1 00:00:00,000 --> 00:00:05,040 የእግዚአብሔር ሰዉ ሲፀልይልኝ፣ ከፍተኛ ሀይል ተሰማኝ! 2 00:00:05,040 --> 00:00:09,760 መንፈሱ ራሱን ገለጠ እና እኔም ማስታወክ ጀመርኩ። 3 00:00:09,760 --> 00:00:14,160 ደም አስታወኩኝ ከዛም ዉስጤን በጣም ሰላም ይሰማዉ ጀመር። 4 00:00:14,160 --> 00:00:17,360 እናም የሆነ ነገር ይሰማኝ ጀመር- ፅንሱም መገላበጥ ጀመረ! 5 00:00:18,920 --> 00:00:24,320 አሁን በዚህ ሰአት የትኛዉም በእስራት ዉስጥ ያለ የህይወታችሁ ክፍል፣ 6 00:00:24,320 --> 00:00:28,000 በኢየሱስ ስም ነፃ ይዉጣ! 7 00:00:28,000 --> 00:00:31,120 በሀያሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፃ ዉጡ! 8 00:00:31,120 --> 00:00:31,880 በሀያሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፃ ዉጡ! 9 00:00:31,880 --> 00:00:35,680 ያ እንግዳ መንፈስ፣ ያ ንፁህ ያልሆነ መንፈስ 10 00:00:35,680 --> 00:00:44,520 ለህመማችሁ፣ ለእስራታችሁ፣ ለተስፋ መቁረጣችሁ እና ላጋጠማችሁ የህይወት ገደብ ምክንያት የሆነ- 11 00:00:44,520 --> 00:00:48,040 አሁኑኑ ለቅቀሀቸዉ ዉጣ! 12 00:00:48,040 --> 00:00:51,880 ዉጣ! 13 00:00:51,880 --> 00:00:55,800 ኣሁን እየተከሰተ ያለዉን ነገር መመልከት ትችላላችሁ። 14 00:00:55,800 --> 00:01:02,640 ይሄም ፈዉስን፣ መለቀቅን እና ነፃነትን ሊያመጣ የወረደ የእግዚአብሔር ሀይል ነው። 15 00:01:02,640 --> 00:01:05,400 አንተ ሰይጣን- በሽታህን ይዘህ ለቀሀቸዉ ሂድ. 16 00:01:05,400 --> 00:01:07,240 አንተ የህመም ምክንያት ነህ! 17 00:01:07,240 --> 00:01:08,960 አንተ የበሽታ ምክንያት ነህ! 18 00:01:08,960 --> 00:01:10,760 አንተ የህመም ምክንያት ነህ! 19 00:01:10,760 --> 00:01:16,040 የትኛዉም የአካላችሁ ክፍል ላይ የሚገኝ፣ ያ በሽታ፣ ያ ህመም- 20 00:01:16,040 --> 00:01:17,320 አስወጡት፣ አስታዉኩት! 21 00:01:17,320 --> 00:01:20,680 ያንን ህመም አስታዉኩት! ያንን መርዝ አስታዉኩት! 22 00:01:20,680 --> 00:01:24,600 በሀያሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሁን አስታዉኩት! 23 00:01:24,600 --> 00:01:28,840 ዛሬ የፈዉሳችሁ እና የመታደሻ ቀናችሁ ነዉ! 24 00:01:28,840 --> 00:01:33,920 በኢየሱስ ስም ተፈወሱ! 25 00:01:33,920 --> 00:01:38,160 በሀያሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ ተፈወሱ! 26 00:01:38,160 --> 00:01:40,800 ለእናንተ መልካም ዜና አለኝ። 27 00:01:40,800 --> 00:01:47,000 በእግዚአብሔር ምህረት፣ በኢየሱስ ስም ነፃ ወጥታችኋል! 28 00:01:48,320 --> 00:01:53,320 ስሜ ፊፋይል ይባላል አጠገቤ የሚገኘዉ ደግሞ ባለቤቴ ነዉ፣ ስቴፋን ይባላል። 29 00:01:53,320 --> 00:01:57,720 ዛሬ ጌታ ይሄንን እድል ስለሰጠን እጅግ በጣም ደስ ብሎናል 30 00:01:57,720 --> 00:02:01,440 ከዚህ ድንቅ ከሆነዉ ልጃችን ጆሽዋ ጋር ሆነን። 31 00:02:01,440 --> 00:02:06,800 በዚህ ቀን ምስክርነቴን ስለምሰጥ ጌታን አመሰግነዋለሁ 32 00:02:06,800 --> 00:02:11,880 ይሄንን ልጅ ለመዉለድ ስጠባበቅ ስለተከሰተዉ ነገር። 33 00:02:11,880 --> 00:02:17,200 ከከፍተኛ የደም ግፊት የተነሳ ብዙ ችግሮች ነበሩብኝ። 34 00:02:17,200 --> 00:02:20,280 ጋድስ ኸርት ቲቪን አገኘናቸዉ 35 00:02:20,280 --> 00:02:26,720 እናም በዚህ የጋራ ፀሎት ፕሮግራም ላይ እንዲፀለይልን እድሉን አገኘን። 36 00:02:26,720 --> 00:02:31,480 ሲፀለይልኝ፣ በሆስፒታል ዉሰጥ ነበርኩ ልጄንም አልወለድኩትም ነበር። 37 00:02:31,480 --> 00:02:35,600 ከልጁ የመሀፀን ዉስጥ አቀማመጥ የተነሳ- የተወሳሰበ ነገር ሰለነበር። 38 00:02:35,600 --> 00:02:40,160 ስለዚህ ይሄ ከከፍተኛ የደም ግፊት ጋር ተጨማሪ ችግር ነበር። 39 00:02:40,160 --> 00:02:48,040 በሰላም እንድገላገል ሀኪሞች ሁሉንም ነገር እየሞከሩ ነበር። 40 00:02:48,040 --> 00:02:54,440 ሲፀለይልኝ፣ ወዲያዉኑ የመንፈስ ቅዱስ ሀይል ተሰማኝ። 41 00:02:54,440 --> 00:03:00,680 የእግዚአብሔር ሰዉም፣ "ይሄ የእምነት ፀሎት ነዉ፣ ልባችሁን ክፈቱ።" አለን 42 00:03:00,680 --> 00:03:04,920 ምክንያቱም ሩቅ ብሆንም፣ ርቀት ገደብ አይደለም። 43 00:03:04,920 --> 00:03:07,880 እንደዉም እግዚአብሔር በርቀት ዉስጥ የበለጠ ይሰራል! 44 00:03:07,880 --> 00:03:13,360 ይሄም እግዚአብህሔር ለእኛ ያቀዳት ጊዜ እንደነበር አዉቅ ነበር። 45 00:03:13,360 --> 00:03:16,040 ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ቀጠሮ ነበረን! 46 00:03:16,040 --> 00:03:25,040 ምክንያቱ ለእኔ ሆስፒታል ዉስጥ ሆኜ ሲፀለይልኝ የተለይ እንደሚሆን አምን ነበር! 47 00:03:25,040 --> 00:03:30,080 የእግዚአብሔር ሰዉ ሲፀልይልኝ፣ ከፍተኛ ሀይል ተሰማኝ! 48 00:03:30,080 --> 00:03:34,800 መንፈሱም ራሱን ገልጦ ማስታወክ ጀመርኩ። 49 00:03:34,800 --> 00:03:39,200 ደም ካስታወኩ በኋላ በጣም ቀለለኝ። 50 00:03:39,200 --> 00:03:43,720 ልጁም በሆዴ ዉስጥ መገላበጥ ጀመረ! 51 00:03:43,720 --> 00:03:52,480 ይሄም ከጌታ ከኢየሱስ የተነሳ እንደሆነ ገባኝ እናም እጄን ጭኜ ኢየሱስ ሆይ አመሰግንሀለሁ ማለት ጀመርኩ! 52 00:03:52,480 --> 00:03:55,600 ከፀሎቱም በኋላ ሊያዩኝ መጡ እና እንዲህ አሉኝ፡ 53 00:03:55,600 --> 00:03:59,080 " እዎ- የሆነ ነገር ተፈጥሯል! ልጁ ወደ ታች ወርዷል!" 54 00:03:59,080 --> 00:04:02,840 ከዚያ በፊት የልጁ አቀማመጥ ወደ ላይ አካባቢ ነበር፣ 55 00:04:02,840 --> 00:04:08,160 ልጁም ወደ ታች ዝቅ አለ ስለዚህ በሰላም መዉለድ እችላለሁ ማለት ነዉ። 56 00:04:08,160 --> 00:04:13,520 የደም ግፊቴንም ለኩት እና በጣም መልካም ሁኔታ ላይ ነዉ! 57 00:04:13,520 --> 00:04:18,160 ከተፀለይልኝ በኋላ የደም ግፊቴን ለኩት፣ በጣም ጥሩ ነበር! 58 00:04:18,160 --> 00:04:20,400 ጌታን በጣም አመሰግነዋለሁ። 59 00:04:20,400 --> 00:04:23,120 ከዛም መዉለድ ቻልኩ። 60 00:04:23,120 --> 00:04:25,680 ይሄንን ድንቅ ልጅ ተገላገልኩ! 61 00:04:25,680 --> 00:04:30,160 የሆስፒታሉ አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጬ እየተጠባበኩ ነበር 62 00:04:30,160 --> 00:04:35,440 የሆነ ብርቱ ድምፅ እንድነሳ ሲናገረኝ። 63 00:04:35,440 --> 00:04:42,400 በሶስት ደቂቃ ዉስጥ ተነሳሁ፣ ዉሀዉም መፍሰስ ጀመረ። 64 00:04:42,400 --> 00:04:44,920 "ኢየሱስ ይመስገን!" አልኩ 65 00:04:44,920 --> 00:04:49,080 ማልቀስ ጀመርኩ ምክንያቱም ኢየሱስ ብቻ ነዉ ይሄንን ማድረግ የሚችለዉ። 66 00:04:49,080 --> 00:04:54,560 አምስት ልጆች ስለነበሩኝ ኢየሱስ ይሄኛዉን እንድወልድ ረዳኝ። 67 00:04:54,560 --> 00:04:57,800 ብዙ ልጆችን ወልጄ ነበር። 68 00:04:57,800 --> 00:05:02,520 ከዚህም የተነሳ ይሄንኛዉም በጌታ እጅ ነበር። 69 00:05:02,520 --> 00:05:07,360 እርሱ ነበር ሲረዳኝ የነበረዉ። በመዉለጃ ክፍል ዉስጥ ምንም ህመም አልነበረኝም! 70 00:05:07,360 --> 00:05:14,120 ለዚህ ነው ከፀሎት የተነሳ እንደሆነ ያወኩት! ፀሎቱ በጣም ሀይል ነበረዉ። 71 00:05:14,120 --> 00:05:19,160 የጠላትን ስራ ሁሉ አስወግዶ ኢየሱስ ነበር ሲሰራ የነበረው! 72 00:05:19,160 --> 00:05:22,280 ሰላም ስሜ ስቴፋን ይባላል። 73 00:05:22,280 --> 00:05:26,880 እጠገቤ ዉዷ ባለቤቴ ፌፋይል እና አዲሱ ልጃችን ጆሽዋ አሉ። 74 00:05:26,880 --> 00:05:28,920 ጀርመን ነዉ ያለነዉ። 75 00:05:28,920 --> 00:05:35,200 በጋድስ ኸርት ቲቪ በወንድም ክሪስ ተፀለይልን፣ 76 00:05:35,200 --> 00:05:38,040 ባለቤቴ ሆስፒታል ዉስጥ ነበረች። 77 00:05:38,040 --> 00:05:42,360 ለአምስተኛ ጊዜ የህክምና ሂደት ዉስጥ ማለፍ ነበረባት- 78 00:05:42,360 --> 00:05:48,960 ሁል ጊዜ ልትወልድ ስትል ከፍ ያለ የደም ግፊት እና ህመም ያጋጥማታል። 79 00:05:48,960 --> 00:05:54,880 ፀሎቱ የተፀለየላት ጊዜ ማስታወክ ጀመረች እናም ነፃ ወጣች። 80 00:05:54,880 --> 00:06:00,280 ልጁንም ስትወልድ፣ በጣም ፈጣን ነበር። 81 00:06:00,280 --> 00:06:07,840 በምጧ ጊዜ ምንም ህመም አልነበራትም። አንዴ አማጠች ከዛም ልጁ ወጣ። 82 00:06:07,840 --> 00:06:11,920 በጣም ፈጣን ከመሆኑ የተነሳ ሀኪሞቹ ራሱ ተደንቀዉ ነበር። 83 00:06:11,920 --> 00:06:18,480 ከወንድም ክሪስ ጋር በጋድስ ኸርት ቲቪ በኩል መገናኘታችን በጣም የሚገርም ነበር። 84 00:06:18,480 --> 00:06:22,880 የነበረባት ከፍተኛ የደም ግፊት- 85 00:06:22,880 --> 00:06:27,760 ከተፀለየላት አንድ ሰአት በኋላ ተመርምራ የደም ግፊቷ ፍፁም መልካም ነበር። 86 00:06:27,760 --> 00:06:32,120 ህኪሞቹ ራሱ ተገርመዉ ነበር፣ በጣምም ይገርም ነበር! 87 00:06:32,120 --> 00:06:35,600 አሁን ላይ በጣም ጤነኛ ወንድ ልጅ አለን። 88 00:06:35,600 --> 00:06:39,480 ባለቤቴም በጣም ጥሩ ጤንነት ላይ ትገኛለች። 89 00:06:39,480 --> 00:06:44,840 ኢየሱስን፣ ወንድም ክሪስን እና ጋድስ ኸርት ቲቪን እናመሰግናለን። 90 00:06:44,840 --> 00:06:51,120 የጋራ ፀሎቱ በጣም ሀይለኛ ነዉ፣ ህይወትን የመቀየር አቅም አለዉ። 91 00:06:51,120 --> 00:06:58,240 እኔ በግሌ፣ ከባድ የራስምታት ህመም ነበረብኝ። 92 00:06:58,240 --> 00:07:01,240 የሆነ ጫና ሲበዛብኝ የራስ ምታቱ ይጀምረኛል። 93 00:07:01,240 --> 00:07:04,960 ያኔ በጀርባዬ መጋደም ይኖርብኛል- የወለደች ጊዜ አካባቢ ራሱ። 94 00:07:04,960 --> 00:07:08,480 ከወንድም ክሪስ ፀሎት በኋላ- 95 00:07:08,480 --> 00:07:12,400 ምንም አይነት ህመም ሆነ ራስ ምታት የለብኝም። 96 00:07:12,400 --> 00:07:15,680 አሁን ሁለተኛ ሳምንቱ ነዉ እናም ፍፁም ነፃ ነኝ። 97 00:07:15,680 --> 00:07:19,720 ፀሎቱም ህይለኛ እና ህይወትን የሚቀይር ነዉ። 98 00:07:19,720 --> 00:07:23,560 ልብን ይቀይራል 99 00:07:23,560 --> 00:07:30,000 በሰዉነት ላይ ተገልጦ ፈዉስን እና ነፃነትን ይሰጣል። 100 00:07:30,000 --> 00:07:36,840 የጋድስ ኸርት ቲቪን እየተከታተሉ ያሉትን ማበረታታት እፈልጋለሁ። 101 00:07:36,840 --> 00:07:40,640 ከምንም በላይ ልባችሁን ለኢየሱስ አዘጋጁ። 102 00:07:40,640 --> 00:07:47,160 ከኢየሱስ ጋር ተገናኙ እናም መንፈስ ቅዱስ በፀሎት ጊዜ ያገኛችኋል። 103 00:07:47,160 --> 00:07:52,720 እግዚአብሄር እንደሚነካቸሁ፣ እንዳሚፈዉሳችሁ እና ፀሎታችሁን እንደሚመልስ እመኑ 104 00:07:52,720 --> 00:07:56,400 ምክንያቱም እግዚአብሔር ፀሎትን የሚመልስ አምላክ ነዉና! 105 00:07:57,000 --> 00:07:59,080 መልካም ጠዋት! 106 00:07:59,080 --> 00:08:07,040 ጌታ ኢየሱስ፣ ስለ ጋድስ ኸርት ቲቪ አመሰግንሀለዉ! 107 00:08:07,040 --> 00:08:09,840 ወንድም ክሪስ አመሰግንሀለዉ።