ሰላም ይህ አጭር ቪዲዮ አሁን በድጋሚ በGMTK ቪዲዮዎች ላይ የተተረጎሙ መግለጫ ጽሁፎችን ማበርከት እንደምትችሉ ለማሳወቅ ነው። YouTube በቅርብ ጊዜ ይህንን ችሎታ ቢያስወግድም አሁን በድጋሚ ይህንን ማድረግ ይምትችሉበት መንገድ አዘጋጅቻለኡው፡፡ የምታደርጉት እንደዚህ ነው... በሁሉም ቪዲዮዎች መግለቻ ጽሁፍ መጨረሻ ላይ ቪዲዮው በAmara (ነጻ የማህበረሰብ መተርጎሚያ ድረገጽ) ላይ ወዳለው ገጹ የሚመራ ሊንክ ይግኛል። በAmara ላይ አካውንት ክክፈቱ በኋላ "Add/Edit subtitles" የሚለውን በመጫን ማበርከት የሚፈልጉትን ቋንቋ መምረጥ ይቻላል። ከዚያ በኋላ የእንግሊዝኛ ጽሁፉን በግራ በኩል እየተመለከቱ የእርስዎን ትርጉም በቀኝ በኩል ባለው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ሁሉንም ከጨረሱ በኋላ "Yes, start syncing" የሚለውን ተጫኑ። ከዛ በኋላ እኔ ጋር ትርጉም እንዳስገቡ ማስታወቂያ ሲደርሰኝ የእናንተን ትርጉም ወደ ቪዲዮው ማስገባት እችላለው። የእናንተንም Amara ስም በቪዲዮው መግለጫ ውስጥ አካትተዋለው። በአዳዲስ ቪዲዮዎች ላይ ለመፍጠን ብሞክርም በቆዩ ቪዲዮዎች ላይ ግን ትርጉሞቹን መጨመር የምችለው በወር አንዴ ብች ነው። በደንብ ግልጽ ለመሆን ሁሉም ትርጉሞች የሚጨመሩት በፍላጎት ነው። እኔ ማንም ይህንን እንዴያደርግ እየጠየኩ አይድለም ግን መተባበር የፈለገን እቀበላለው። እስካሁንም የGMTK ቪዲዮዎችን ወደ ፈረንሳይኛ፣ ጣልያንኛ፣ ኮሪያኛ ቱርክኛ፣ ጃፓንኛ፣ ስፓኒሽ እንዲሁም ወደ ሌሎች ብዙ ብዙ ቋንቋዎች በመተርጎም የተባበሩኝን አመሰግናለው። የጌም ፈጠራ እውቀት ነጻና ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን እያደረጋቹ ነው። ስለዚህ አመሰግናለሁ እና በቅርቡ እንገናኛለን።