0:00:01.560,0:00:04.135 ይህ መልእክት እንደዋዛ መታየት ያለበት አደለም፡፡ 0:00:04.375,0:00:06.651 እኔ ስሜ ግሬታ ቱንበርግ ነው፡፡ 0:00:06.852,0:00:10.212 እኛ አሁን እየኖርን ያለነው በጅምላ በምንጠፋበት[br]ሁኔታ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ነው፡፡ 0:00:11.171,0:00:13.612 የአየር ንብረታችን በእጅጉ እየተበላሸ ነው፡፡ 0:00:14.022,0:00:18.217 እንደ እኔ ያሉ ሕጻናት ይህንን ለመቃወም[br]ትምህርታቸውን እያቆሙ ነው፡፡ 0:00:18.561,0:00:20.897 ነገር ግን ይህንን አሁንም ማስተካከል እንችላለን፡፡ 0:00:20.897,0:00:22.963 እናንተም ይህንን ለማስተካከል አሁንም ትችላላችሁ፡፡ 0:00:23.372,0:00:26.577 በሕይወት ለመኖር መቀጠል እንችል ዘንድ የቅሪተ አካል ነዳጅን ማቃጠል ማቆም ይኖርብናል፤ ይሁንና ይህ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ 0:00:27.217,0:00:29.822 ብዙ መፍትሄዎች ስለመኖራቸው እየተነገረ ይገኛል፤ ነገር ግን ከፊት ለፊታችን ስለሚገኘው መፍትሄ ምን ያህል 0:00:30.112,0:00:32.692 እናውቃለን? 0:00:32.692,0:00:35.412 የእኔ ጓደኛ ጆርጅ ስለዚህ ጉዳይ እንዲያስረዳ እተዋለሁ፡፡ 0:00:35.682,0:00:38.112 ካርቦንን ከአየር ውስጥ ስቦ የሚያስወጣ፣ ወጭው አነስተኛ የሆነና[br]ራሱን የሚገነባ ተዐምረኛ ማሽን 0:00:38.211,0:00:42.721 አለ፡፡ 0:00:42.721,0:00:44.418 ይህም … ዛፍ ተብሎ ይጠራል፡፡ 0:00:44.418,0:00:46.466 ዛፍ አንድ የተፈጥሯዊ የአየር ንብረት መፍትሄ ምሣሌ ነው፡፡ 0:00:46.576,0:00:47.929 ውሃ አካባቢ የሚበቅሉ ዕጽዋቶች፣ በእጽዋት ብስባሽ የተሞሉ[br]ረግራጋ መሬቶች፣ ደኖች፣ 0:00:47.929,0:00:48.872 ረግረጎች፣ የባሕር ወለሎች፣ የኬልፕ ጫካዎች፣ እና የኮራል ሪፎች 0:00:48.952,0:00:53.692 ካርቦንን ከአየር ውስጥ በማስወጣት እንዳይመለስ ያደርጉታል፡፡ 0:00:53.692,0:00:56.502 በእጅጉ የተበላሸውን የአየር ንብረታችንን ለማከም ተፈጥሮ መሣሪያ ነው፡፡ 0:00:56.502,0:00:58.772 እነዚህ የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎች[br]እጅግ ከፍተኛ ልዩነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ናቸው፡፡ 0:00:58.772,0:01:02.692 እጅግ መልካም ነው፣ አይደል? 0:01:03.212,0:01:05.957 ሆኖም የቅሪተ አካል ነዳጆችን በከርሰ ምድር ውስጥ[br]እንዳሉ ስንተዋቸው ብቻ ነው፡፡ 0:01:05.957,0:01:08.093 የሚያናድደው ነገር ግን ይህ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ ትኩረት ነፍገናቸዋል ፡፡ 0:01:08.502,0:01:12.325 ከተፈጥሯዊ መፍትሄዎች ይልቅ በአለም አቀፍ ደረጃ ለቅሪተ አካል ነዳጅ የምንሰጠው ድጎማ ከአንድ ሺህ እጥፍ በላይ ነው፡፡ 0:01:12.325,0:01:14.012 የአየር ንብረት መበላሸትን ለመቋቋም ከሚሰጠው ድጋፍ የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎች የሚያገኙት ድጎማ 0:01:14.222,0:01:17.622 2% የሚሆነው ብቻ ነው፡፡ 0:01:19.702,0:01:21.892 0:01:21.892,0:01:24.402 ይህ የእናንተ ገንዘብ፣ የእናንተ የግብር ክፍያ፣ [br]የእናንተ የቁጠባ ገንዘብ ነው፡፡ 0:01:25.744,0:01:30.548 ሌላው ዕብደት ደሞ ተፈጥሮን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ [br]በእጅጉ በምንፈልጋት በአሁኑ ወቅት 0:01:30.548,0:01:32.842 ከምንጊዜውም በላይ በፍጥነት እያወደምናት ነው፡፡ 0:01:32.842,0:01:35.377 በእያንዳንዱ ቀን እስከ 200 የሚደርሱ የተፈጥሮ ዝርያዎች [br]ከምድረ-ገጽ እየጠፉ ነው፡፡ 0:01:35.377,0:01:37.095 አብዛኛው የአርክቲክ በረዶ ጠፍቷል፡፡ 0:01:37.095,0:01:39.453 አብዛኛዎቹ የዱር እንስሳቶቻችን የሉም፡፡ 0:01:39.453,0:01:41.021 አብዛኛው አፈራችን የለም፡፡ 0:01:41.021,0:01:43.468 እና ምን ማድረግ ይኖርብናል? 0:01:43.773,0:01:44.958 እናንተ ምን ማድረግ አለባችሁ? 0:01:44.958,0:01:47.211 ቀላል ነው … መከላከል፣ እንደገና መመለስ፣ እና በገንዘብ መደገፍ ያስፈልገናል፡፡ 0:01:47.211,0:01:50.094 መከላከል 0:01:50.094,0:01:54.228 የሐሩር አውራጃ (ትሮፒካል) ደኖች 0:01:54.462,0:01:57.050 30 የእግር ኳስ ሜዳ የሚያህሉት በአንድ ደቂቃ ውስጥ እየተመነጠሩ ይገኛሉ፡፡ 0:01:57.050,0:01:59.029 ተፈጥሮ በጣም አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ሁሉ [br]ልንጠብቀው ወይም ልንከላከለው ይገባል፡፡ 0:01:59.029,0:02:01.012 እንደገና መመለስ 0:02:01.012,0:02:02.813 አብዛኛው የዓለማችን ክፍል ተጎድቷል፡፡ 0:02:02.813,0:02:04.374 ሆኖም ተፈጥሮ ራሷን መልሳ ማቋቋም የምትችል ሲሆን 0:02:04.374,0:02:05.458 እኛም ሥርዓተ-ምህዳሩ ወደነበረበት እንዲመለስ መርዳት እንችላለን፡፡ 0:02:05.458,0:02:06.225 በገንዘብ መደገፍ 0:02:06.225,0:02:07.429 ተፈጥሮን የሚያጠፉ ነገሮችን በገንዘብ ከመደገፍ 0:02:07.429,0:02:08.501 እና ይህንንም ለሚረዱ ነገሮች ክፍያ ከመፈጸም መቆጠብ ይኖርብናል፡፡ 0:02:08.501,0:02:09.513 ይህን ያህል ቀላል ነው፡፡ 0:02:10.084,0:02:11.198 መከላከል፣ እንደገና መመለስ፣ እና በገንዘብ መደገፍ፡፡ 0:02:11.198,0:02:13.325 ይህ የትም ሥፍራ ሊፈጸም የሚቻል ነው፡፡ 0:02:13.325,0:02:16.153 በርካታ ሰዎች የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን መጠቀም ጀምረዋል፡፡ 0:02:16.153,0:02:18.679 ይህንን እጅግ ከፍተኛ በሆነ መጠን ልንተገብረው ይገባል፡፡ 0:02:18.679,0:02:20.505 እናንተም የዚህ አንድ አካል መሆን ትችላላችሁ፡፡ 0:02:20.505,0:02:21.878 ተፈጥሮን ለሚከላከሉ ሰዎች የምርጫ ድምጸችሁን ስጡ፡፡ 0:02:21.878,0:02:24.581 ይህንን ቪዲዮ ለሌሎችም አጋሩ፡፡ 0:02:24.581,0:02:26.581 በዚህ ርዕስ ላይ ተወያዩ፡፡ 0:02:26.581,0:02:30.042 በመላው ዓለም ላይ ለተፈጥሮ አስገራሚ ትግሎች እየተደረጉ ነው፡፡ 0:02:31.051,0:02:31.881 ተቀላቀሏቸው! 0:02:32.702,0:02:36.172 ሁሉም ነገር ዋጋ አለው፡፡ 0:02:36.172,0:02:38.412 እናንተም የምታደርጉት ዋጋ አለው፡፡