምን የልጆች ሽልማትን ተሸለመች ። ከዛም ስዊድን ሀገር ተጋበዘች ። ለመጀመሪያ ግዜ ከመንደርው ወጣች ። ስዊድንን አይታ አታውቅም ነበር ። ነገሮች ምንም አልደነቋትም ነበር ። የስዊድን ንግስት ስትተዋወቃት እንዲህ ብላ ጠየቀችኝ፥ "ልብዋ እንዲህ የሞላው እንዴት ሆኖ ነው? ብለህ ጠይቅልኝ" አልቺኝ ። "12 ዓመትዋ ብቻ ነው ፣ ና ምንም ነገር የደነቃት ወይም ያስፈራት ኣይመስልም ።" በስተግራዋ ቆማ የነበረችው ልጅትዋም የንግስትዋን ዓይን በደንብ እያየች እንዲህ አለቻት፥ "እባኮን ጠቅላይ ምንስቴር ነኝ ብለው ይንገሩልኝ ።" (ሣቅታ) (ጭብጨባ) ማንበብ ለማይችሉ በአሻንጉሊት እናስተምራለን ። ምንነጋገረው በአሻንጉሊት ነው ። ለምሳሌ ፣ ጆኪም ቻቻ አለ እድሜው 300 ዓመት ነው ። የአእምሮ ሀኪሜ ነው ፣ አስተማሪኤ ነው ። ሀኪሜ ነው ፣ጠበቃኤ ነው ። ለጋሼ ነው ። ገንዘብ ሁሉ ይሰበስብልናል ንትርክ ይፈታልናል ፣ መንደራችን ውስጥ ያለውን ችግር ሁሉ ይፈታልናል ። ጥላቻ ከተፈጠረ መንደራችን ውስጥ ፤ ተማሪዎች ትምህርት ቤት መምጣት ከቀነሱ ፤ አስተማሪውችና ቤተሰቦች ካልተስማሙ ፤ አሻንጉሊቱ ሁሉንም ኣስተማሪና ቤተሰብን ጠርቶ ተጨባበጡ ፣ ተማሪዎቻችን መማር መቀጠል አለባቸው ፣ ይላችዋል ። እነዚህ አሻንጉሊቶች በ ውርልድ ባንክ ትርፍራፊ ወረቀቶች የተሰሩ ናቸው ። (ሣቅታ) (ጭብጨባ) ይሄ ከባድና የማይቻል የመሰለ የ ፀሐይ ሥነ መላ ፥ በየመንደሩ አለ ። ህንድ ሀገርን በሞላ አድርሰናል ከ ላዳክ (Ladakh) እስከ ቡታን (Bhutan) መንደሮቹ ሁሉ በ ፀሐይ ሃይል በርተዋል እድሜ ለ ተማሪዎቻችን ስልጠና ። ላዳክ ሄድንና አንድዋን ሴትዮ እንዲህ ብለን ጠየቅናት ፥ በነገራችን ላይ ፣ ቅዝቃዜው -40 ፣ነገር ግን ደጅ መውጣት ነበረብን ምክንያቱም በረዶ በየበኩሉ ነበር ፣ ሴትያዋን እንዲህ ብለን ጠየቅናት ፥ "ምን ጠቀማቹ ይሄ የ ፀሐይ ሃይል ኤለክትሪክ በመኖሩ?" ለ አንድ ደቂቃ አሰበችና እንዲህ አለች፥ ለመጀመርያ ግዜ በክረምት ወቅት የባለቤቴን ፊት ማየት ቻልኩኝ። (ሣቅታ) አፍጋኒስታንም ሄድን ። ከህንድ የተማርነው አንድ ነገር ፤ ወንዶች ምንም አይሰለጥኑም ። (ሣቅታ) ወንዶች አርፈው መቀመጥ አይችሉም ፤ ወንዶች ታታሪ ናቸው ፤ ወንዶች ብዙ መነቃነቅ ይወዳሉ ፤ ደግሞም ሁሉም ሰርተፊኬት ይፈልጋሉ ። (ሣቅታ) የዓለም ወንዶች ሁሉ ያቺን ሰረተፊኬት የፈልጓታል ። ለምን? ምክንያቱም ከገጠር መውጣት ይፈለጋሉ ወደ ከታማ ሰራ መፈለግ ይሻላችዋል ። ስለዚህ ጥሩ መፍትሄ አቀረብን ፥ የሴት አያቶችን ማሰልጠን ። ዘንድሮ ዓለም ላይ ዋና የወሬ ማሰራጫ ምንድን ነው? ቴሌቪዥን? አይደለም ቴሌግራፍ? አይደለም ስልክ? አይደለም ለሴት ማናገር ። (ሣቅታ) (ጭብጨባ) እንድግዲህ፣ ለመጀመሪያ ግዜ አፍጋኒስታን ሄድን 3 ሴቶችን ለመውሰድ ተዘጋጀን እንዲም አልን፥ "ህንድ ሀገር ልንወስዳቸው እንፈለጋለን ።" "በተዓምር አይሆንም፣ ከቤታቸውም አይወጡም ፣ እንኯን ህንድ ሊሄዱ ።" እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩላቸው "ባለቤቶቻቸውንም እንወስዳለን" ። ስለዚህ፣ ባለቤቶቻቸውም መጡ ። በእርግጥ ሰቶቹ ከወንዶቹ ይበልጥ ብልህ ነበሩ ። በ 6 ወር ውስጥ እንዴት ነው ሴቶቹን የምናሰለጥነው? በምልክት መነጋገር ። ፅሁፍን አለመጠቀም ። ንግግርን አለመጠቀም ። የምልክት ቋንቋ ብቻ ። በ 6 ወር ውስጥ የ ፀሐይ ኀይል መሃንዲስ ይሆናሉ ። ሀገራቸው ገብተው የ ፀሐይ ኀይል ኤሌክትሪክን ያስገባሉ ። ይቺህ ሴትዮ ሄዳ የመጀመሪየውን መንደር በፀሐይ ኀይል አበራችው ፣ (ስልጠና አዘጋጅታ) በ አፍጋኒስታን ውስጥ የመጀመሪየው መንደር በ ፀሐይ ኀይል የሰራው ዕድሜ ለነዚህ 3 ሴቶች ነው :: ይቺህ ሴትዮ ልዩ አያት ናት ። በ 55 ዓመቷ 200 ቤቶችን አፍጋኒስታን ውስጥ በ ፀሐይ ኀይል አብርታለች ። እስካሁን ምንም አልተበላሹም ። እንደውም የአፍጋኒስታን ምሕንድስና መምሪያ ሄዳ ንግ ግር አርጋለች ዋናውን ኀላፊ የACና የDCን ልዮነት አስተማረችው ። አያቅም ነበረ ። እነዚ 3 ሴቶች ሌላ 27 ሴቶችን አሰልጥነዋል ። 100 መንደሮችን በ ፀሐይ ኀይል አብርተዋል ። አፍሪካ ሄድን ፣ አንዳይነት ነገር አደረግን ። ከ 8 ፣ 9 የተልየያዩ ሀገሮች የመጡ ሴቶች ቁጭ በለው ነበር ። ሁሉም የተለያዪ ቋንቋ ስለሚናገሩ አይግባቡም ነበር ግን እንደምንም ይነጋገሩ ነበር ። የምልክት ንግግራቸው ይበቃቸው ነበር ለመግባባት ። ዕርስ በዕርስ እየተነጋገሩ ፣ የ ፀሐይ ኀይል መሃንዲስ ሆነዋል ። ስዬራ ሌዎን ሄድኩኝና በምሽቱ መኪና የሚነዳ ቄስ ነበር መንደሩ ውስጥ ገቡ። ተመልሰው ወጡና እንዲህ አለን፥ "እንዴት ነው ነገሩ? እነዚህ አዝውንቶች... አያቶች?" ቄሱ ማመን አልቻሉም ነበር ። ከዛም የት ሄዱ? ህንድ ሃገር ሄደው ተመለሱ ። ቀጥታ ፕሬዝዳንቱ ጋር ሄዱ ። እንዲህ አለው፥ "ስዬራ ሌዎን ውስጥ በፀሃይ ሃይል የሚሰሩ መብራቶች እንዳሉ ታቃለህ?" "አይ" አለ ። በንግታው ግማሹ የ ካብኔው አባላቶቹ አያቶቹን ለማየት ሄዱ ። "እንዴት ነው ነገሩ?" አስጠራኝና እንዲህ ብሎ ጠየቀኝ ፥ "150 አያቶች ልታሰለጥንልኝ ትችላለህ?" እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩኝ ፥ "አልችልም አቶ ፕሬዝዳንት ።" እነሱ ግን ይችላሉ። አያቶቹ ራሳቸው ።" ስዬራ ሌዎን ውስጥ የመጀመሪያውን ቤርፊት ኮሌጅ ከፈተልኝ ። 150 አዛውንቶች ሰልጥነዋል እዚህ ኮሌጅ ውስጥ ። ጋምቢያ ፥ ጋምቢያ ሄደን አያቶችን ለመምረጥ። መንደር ውስጥ ሄድን የምፈልገውን አዛውንቶች የቶቹ እንደሆኑ አውቅ ነበር። ማኅበረሰቡ ግን ሌላዎችን አያቶችን መርጠው ነበር፥ "እነዚህ" አሉኝ ። "አይ እነዚህን ነው ምፈልገው" አልኳቸው። "ለምን" አሉኝ "ቋንቋ አትችልም ይቺ ፣ አታውቃትም" እኔም እንዲህ አልኩኝ ፥ "አኳሗኗን ወድጄዋለው ። አወራርዋን ወድጄዋለው ።" "አይሆንም። ባለቤቷ አስቸጋሪ ነው።" ባለቤቷን አስጠራሁት ። መጣ ። ፖለቲካ ውስጥ የታወቀ ሰውዬ ነበር "አይሆንም" አለ። "ለምን?" አልኩት ። "እንዴአት እንደምታምር እይ እስቲ" "አዎን" አልኩት፣ "በጣም ታምራለች ።" " ከ አንዱ ህንድ ጋር ብትጠፋስ?" ይሄንን ነበር ከሁሉ የሚፋራው። እንዲህ አልኩት፥ "ደስ ነው ሚላት፤ ሞባይልህ ላይ ትደውልልሃለች።" አያት የነበረችዋ ሴትዮ ነብር ሆና ተመለሰች። ከ አውሮፕላን ውስጥ ወታ ጋዘጠኛ ፊት ሁሉ ንግግር አደረገች ልክ ልምድ እንዳለው ሰው ። ለ ሀገራዊው ጋዘጠኛ በስነስረዓት መለሰች ና ታዋቂ ኮኮብ ሆነች። ከ 6 ወር በኋላ ሄጄ ሳገኛት ፥ "ባለበቤትሽ የት አለ?" ብዬ ስጠይቃት ፣ "እኔንጃ አንዱ ጋር ፣ ግድ የለም።" (ሣቅታ) ይሄ ነው የተሳካ ሂወት ማለት ። (ሣቅታ) (ጭብጨባ) እንዲህ ብዬ ልጨርስ ፥ መፍትሄ ውጭ አይደለም የሚገኘው ። ከውስጥ ፈልጉት ። ሰውን አዳምጡ ። መፍትሄውን ይሰጧቿል ። ዓለም ውስጥ ሁሉ አሉ ። አትጨነቁ ። ውርልድ ባንክን (World Bank) አታዳምጡ ፤ ካጠገባቹ ያሉትን ሰዎች አዳምጡ ። የዓለም መፍትሄ በእጃቸው ውስጥ ነው ። ማህትማ ጋንዲን ጠቅሼ ልጨርስ ፥ "በመጀመሪያ ይገልሏቿል ፤ ከዛም ይስቁባቿል፤ ከዛም ይዋጏቿል ፤ በመጨረሻም ታሸንፋላቹ ።" አመሰግናለሁ ። (ጭብጨባ)