እንዴት መመዝገብ ይቻላል
ወደ ማህበረሰባዊ የትርጉም ፕሮጀክት እንኳን በደኅና መጡ
ማበርከት ለመጀመር
ወደ ቴድ ዶት ኮም በመሄድ የራሶን ገጽ ይክፈቱ
ከዛም መመዝገብ ይኖርቦታል
በድረ-ገጽ የትርጉምና የድምፅ ወደ ፅሁፍ የመቀየሪያ መሳሪያችን ወደ ሆነው አማራ
ይህን ለማድረግ ወደ Amara.org ይሂዱ
የቴድ አድረሻዎን በመጠቀም ይቀላቀሉ
አሁን ቋንቋዎን ይምረጡ
በማህበረሰባዊ የትርጉም ፕሮጀክት ላይ
የቴድ እንግሊዘኛ ንግግሮችን ከመተርጎም ባሻገር
በሌላ ቋንቋ የተካሄዱ የቴድ ኤክስ ንግግሮችን መተርጎምና ከድምፅ ወደ ፅሁፍ መቀየር ይችላሉ
እዚ ላይ የፈለጉትን ቋንቋ ይምረጡ
ለመተርጎምና ከድምፅ ወደ ፅሁፍ ለመቀየር ይቀለኛል የሚሉትን
ከዛም መመዝገብ ይኖርቦታል "Apply to Join." የሚለውን ይጫኑ
የተወሰኑ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ይጠየቃሉ
በትክክል ለመመለስ ይጣሩ
ሁሉንም በእንግሊዘኛ መመለሶን አይዘንጉ
ዝግጁ ሲሆኑ ማመልከቻዎን ያስገቡ
እስቲ ፍንጭ ልስጦት
በአማራ የሚላክሎት መልዕክት በኢሜል አድራሻዎ በኩል ማረጋገጦን አይዘንጉ
ይሄ መረጃዎች እንዲደርሶ ያስችላል
በተለይ ማመልከቻዎ ተቀባይነት ያገኘ ጊዜ
አብዛኘውን ጊዜ አንድ ማመልከቻ ለማጽደቅ አምስት ቀናት ያስፈልጉናል
ይህንን ጊዜ በመዘጋጀት ያሳልፉ
በቴድ ዶት ኮም፣ ዊኪ እና ኦቲፔዲያ ላይ የሚገኙትን የስልጠና መሳሪያዎቻችንን በመመልት
የቴድ፣ የቴዴክስ ንግግሮችን እና የቴድ ኤድ ትምህርቶችን በመመልከት
ሊተረጉሙ የሚሹትን ይምረጡ
ማመልከቻዎ ተቀባይነት ሲያገኝ
ከማህበረሰባዊ የትርጉም ፕሮጀክት አባላት ጋር ይገናኙ
በጠቅላላ የፌስቡክ ግሩፓችን ውስጥ
‹ቴድ ቶክ እተረጉማለሁ› እና ‹ቴድ ኤክስ ቶኮችን ከድምፅ ወደ ፅሁፍ እቀይራለሁ› በሚሉት ውስጥ
እናም ሁሌ በማደግ ላይ ባለው ኦቲፒዲያ ዝርዝር ውስጥ የእርሶን የቋንቋ ቡድን (ግሩፕ) ይፈልጉ
ለአሁኑ መልካም የትርጉምና ከድምፅ ወደ ፅሁፍ የመቀየር ስራ ይሁንሎ!