የንፋስን ሀይል እንዴት መጠቀም እንደቻልኩ
-
0:00 - 0:03አመሰግናለሁ!
-
0:03 - 0:07ከሁለት አመት በፊት በአሩሻ ታንዛኒያ
በቴድ መድረክ ቆሜ ነበር -
0:07 - 0:12ስለምኮራበት የፈጠራ ስራዬ
ትንሽ ተናግሬ ነበር -
0:12 - 0:16ህይወቴን ስለቀየረ
ቀላል መሳሪ ነበር -
0:16 - 0:18ከዛ በፊት
-
0:18 - 0:21በጭራሽ ከቤቴ ርቄ
አላውቅም ነበር -
0:21 - 0:24ማላዊ ውስጥ
-
0:24 - 0:26ኮምፒውተር በጭራሽ
ተጠቀሜ አላውቅም -
0:26 - 0:30ድህረ ገጽ በጭራሽ
ተመልክቼ አላውቅም -
0:30 - 0:35በእለቱ መድረኩ ላይ
በጣም ፈርቼ ነበር -
0:35 - 0:39እንግሊዘኛ ጠፍቶብ ነበር
-
0:39 - 0:41ማስመለስ ፈልጌ ነበር
-
0:41 - 0:45(ሳቅ)
-
0:45 - 0:49እንደዚህ ያህል የበዙ አዙንጉዎች
ተከብቤ አላውቅም -
0:49 - 0:51ነጮች
-
0:51 - 0:54(ሳቅ)
-
0:54 - 0:57በጊዜው መናግር ያልቻልኩት
ታሪክ ነበር -
0:57 - 1:00ግን አሁን ጥሩ ስሜት ላይ
ስለሆንኩ -
1:00 - 1:03ያንን ታሪክ ዛሬ
ላጋራቹ እፈልጋለሁ -
1:03 - 1:05ቤት ውስጥ ሰባት ልጆች ነበርን
-
1:05 - 1:09ከኔ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ናቸው
-
1:09 - 1:14ይሄ እኔ ነኝ ትንሽ ልጅ
እያለሁ ከአባቴ ጋር -
1:14 - 1:17የሳይንስን እውቀት
ከማግኘቴ በፊት -
1:17 - 1:19ተራ አርሶ አደር ነበርኩ
-
1:19 - 1:22ደሀ አርሷደሮች ባሉበት አገር
-
1:22 - 1:26ልክ እንደሌላው ሁሉ
በቆሎ ነበር የምናበቅለው -
1:26 - 1:31አንድ አመት ላይ
እድላችን መጥፎ ሆኖ ነበር -
1:31 - 1:36በ2001 በጣም ዘግናኝ
ረሀብ አጋጠመን -
1:36 - 1:43በአምስት ወር ውስጥ
መላው ማላዊ እስኪ ሞት ተርቦ ነበር -
1:43 - 1:47ቤተሰቤ በቀን አንዴ ነበር
የሚመገበው ማታ ላይ -
1:47 - 1:51ለእያንዳንዳችን ሶስት ጉርሻ ኒሲማ
ይደርሰን ነበር -
1:51 - 1:53ምግቡ ሰውነታችን ውስጥ ገብቶ
-
1:53 - 1:57ምንም አልጠቀመንም
-
1:57 - 2:00በማላዊ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
-
2:00 - 2:02መክፈል ይጠበቅብናል
-
2:02 - 2:08በረሀቡ ምክያንት ትምህረቴን
ለማቋረጥ ተገደድኩ -
2:08 - 2:10አባቴን ስመለከት
-
2:10 - 2:12የደረቀውን ማሳ ሳይ
-
2:12 - 2:16ልቀበለው የምችለው
የወደፊት እጣ አልነበረም -
2:16 - 2:20ትምህርት ቤት መገኘት
ያስደስተኝ ነበር -
2:20 - 2:25ስለዚህ የሚቻለውን
ለማድረግ ቆርጬ ነበር -
2:25 - 2:27ትምህርት ለማግኘት
-
2:27 - 2:29ስለዚህ ወደ ቤተመጽሀፍት
ሄድኩ -
2:29 - 2:33መጽሀፍቶች አነበብኩ የሳይንስ መጻህፍት
በተለይ የፊዚክስ -
2:33 - 2:35እንግሊዘኛ ያን ያህል ማንበብ
አልችልም ነበር -
2:35 - 2:38የምስል ገለጻዎችንና
ፎቶዎችን እጠቀም ነበር -
2:38 - 2:43በነሱ ዙሪያ ያሉ ቃላት ለመረዳት
-
2:43 - 2:47አንድ መጽሀፍ እውቀትን
በእጄ አስጨበጠኝ -
2:47 - 2:53የንፋስ ተርባይን ውሀ ማፍለቅና
ኤሌክተሪክ ማመንጨት ይችላል ይላል -
2:53 - 2:56ውሀ ማፍለቅ
መስኖ ማለት ነው -
2:56 - 2:58ረሀብን መቋቋሚ ዘዴ
-
2:58 - 3:02በጊዜው ያ ነበር
የኛ ችግር -
3:02 - 3:06ስለዚህ ለራሴ አንድ የንፋስ ተርባይን
ለመስራት ወሰንኩ -
3:06 - 3:09ግን መስሪያ ቁሳቁሶች
አልነበረኝም -
3:09 - 3:11ስለዚህ ቁሻሻ መጣያ ቦታ ሄድኩ
-
3:11 - 3:14ቁሳቁሶችን ከዛ አገኘው
-
3:14 - 3:18ብዙ ሰዎች እናቴን ጨምሮ
-
3:18 - 3:20አብደሀል ሲሉኝ ነበር
-
3:20 - 3:22(ሳቅ)
-
3:22 - 3:24የትራክተር ንፋስ መስጫ፣
-
3:24 - 3:26ንዘረት ተከላካይ፣
የፒቪሲ ቱቦ አገኘሁ -
3:26 - 3:29የባይስክል ቸርኬና
-
3:29 - 3:33ያረጀ የባይስክል
ዳይናሞ በመጠቀም -
3:33 - 3:35መሳሪያዬን ገነባሁ
-
3:35 - 3:38መጀመሪያ ለአንድ መብራት
-
3:38 - 3:41ቀጥሎ አራት መብራቶች
-
3:41 - 3:46አራት መብራቶች ከነ ማብሪያ ማጥፊያ
ሀይል ማገጃ ሳይቀር -
3:46 - 3:50ከኤሌክትሪክ ደወል
ጋር የሚመሳሰል -
3:50 - 3:54ሌላኛው መሳሪያ ውሀ ያፈልቃል
-
3:54 - 3:57ለመስኖ የሚሆን
-
3:57 - 4:00የተወሰኑ ሰዎች ቤቴ ደጃፍ
መሰለፍ ጀመሩ -
4:00 - 4:02(ሳቅ)
-
4:02 - 4:04የሞባይል ስልካቸውን
ሀይል ለመሙላት -
4:04 - 4:08(ጭብጨባ)
-
4:08 - 4:10ላባርራቸው አልቻልኩም!
-
4:10 - 4:12(ሳቅ)
-
4:12 - 4:15ቀጥሎ ሪፖርተሮች መጡ
-
4:15 - 4:17ቀጥሎ ጦማሪያን
-
4:17 - 4:22ቀጥሎ ቴድ ከሚባል ነገር
የስልክ ጥሪ መጣ -
4:22 - 4:24በጭራሽ አውሮብላን አይቼ
አላውቅም ነበር -
4:24 - 4:27ሆቴል ውስጥ
በጭራሽ አድሬ አላውቅም -
4:27 - 4:31የዛን ቀን በአሩሻ
መድረኩ ላይ -
4:31 - 4:34እንግሊዘኛ ጠፋኝ
-
4:34 - 4:37እንደዚህ የመሰለ ነገር ነበር ያልኩት
-
4:37 - 4:41"ሞከርኩ እናም ተሳካልኝ"
-
4:41 - 4:43አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ
-
4:43 - 4:46በውጭ ላሉ እኔን ለሚመስሉ ሁሉ
-
4:46 - 4:49ለአፍሪካኖች እና ለድሆች
-
4:49 - 4:53ህልማችሁን ለማሳካት
ትግል ላይ ላላቹ -
4:53 - 4:55አምላክ ይባርካቹ!
-
4:55 - 4:59ምናልባት አንድ ቀን በድህረ ገጽ
ይሄን ታዩ ይሆናል -
4:59 - 5:04እምላችሁ በራሳችሁ ተማመኑ
እናም እመኑ -
5:04 - 5:06ምንም ነገር ቢከሰት
ተስፋ እንዳትቆርጡ -
5:06 - 5:08አመሰግናለሁ!
-
5:08 - 5:38(ጭብጨባ)
- Title:
- የንፋስን ሀይል እንዴት መጠቀም እንደቻልኩ
- Speaker:
- ዊልያም ካምክዋምባ
- Description:
-
በ14 አመቱ በድህነትና በረሀብ ችግር ውስጥ ያደገው ማላዊው ህጻን ለቤተሰቡ በንፋስ ሀይል የኤሌክትሪክ ማመኝጫ ገነባ፡፡ ዊልያም ካምክዋምባ አሁን በ22 አመቱ ለሁለተኛ ጊዜ በቴድ መድረክ ቀርቦ በራሱ አንደበት ህይወቱን ስለቀየረለት የፈጠራ ስራው ይነግረናል፡፡
- Video Language:
- English
- Team:
closed TED
- Project:
- TEDTalks
- Duration:
- 05:39
![]() |
Dimitra Papageorgiou approved Amharic subtitles for How I harnessed the wind | |
![]() |
dagim zerihun accepted Amharic subtitles for How I harnessed the wind | |
![]() |
dagim zerihun edited Amharic subtitles for How I harnessed the wind | |
![]() |
dagim zerihun edited Amharic subtitles for How I harnessed the wind | |
![]() |
dagim zerihun edited Amharic subtitles for How I harnessed the wind | |
![]() |
dagim zerihun declined Amharic subtitles for How I harnessed the wind | |
![]() |
dagim zerihun edited Amharic subtitles for How I harnessed the wind | |
![]() |
dagim zerihun edited Amharic subtitles for How I harnessed the wind |