የእግዚአብሔር ሰዉ ሲፀልይልኝ፣ ከፍተኛ ሀይል ተሰማኝ!
መንፈሱ ራሱን ገለጠ እና እኔም ማስታወክ ጀመርኩ።
ደም አስታወኩኝ ከዛም ዉስጤን በጣም ሰላም ይሰማዉ ጀመር።
እናም የሆነ ነገር ይሰማኝ ጀመር- ፅንሱም መገላበጥ ጀመረ!
አሁን በዚህ ሰአት የትኛዉም በእስራት ዉስጥ ያለ የህይወታችሁ ክፍል፣
በኢየሱስ ስም ነፃ ይዉጣ!
በሀያሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፃ ዉጡ!
በሀያሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፃ ዉጡ!
ያ እንግዳ መንፈስ፣ ያ ንፁህ ያልሆነ መንፈስ
ለህመማችሁ፣ ለእስራታችሁ፣ ለተስፋ መቁረጣችሁ እና ላጋጠማችሁ የህይወት ገደብ ምክንያት የሆነ-
አሁኑኑ ለቅቀሀቸዉ ዉጣ!
ዉጣ!
ኣሁን እየተከሰተ ያለዉን ነገር መመልከት ትችላላችሁ።
ይሄም ፈዉስን፣ መለቀቅን እና ነፃነትን ሊያመጣ የወረደ የእግዚአብሔር ሀይል ነው።
አንተ ሰይጣን- በሽታህን ይዘህ ለቀሀቸዉ ሂድ.
አንተ የህመም ምክንያት ነህ!
አንተ የበሽታ ምክንያት ነህ!
አንተ የህመም ምክንያት ነህ!
የትኛዉም የአካላችሁ ክፍል ላይ የሚገኝ፣ ያ በሽታ፣ ያ ህመም-
አስወጡት፣ አስታዉኩት!
ያንን ህመም አስታዉኩት! ያንን መርዝ አስታዉኩት!
በሀያሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሁን አስታዉኩት!
ዛሬ የፈዉሳችሁ እና የመታደሻ ቀናችሁ ነዉ!
በኢየሱስ ስም ተፈወሱ!
በሀያሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ ተፈወሱ!
ለእናንተ መልካም ዜና አለኝ።
በእግዚአብሔር ምህረት፣ በኢየሱስ ስም ነፃ ወጥታችኋል!
ስሜ ፊፋይል ይባላል አጠገቤ የሚገኘዉ ደግሞ ባለቤቴ ነዉ፣ ስቴፋን ይባላል።
ዛሬ ጌታ ይሄንን እድል ስለሰጠን እጅግ በጣም ደስ ብሎናል
ከዚህ ድንቅ ከሆነዉ ልጃችን ጆሽዋ ጋር ሆነን።
በዚህ ቀን ምስክርነቴን ስለምሰጥ ጌታን አመሰግነዋለሁ
ይሄንን ልጅ ለመዉለድ ስጠባበቅ ስለተከሰተዉ ነገር።
ከከፍተኛ የደም ግፊት የተነሳ ብዙ ችግሮች ነበሩብኝ።
ጋድስ ኸርት ቲቪን አገኘናቸዉ
እናም በዚህ የጋራ ፀሎት ፕሮግራም ላይ እንዲፀለይልን እድሉን አገኘን።
ሲፀለይልኝ፣ በሆስፒታል ዉሰጥ ነበርኩ ልጄንም አልወለድኩትም ነበር።
ከልጁ የመሀፀን ዉስጥ አቀማመጥ የተነሳ- የተወሳሰበ ነገር ሰለነበር።
ስለዚህ ይሄ ከከፍተኛ የደም ግፊት ጋር ተጨማሪ ችግር ነበር።
በሰላም እንድገላገል ሀኪሞች ሁሉንም ነገር እየሞከሩ ነበር።
ሲፀለይልኝ፣ ወዲያዉኑ የመንፈስ ቅዱስ ሀይል ተሰማኝ።
የእግዚአብሔር ሰዉም፣ "ይሄ የእምነት ፀሎት ነዉ፣ ልባችሁን ክፈቱ።" አለን
ምክንያቱም ሩቅ ብሆንም፣ ርቀት ገደብ አይደለም።
እንደዉም እግዚአብሔር በርቀት ዉስጥ የበለጠ ይሰራል!
ይሄም እግዚአብህሔር ለእኛ ያቀዳት ጊዜ እንደነበር አዉቅ ነበር።
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ቀጠሮ ነበረን!
ምክንያቱ ለእኔ ሆስፒታል ዉስጥ ሆኜ ሲፀለይልኝ የተለይ እንደሚሆን አምን ነበር!
የእግዚአብሔር ሰዉ ሲፀልይልኝ፣ ከፍተኛ ሀይል ተሰማኝ!
መንፈሱም ራሱን ገልጦ ማስታወክ ጀመርኩ።
ደም ካስታወኩ በኋላ በጣም ቀለለኝ።
ልጁም በሆዴ ዉስጥ መገላበጥ ጀመረ!
ይሄም ከጌታ ከኢየሱስ የተነሳ እንደሆነ ገባኝ እናም እጄን ጭኜ ኢየሱስ ሆይ አመሰግንሀለሁ ማለት ጀመርኩ!
ከፀሎቱም በኋላ ሊያዩኝ መጡ እና እንዲህ አሉኝ፡
" እዎ- የሆነ ነገር ተፈጥሯል! ልጁ ወደ ታች ወርዷል!"
ከዚያ በፊት የልጁ አቀማመጥ ወደ ላይ አካባቢ ነበር፣
ልጁም ወደ ታች ዝቅ አለ ስለዚህ በሰላም መዉለድ እችላለሁ ማለት ነዉ።
የደም ግፊቴንም ለኩት እና በጣም መልካም ሁኔታ ላይ ነዉ!
ከተፀለይልኝ በኋላ የደም ግፊቴን ለኩት፣ በጣም ጥሩ ነበር!
ጌታን በጣም አመሰግነዋለሁ።
ከዛም መዉለድ ቻልኩ።
ይሄንን ድንቅ ልጅ ተገላገልኩ!
የሆስፒታሉ አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጬ እየተጠባበኩ ነበር
የሆነ ብርቱ ድምፅ እንድነሳ ሲናገረኝ።
በሶስት ደቂቃ ዉስጥ ተነሳሁ፣ ዉሀዉም መፍሰስ ጀመረ።
"ኢየሱስ ይመስገን!" አልኩ
ማልቀስ ጀመርኩ ምክንያቱም ኢየሱስ ብቻ ነዉ ይሄንን ማድረግ የሚችለዉ።
አምስት ልጆች ስለነበሩኝ ኢየሱስ ይሄኛዉን እንድወልድ ረዳኝ።
ብዙ ልጆችን ወልጄ ነበር።
ከዚህም የተነሳ ይሄንኛዉም በጌታ እጅ ነበር።
እርሱ ነበር ሲረዳኝ የነበረዉ። በመዉለጃ ክፍል ዉስጥ ምንም ህመም አልነበረኝም!
ለዚህ ነው ከፀሎት የተነሳ እንደሆነ ያወኩት! ፀሎቱ በጣም ሀይል ነበረዉ።
የጠላትን ስራ ሁሉ አስወግዶ ኢየሱስ ነበር ሲሰራ የነበረው!
ሰላም ስሜ ስቴፋን ይባላል።
እጠገቤ ዉዷ ባለቤቴ ፌፋይል እና አዲሱ ልጃችን ጆሽዋ አሉ።
ጀርመን ነዉ ያለነዉ።
በጋድስ ኸርት ቲቪ በወንድም ክሪስ ተፀለይልን፣
ባለቤቴ ሆስፒታል ዉስጥ ነበረች።
ለአምስተኛ ጊዜ የህክምና ሂደት ዉስጥ ማለፍ ነበረባት-
ሁል ጊዜ ልትወልድ ስትል ከፍ ያለ የደም ግፊት እና ህመም ያጋጥማታል።
ፀሎቱ የተፀለየላት ጊዜ ማስታወክ ጀመረች እናም ነፃ ወጣች።
ልጁንም ስትወልድ፣ በጣም ፈጣን ነበር።
በምጧ ጊዜ ምንም ህመም አልነበራትም። አንዴ አማጠች ከዛም ልጁ ወጣ።
በጣም ፈጣን ከመሆኑ የተነሳ ሀኪሞቹ ራሱ ተደንቀዉ ነበር።
ከወንድም ክሪስ ጋር በጋድስ ኸርት ቲቪ በኩል መገናኘታችን በጣም የሚገርም ነበር።
የነበረባት ከፍተኛ የደም ግፊት-
ከተፀለየላት አንድ ሰአት በኋላ ተመርምራ የደም ግፊቷ ፍፁም መልካም ነበር።
ህኪሞቹ ራሱ ተገርመዉ ነበር፣ በጣምም ይገርም ነበር!
አሁን ላይ በጣም ጤነኛ ወንድ ልጅ አለን።
ባለቤቴም በጣም ጥሩ ጤንነት ላይ ትገኛለች።
ኢየሱስን፣ ወንድም ክሪስን እና ጋድስ ኸርት ቲቪን እናመሰግናለን።
የጋራ ፀሎቱ በጣም ሀይለኛ ነዉ፣ ህይወትን የመቀየር አቅም አለዉ።
እኔ በግሌ፣ ከባድ የራስምታት ህመም ነበረብኝ።
የሆነ ጫና ሲበዛብኝ የራስ ምታቱ ይጀምረኛል።
ያኔ በጀርባዬ መጋደም ይኖርብኛል- የወለደች ጊዜ አካባቢ ራሱ።
ከወንድም ክሪስ ፀሎት በኋላ-
ምንም አይነት ህመም ሆነ ራስ ምታት የለብኝም።
አሁን ሁለተኛ ሳምንቱ ነዉ እናም ፍፁም ነፃ ነኝ።
ፀሎቱም ህይለኛ እና ህይወትን የሚቀይር ነዉ።
ልብን ይቀይራል
በሰዉነት ላይ ተገልጦ ፈዉስን እና ነፃነትን ይሰጣል።
የጋድስ ኸርት ቲቪን እየተከታተሉ ያሉትን ማበረታታት እፈልጋለሁ።
ከምንም በላይ ልባችሁን ለኢየሱስ አዘጋጁ።
ከኢየሱስ ጋር ተገናኙ እናም መንፈስ ቅዱስ በፀሎት ጊዜ ያገኛችኋል።
እግዚአብሄር እንደሚነካቸሁ፣ እንዳሚፈዉሳችሁ እና ፀሎታችሁን እንደሚመልስ እመኑ
ምክንያቱም እግዚአብሔር ፀሎትን የሚመልስ አምላክ ነዉና!
መልካም ጠዋት!
ጌታ ኢየሱስ፣ ስለ ጋድስ ኸርት ቲቪ አመሰግንሀለዉ!
ወንድም ክሪስ አመሰግንሀለዉ።