YouTube

Har du ett Youtubekonto?

New: enable viewer-created translations and captions on your YouTube channel!

Amharic undertexter

← NatureNow: Greta Thunberg and George Monbiot make short film on the climate crisis

Få inbäddningskod
65 Språk

Undertext översatt från Grekiska Visar version 1 skapad 12/19/2019 av TWB.

 1. ይህ መልእክት እንደዋዛ መታየት ያለበት አደለም፡፡
 2. እኔ ስሜ ግሬታ ቱንበርግ ነው፡፡
 3. እኛ አሁን እየኖርን ያለነው በጅምላ በምንጠፋበት
  ሁኔታ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ነው፡፡
 4. የአየር ንብረታችን በእጅጉ እየተበላሸ ነው፡፡
 5. እንደ እኔ ያሉ ሕጻናት ይህንን ለመቃወም
  ትምህርታቸውን እያቆሙ ነው፡፡
 6. ነገር ግን ይህንን አሁንም ማስተካከል እንችላለን፡፡
 7. እናንተም ይህንን ለማስተካከል አሁንም ትችላላችሁ፡፡
 8. በሕይወት ለመኖር መቀጠል እንችል ዘንድ የቅሪተ አካል ነዳጅን ማቃጠል ማቆም ይኖርብናል፤ ይሁንና ይህ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡
 9. ብዙ መፍትሄዎች ስለመኖራቸው እየተነገረ ይገኛል፤ ነገር ግን ከፊት ለፊታችን ስለሚገኘው መፍትሄ ምን ያህል
 10. እናውቃለን?
 11. የእኔ ጓደኛ ጆርጅ ስለዚህ ጉዳይ እንዲያስረዳ እተዋለሁ፡፡
 12. ካርቦንን ከአየር ውስጥ ስቦ የሚያስወጣ፣ ወጭው አነስተኛ የሆነና
  ራሱን የሚገነባ ተዐምረኛ ማሽን
 13. አለ፡፡
 14. ይህም … ዛፍ ተብሎ ይጠራል፡፡
 15. ዛፍ አንድ የተፈጥሯዊ የአየር ንብረት መፍትሄ ምሣሌ ነው፡፡
 16. ውሃ አካባቢ የሚበቅሉ ዕጽዋቶች፣ በእጽዋት ብስባሽ የተሞሉ
  ረግራጋ መሬቶች፣ ደኖች፣
 17. ረግረጎች፣ የባሕር ወለሎች፣ የኬልፕ ጫካዎች፣ እና የኮራል ሪፎች
 18. ካርቦንን ከአየር ውስጥ በማስወጣት እንዳይመለስ ያደርጉታል፡፡
 19. በእጅጉ የተበላሸውን የአየር ንብረታችንን ለማከም ተፈጥሮ መሣሪያ ነው፡፡
 20. እነዚህ የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎች
  እጅግ ከፍተኛ ልዩነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ናቸው፡፡
 21. እጅግ መልካም ነው፣ አይደል?
 22. ሆኖም የቅሪተ አካል ነዳጆችን በከርሰ ምድር ውስጥ
  እንዳሉ ስንተዋቸው ብቻ ነው፡፡
 23. የሚያናድደው ነገር ግን ይህ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ ትኩረት ነፍገናቸዋል ፡፡
 24. ከተፈጥሯዊ መፍትሄዎች ይልቅ በአለም አቀፍ ደረጃ ለቅሪተ አካል ነዳጅ የምንሰጠው ድጎማ ከአንድ ሺህ እጥፍ በላይ ነው፡፡
 25. የአየር ንብረት መበላሸትን ለመቋቋም ከሚሰጠው ድጋፍ የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎች የሚያገኙት ድጎማ
 26. 2% የሚሆነው ብቻ ነው፡፡
 27. ይህ የእናንተ ገንዘብ፣ የእናንተ የግብር ክፍያ፣
  የእናንተ የቁጠባ ገንዘብ ነው፡፡
 28. ሌላው ዕብደት ደሞ ተፈጥሮን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ
  በእጅጉ በምንፈልጋት በአሁኑ ወቅት
 29. ከምንጊዜውም በላይ በፍጥነት እያወደምናት ነው፡፡
 30. በእያንዳንዱ ቀን እስከ 200 የሚደርሱ የተፈጥሮ ዝርያዎች
  ከምድረ-ገጽ እየጠፉ ነው፡፡
 31. አብዛኛው የአርክቲክ በረዶ ጠፍቷል፡፡
 32. አብዛኛዎቹ የዱር እንስሳቶቻችን የሉም፡፡
 33. አብዛኛው አፈራችን የለም፡፡
 34. እና ምን ማድረግ ይኖርብናል?
 35. እናንተ ምን ማድረግ አለባችሁ?
 36. ቀላል ነው … መከላከል፣ እንደገና መመለስ፣ እና በገንዘብ መደገፍ ያስፈልገናል፡፡
 37. መከላከል
 38. የሐሩር አውራጃ (ትሮፒካል) ደኖች
 39. 30 የእግር ኳስ ሜዳ የሚያህሉት በአንድ ደቂቃ ውስጥ እየተመነጠሩ ይገኛሉ፡፡
 40. ተፈጥሮ በጣም አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ሁሉ
  ልንጠብቀው ወይም ልንከላከለው ይገባል፡፡
 41. እንደገና መመለስ
 42. አብዛኛው የዓለማችን ክፍል ተጎድቷል፡፡
 43. ሆኖም ተፈጥሮ ራሷን መልሳ ማቋቋም የምትችል ሲሆን
 44. እኛም ሥርዓተ-ምህዳሩ ወደነበረበት እንዲመለስ መርዳት እንችላለን፡፡
 45. በገንዘብ መደገፍ
 46. ተፈጥሮን የሚያጠፉ ነገሮችን በገንዘብ ከመደገፍ
 47. እና ይህንንም ለሚረዱ ነገሮች ክፍያ ከመፈጸም መቆጠብ ይኖርብናል፡፡
 48. ይህን ያህል ቀላል ነው፡፡
 49. መከላከል፣ እንደገና መመለስ፣ እና በገንዘብ መደገፍ፡፡
 50. ይህ የትም ሥፍራ ሊፈጸም የሚቻል ነው፡፡
 51. በርካታ ሰዎች የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን መጠቀም ጀምረዋል፡፡
 52. ይህንን እጅግ ከፍተኛ በሆነ መጠን ልንተገብረው ይገባል፡፡
 53. እናንተም የዚህ አንድ አካል መሆን ትችላላችሁ፡፡
 54. ተፈጥሮን ለሚከላከሉ ሰዎች የምርጫ ድምጸችሁን ስጡ፡፡
 55. ይህንን ቪዲዮ ለሌሎችም አጋሩ፡፡
 56. በዚህ ርዕስ ላይ ተወያዩ፡፡
 57. በመላው ዓለም ላይ ለተፈጥሮ አስገራሚ ትግሎች እየተደረጉ ነው፡፡
 58. ተቀላቀሏቸው!
 59. ሁሉም ነገር ዋጋ አለው፡፡
 60. እናንተም የምታደርጉት ዋጋ አለው፡፡