< Return to Video

ዘላቂ ፍቅር ምን ያመስላል

  • 0:01 - 0:05
    አስር አመት አካባቢ ይሆናል ከቴክሳስ ከአንድ ሴት የስልክ ጥሪ ደረሰኝ
  • 0:05 - 0:06
    እስቴሲ ቤከር
  • 0:06 - 0:10
    የኔን የተወሰኑ ፎቶግራፎችንና የፎቶ አውደራዕይ ተመልክታ ነበር
  • 0:10 - 0:15
    የቤተሰብ አልበም በክፍያ እንድሰራላት ፈልጋ ነበር
  • 0:16 - 0:19
    በጊዜው ከእስቴሲ ጋር አልተገናኘንም ነበር እናም የተሰማኝ ይሄ ነገር
  • 0:19 - 0:23
    የነዳጅ ሀብት አግኝቼ የከበርኩ ነው የመሰለኝ
  • 0:23 - 0:25
    ግን ቆይቶ ነበር ነገሩ የተገለጸልኝ
  • 0:25 - 0:28
    ይሄንን ለማድረግ ስትል ተበድራ ነበር
  • 0:29 - 0:31
    የናት አባቷን ምስል አነሳሁ
  • 0:31 - 0:35
    ግን እስቴሲን ፎቶ ማንሳት ነበር ይበልጥ ያስደሰተኝ
  • 0:35 - 0:37
    በእለቱ ያነሳሁት ምስል
  • 0:37 - 0:40
    ከሰራኋቸው ሁሉ የተሻለው ለመሆን በቃ
  • 0:42 - 0:45
    ይሄን ፎቶ ባነሳሁበት ጊዜ እስቴሲ ጠበቃ ሆና ትሰራ ነበር
  • 0:45 - 0:47
    በቴክሳስ አስተዳደር
  • 0:47 - 0:51
    ብዙም ሳይቆይ ስራዋን በመተው በሜይን የፎቶ ጥበብ ማጥናት ጀመረች
  • 0:51 - 0:54
    እዛ በቆየችበት አጋጣሚ ሳይታሰብ
  • 0:54 - 0:57
    የኒውዬርክ ታየምስ መጽሄት የፎቶ ጥበብ ዳይሬክተር ተዋወቀች
  • 0:57 - 1:00
    በዛም የስራ እድል ቀረበላት
  • 1:00 - 1:03
    ከዛን ጊዜ ጀምሮ አሌክና እኔ
  • 1:03 - 1:05
    በጋራ ብዙ የመጽሄት ፕሮጀክቶችን ሰርተናል
  • 1:05 - 1:07
    እንም ጓደኝሞች ለመሆን በቃን
  • 1:07 - 1:12
    ከጥቂት ወራቶች በፊት ከአሌክ ጋር ስለሚመስጠን አንድ ነገር መነጋገር ጀመርን
  • 1:12 - 1:15
    ጥንዶች እንዴት እንደሚገናኙ ማወቅ የሁልጊዜም ጉጉቴ
  • 1:15 - 1:18
    አሌክን ከባለቤቱ ራሄል ጋር እንዴት እንደተገናኙ ጠይቄው ነበር
  • 1:18 - 1:21
    የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የኳስ ጨዋታ ላይ ነበር
  • 1:21 - 1:24
    እሷ 16 እሱ 15 ነበር
  • 1:24 - 1:26
    ጠየቃት
  • 1:26 - 1:28
    ሮዝ ጸጉሯን ይወድላት ነበር
  • 1:28 - 1:31
    እሺ አለችው ይሄው ነበር
  • 1:31 - 1:35
    በመቀጠል አሌክ ፎቶግራፍ ፕሮጀክት ለመስራት ፍላጎቱን እንዳለው ጠየኩት
  • 1:35 - 1:37
    በዚሁ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን
  • 1:37 - 1:41
    ጉዳዩ ስቦኝ ነበር ግን ይበልጥ ፍላጎቴ የነበረው
  • 1:41 - 1:45
    እስቴሲ ለመጠየቅ ያነሳሳት ነገር ላይ ነበር
  • 1:45 - 1:49
    ምክንያቱም እስቴሲ በጭራሽ ፍቅረኛ ይዛ አይቻት አላውቅም
  • 1:49 - 1:52
    ስለዚህ በዚህ ፕሮጀክት አጋጣሚ ሳስበው
  • 1:52 - 1:54
    የሆነ ሰው ለማግኘት ብትሞክር ጥሩ ይሆናል
  • 1:54 - 1:58
    ሀሳቡ እስቴሲ እስፒድ ዴቲን ማስገባት ነበር
  • 1:58 - 2:03
    ያውም ላስቬጋስ ውስጥ በፍቅረኞች ቀን
  • 2:03 - 2:08
    (ሳቅ) (ጭብጨባ)(ሙዚቃ)
  • 2:08 - 2:14
    በአለም ትልቅ ከሚባለለት የችኮላ "ዴቲንግ" ዝግጅት ላይ ተገኘን
  • 2:14 - 2:16
    19 ወንድ ተዋውቄአለሁ
  • 2:16 - 2:19
    ከእያንዳንዱ ለ3 ደቂቃ ነበር የቆየሁት
  • 2:19 - 2:23
    ሂደቱ እንዲቀጥል ለተሳታፊዎች የሚያዝናኑ ጥያቄዎች ተሰቶ ነበር
  • 2:23 - 2:27
    ለምሳሌ "እንስሳ መሆን ብትችዪ፣ ምን ትሆኒ ነበር?"
  • 2:27 - 2:28
    እንደዚ የመሰለ ጥያቄ ነበር
  • 2:28 - 2:31
    የመጀመሪያው ኮሊን ነበር
  • 2:31 - 2:33
    እንግሊዛዊ ነው
  • 2:33 - 2:38
    ሚስት ነበረችው
  • 2:38 - 2:40
    አሌክና አኔ ማታ ላይ አግኝተነው ነበር
  • 2:40 - 2:45
    ወረፋ መጠበቂያ ላይ አንድ ሴት እንደሳመ ነገሮናል
  • 2:45 - 2:48
    ዛክና ክሪስ አንድ ላይ ነበር የመጡት
  • 2:51 - 2:53
    ይሄ ካርል ነው
  • 2:53 - 2:59
    ካርልን ሴት ስታገኝ መጀመሪያ የሚታይህ ምንድ ነው አልኩት
  • 2:59 - 3:01
    ጡት አለኝ
  • 3:01 - 3:03
    (ሳቅ)
  • 3:05 - 3:09
    ማቲው ጡንቸኛ እግር ያላት ሴት ትማርከዋለች
  • 3:09 - 3:12
    ስለ ሩጫ አውርተን ነበር እሱ ትሪታሎን ይሰራል አኔ ግማሽ ማራቶን ሮጫለሁ
  • 3:12 - 3:17
    አሌክ አይኑ ያምራል ወደድሽው ሲለኝ ነበር ግን እኔ አልሳበኝም
  • 3:17 - 3:20
    እሱም የተመቸሁት አይመስለኝም
  • 3:21 - 3:25
    ኦስቲንና ማይክ አብረው ነበር የመጡት
  • 3:25 - 3:27
    ማይክ መስቀለኛ ጥያቄ አነሳ
  • 3:27 - 3:32
    "ሊፍት ውስጥ ብትሆኚና ለስብሰባ ረፍዶብሽ ቢሆን
  • 3:32 - 3:34
    የሆነ ሰው ወደ ሊፍቱ እየመጣ ምልክት ቢሰጥሽ
  • 3:34 - 3:37
    ሊፍቱን ትይዢለታለሽ?"
  • 3:37 - 3:39
    አላደርገውም አልኩት
  • 3:39 - 3:42
    (ሳቅ)
  • 3:44 - 3:48
    ክሊፍ ከሴት ቀድሜ የማየው ጥርሷን ነው አለ
  • 3:48 - 3:51
    ጥርሳችን ያምራል ስንባባል ነበር
  • 3:51 - 3:53
    አፉን ከፍቶ ስለሆነ የሚተኛው
  • 3:53 - 3:57
    በሽታ እንዳይዘው ጥረሱን ብዙ ጊዜ መቦረሽ እንዳለበት አወራኝ
  • 3:57 - 4:00
    በምን ያህል ጊዜ ትፍቃለህ ስለው
  • 4:00 - 4:02
    በቀን አንዴ አለ
  • 4:02 - 4:04
    (ሳቅ)
  • 4:06 - 4:08
    እንግዲህ እኔ በቀን ሁለቴ ለሚፍቅ ሰው
  • 4:08 - 4:10
    እሱ እንደሚለው መፋቅ የበዛበት አይመስለኝም
  • 4:10 - 4:13
    እንዲህ ብዬ ግን አልነገርኩትም
  • 4:13 - 4:16
    ቢል የኦዲት ባለሙያ ነው
  • 4:16 - 4:21
    ሦስት ደቂቃውን በሙሉ ስለ ኦዲት ስናወራ ነበር (ሳቅ)
  • 4:23 - 4:27
    እስፔንሰር ከሴት ቀድሞ የሚያየው የፊት ማሰማመሪያን ነው
  • 4:27 - 4:29
    ብዙ ሴቶች ሜክአፕ እንደሚያበዙ ነው የሚሰማው
  • 4:29 - 4:33
    በትንሹ ለመታየት ካልሆን በስተቀር ማድረግ የለባቸውም ባይ ነው
  • 4:33 - 4:35
    ምንም ሜክአፕ አለማድረጌን ነገርኩት
  • 4:35 - 4:38
    ሀሳቡ ሳመቸው አይቀርም
  • 4:39 - 4:43
    ክሬግ ስለ እራሴ ግልጽ መሆን የምፈልግ አልመሰለውም
  • 4:43 - 4:48
    በህይወቴ ስለገጠመኝ የሚያሳፍር ነገር ማስታወስ ባለመቻሌ ሲበሳጭ ነበር
  • 4:48 - 4:51
    የዋሸሁት መስሎታል ግን አልዋሸሁም
  • 4:51 - 4:54
    የወደደኝ አይመስለኝም ግን መጨረሻ ላይ
  • 4:54 - 4:57
    ተመልሶ መጥቶ ሙሉ ቸኮሌት ሰጠን
  • 4:58 - 5:01
    ዊልያም ሊያወሩት የሚከብድ ሰው ነው
  • 5:01 - 5:03
    ሳይክር አልቀረም
  • 5:03 - 5:05
    (ሳቅ)
  • 5:06 - 5:09
    ተዋናይ ክሪስ ማኬና በዝግጅቱ ዋና አድማቂ እሱ ነበር
  • 5:09 - 5:11
    ወጣትና እረፍት አልባ የሚል ፊልም ላይ ነበረበት
  • 5:11 - 5:14
    ከእሱ ጋር አልተገናኘሁም
  • 5:14 - 5:18
    አሌክ ነው ብዙ ሴቶች ስልክ ቁጥር ሲሰጡት ያየው
  • 5:19 - 5:24
    ቢሆንም ፍቅር አልያዘኝም
  • 5:24 - 5:28
    ከማናቸውም ጋር የተለየ የተሰማኝ ነገር አልነበረም
  • 5:28 - 5:32
    እነሱም ቢሆኑ ከኔ ጋር የተሰማቸው ነገር ያለ አይመስለኝም
  • 5:33 - 5:36
    ለኔ ከሁሉም ነገር ውብ ሆኖ የሚታየን
  • 5:36 - 5:42
    (ሳቅ)እንደ ፎቶ አንሺነቴ ተጋላጭነት ነው
  • 5:42 - 5:45
    ውጫዊ አካላችን ውስጣችንን በቀዳዳ አሳልፎ ይሰጠናል
  • 5:45 - 5:49
    በተለይ ውስጣችን ያልተረጋጋ ከሆነ
  • 5:49 - 5:52
    በዚህ ዝግጅት ደግሞ ያን የሚመሰክር ብዙ ነገር አይቻለሁ
  • 5:52 - 5:56
    ግን እስቴሲ ያገኘቻቸውን ወንዶች ሳይና ስለእነሱ ሳዋራት
  • 5:56 - 6:03
    የተረዳሁት ነገር ምን ያህል በፎቶ ያለ ፍቅርና እውነተኛ ፍቅር እንደሚለያይ ነው
  • 6:03 - 6:06
    እውነተኛ ፍቅር ምንድን ነው? እንዴት ነው ሚሰራው?
  • 6:06 - 6:11
    ይሄን ጥያቄ ለመመለስና
  • 6:11 - 6:15
    በትውውቅ ተገናኝቶ አብሮ እስከመኖር እንዴት እንደሚደረስ ለመረዳት ስንል
  • 6:15 - 6:18
    እስቴሲና እኔ ወደ ሰን ሲቲ ሰመርሊን አመራን
  • 6:18 - 6:22
    ያው በላስ ቬጋስ ያለ ትልቁ የአዛውንቶች መጦሪያ ስፍራ ነው
  • 6:23 - 6:28
    አገናኛችን ጆርጅ ይባላል የፎቶግራፍ ክበብ መሪ ነው
  • 6:28 - 6:32
    ለፎቶ የተገኙ ጥንዶችን እንድናነጋግር አመቻችቶልን ነበር
  • 6:32 - 6:38
    ከ45 አመታት የትዳር ቆይታ በኋላ የአንስታሲያ ባለቤት ከሞተ ሁለት ሆኖታል
  • 6:38 - 6:41
    የቆየ የሰርግ ፎቶ እንዳላት ጠይቀናት ነበር
  • 6:41 - 6:44
    ባለቤቷን ያገኘቸው በ15 አመቷ በአስተናጋጅነት
  • 6:44 - 6:47
    ከምትሰራበት በሚቺንጋን ከሚገኝ ትንሽ ምግብ ቤት ውስጥ ነበር
  • 6:47 - 6:48
    እሱ 30 ነበር
  • 6:48 - 6:51
    እድሜዋን ዋሽታለች
  • 6:51 - 6:53
    የመጀመሪያዋ ነበር
  • 6:53 - 6:58
    ዲን ለሁለት አመት በተከታታይ በላስ ቬጋስ የአመቱ ምርጥ ፎቶግራፈር በመሆን ተመጧል
  • 6:58 - 7:00
    ይሄ አሌክን ስቦት ነበር
  • 7:00 - 7:02
    ባለቤቱን ጁድ ያገነበት አኳሀን
  • 7:02 - 7:06
    አሌክ ራሄልን ባገኘበት ተመሳሳይ እድሜ ላይ ነበር
  • 7:06 - 7:09
    ዲን በባህሪው ቆንጆ ሴት ማየት እንደሚወድ ቢያምንም
  • 7:09 - 7:13
    ጁድን ለማግባት የመወሰኑን ትክክለኝነት አይጠራጠርም
  • 7:13 - 7:15
    ጆርጅ ጆሴፊንን ዳንስ ላይ ነበር ያገናት
  • 7:15 - 7:18
    እሱ 18 እሷ 15 ነበሩ
  • 7:18 - 7:21
    በብዛት እንዳገኘናቸው ጥንዶች እነሱ
  • 7:21 - 7:23
    ስላለፈ የህይወት ምርጫቸው የሚፈላሰፉ አልነበሩም
  • 7:23 - 7:26
    ጆርጅ ያነኝ ነገር እስካሁን አብሮኝ አለ
  • 7:26 - 7:32
    "ያ ስሜት ሲሰማሽ ዝም ብለሽ ትከተይዋለሽ" ነበር ያለው
  • 7:34 - 7:38
    ቦብና ትሩዲ እሷ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ እያለች ነበር የተገናኙት
  • 7:38 - 7:40
    የመዋደድ ስሜት አልነበራቸውም
  • 7:40 - 7:42
    መጀመሪያ የተገናኙ ጊዜ
  • 7:42 - 7:45
    ይሁን እንጂ ብዙም ሳይቆዩ ተጋብተዋል
  • 7:45 - 7:48
    ከሁሉም ተለይቶ ውስጤ የቀረው
  • 7:48 - 7:52
    የጆርጅ የፎቶ ክበብ ሀላፊው ና የባለቤቱ ሜሪ ታሪክ ነበር
  • 7:52 - 7:56
    ጆርጅ ይሄ ነው የሜሪ ደግሞ ሁለተኛ ትዳር
  • 7:56 - 8:00
    በሎዊስቫይል ኬንተርኪ በሚገኝ ሳሃራ ሚባል አገረሰብ ክለብ ነበር የተገኛኙት
  • 8:00 - 8:04
    እሱ ብቻውን እየጠጣ እሷ ደግሞ ከጓደኘቿ ጋር ነበረች
  • 8:04 - 8:10
    መውጣት የጀመሩ ሰሞን እሱ ቴክሳስ ውስጥ 9ሺ ዶላር የታክስ እዳ ነበረበት
  • 8:10 - 8:12
    ከእዳ እንዲወጣ አግዛዋለች
  • 8:12 - 8:16
    ስለዚህ ለቀጣይ አንድ አመት ደመወዙን ለሜሪ ነበር የሚሰጠው
  • 8:16 - 8:19
    በዚህም ከእዳ ነጻ እንዲሆን አድርጋዋለች
  • 8:19 - 8:23
    በመሰረቱ ሲጋቡም ጀምሮ ጆርጅ የመጠጥ ሱሰኛ ነበር ሜሪ ይሄን ታውቃለች
  • 8:23 - 8:26
    በትዳር ውስጥ እያሉ እሱ እንዳለው
  • 8:26 - 8:30
    በቀን 54 ቢራ የጠጣበት አጋጣሚ ነበር
  • 8:30 - 8:32
    በሌላ ጊዜ በጣም ሰክሮ እሷና
  • 8:32 - 8:34
    በሁለት ልጆቿን ላይ የመግደል ሙከራ አድረጓል
  • 8:34 - 8:38
    ግን አምልጠዋል ልዩ የፖሊስ ሀይል ቤታቸው መቶ ነበር
  • 8:38 - 8:41
    የሚያስደንቀው ይቅር ብላ ታረቀችው
  • 8:41 - 8:43
    ከዛ በኋላ ነገሮች እየተሸሉ መጡ
  • 8:43 - 8:46
    ጆርጅ ከመጠት ሱስ ለመገላገል የምክር አገልግሎት ተካፍሏል
  • 8:46 - 8:49
    እናም ለ36 አመት ያህል መጠጥ ጠጥቶ አያቅም
  • 8:49 - 8:50
    (ሙዚቃ)
  • 8:50 - 8:52
    በስተ መጨረሻ ሰን ሲቲን ለቀን ከወጣን ስንወጣ
  • 8:52 - 8:55
    ለአሌክ የነገርኩት
  • 8:55 - 8:59
    እነዚን ጥንዶች የተገናኙበት ታሪክ አይደለም ቁም ነገሩ
  • 8:59 - 9:01
    ዋናው ነገር
  • 9:01 - 9:05
    እንዴት አብረው መቆየት እንደቻሉ ነው
  • 9:05 - 9:09
    ሁሉም ጋር የሚምር ጽናት አለ
  • 9:09 - 9:11
    ግን ላጤዎቹም ቢሆኑ እንደዛው ናቸው
  • 9:11 - 9:15
    ህይወት ከባድ ነው እነሱ ደግሞ ወተው
  • 9:15 - 9:17
    ሌሎችን ሰዎች ለማግኘት እየታገሉ ነው
  • 9:17 - 9:20
    ጥንዶቹ እጅ ለእጅ እንደተያያዙ ነው
  • 9:20 - 9:22
    ከስነት አስርት አመታት በኋላም ቢሆን
  • 9:24 - 9:27
    በዚህ ጉዞ የወደድኩት ምስል የጆይ እና ሮሴአንን ነው
  • 9:27 - 9:29
    እነሱን ባገኘንበት ሰአት
  • 9:29 - 9:35
    የሰርግ ፎቶ መጠየቅን እንደ ልምድ አድረገነው ነበር
  • 9:35 - 9:40
    የነሱ የሚለየው ሁለቱም በተመሳሳይ ጊዜ ከኪስ ቦርሳቸውን
  • 9:40 - 9:44
    አንድ አይነት ፎቶ ማውጣታቸው ነበር
  • 9:44 - 9:47
    ለራሴ ሳስበው የትኛው ነው ይበልጥ የሚያምረው
  • 9:47 - 9:51
    ምስሉ ላይ ያሉት ሁለት ትኩስ ፍቀር ላይ ያሉ ጥንዶች
  • 9:51 - 9:57
    ወይስ የነዚህ ሁለት ሰዎች ለአመታት ይሀንን ምስል ይዘው የመገኘታቸው ሀሳብ
  • 9:58 - 10:00
    አመሰግናለሁ
  • 10:00 - 10:06
    (ጭብጨባ)
Title:
ዘላቂ ፍቅር ምን ያመስላል
Speaker:
አሌክ ሶዝ + እስቴሲ ቤከር
Description:

እስቴሲ ቤከር ሁሌጊዜም ፍቀረኞችን ለትውውቅ የሚያበቃቸውን አጋጣሚ ታሪክ የማወቅ ጽኑ ፍላጎት ነበራት፡ የፎቶ ግራፍ ባለሙያውን አሌክ ሶዥ ይሄን ታሪክ ለመዳሰስ አንዲረዳት በጠየቀችው ጊዜ እራሷን በአለም ፈጣን ከሚባልለት የፍቅር ትውውቅ መድረክ ላይ አገኘችው ላስ ቬጋስ ውስጥ ያውም በፍቅረኞች ቀን በመቀጠል በኔቫዳ የአረጋውያን ማህበረሰብ በመገኘት ከአሌክ ሶዥ ጋር በመሆን የጥንዶችን ፎቶ መሰብሰብ ያዙ፣ በነዚህ ሁለት ተጻራሪ ውኔታዎች መሀካል በፍቅር ተጣማሪዎች ጥንዶች ከትውውቅ የጋራ ህይወት ወደ መመስረት የሚያሸጋግራቸውን ቁም ነገር አገኙት (ይሄ ንግግር የተዘጋጀው ከፖፕ አፕ መጽሄት ጋር በመተባባር የቴድ 2015 መርሀግብር አካል ሆኖ ነው)

more » « less
Video Language:
English
Team:
closed TED
Project:
TEDTalks
Duration:
10:18

Amharic subtitles

Revisions Compare revisions