WEBVTT 00:00:01.560 --> 00:00:04.135 ይህ መልእክት እንደዋዛ መታየት ያለበት አደለም፡፡ 00:00:04.375 --> 00:00:06.651 እኔ ስሜ ግሬታ ቱንበርግ ነው፡፡ 00:00:06.852 --> 00:00:10.212 እኛ አሁን እየኖርን ያለነው በጅምላ በምንጠፋበት ሁኔታ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ነው፡፡ 00:00:11.171 --> 00:00:13.612 የአየር ንብረታችን በእጅጉ እየተበላሸ ነው፡፡ 00:00:14.022 --> 00:00:18.217 እንደ እኔ ያሉ ሕጻናት ይህንን ለመቃወም ትምህርታቸውን እያቆሙ ነው፡፡ 00:00:18.561 --> 00:00:20.897 ነገር ግን ይህንን አሁንም ማስተካከል እንችላለን፡፡ 00:00:20.897 --> 00:00:22.963 እናንተም ይህንን ለማስተካከል አሁንም ትችላላችሁ፡፡ 00:00:23.372 --> 00:00:26.577 በሕይወት ለመኖር መቀጠል እንችል ዘንድ የቅሪተ አካል ነዳጅን ማቃጠል ማቆም ይኖርብናል፤ ይሁንና ይህ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ 00:00:27.217 --> 00:00:29.822 ብዙ መፍትሄዎች ስለመኖራቸው እየተነገረ ይገኛል፤ ነገር ግን ከፊት ለፊታችን ስለሚገኘው መፍትሄ ምን ያህል 00:00:30.112 --> 00:00:32.692 እናውቃለን? 00:00:32.692 --> 00:00:35.412 የእኔ ጓደኛ ጆርጅ ስለዚህ ጉዳይ እንዲያስረዳ እተዋለሁ፡፡ 00:00:35.682 --> 00:00:38.112 ካርቦንን ከአየር ውስጥ ስቦ የሚያስወጣ፣ ወጭው አነስተኛ የሆነና ራሱን የሚገነባ ተዐምረኛ ማሽን 00:00:38.211 --> 00:00:42.721 አለ፡፡ 00:00:42.721 --> 00:00:44.418 ይህም … ዛፍ ተብሎ ይጠራል፡፡ 00:00:44.418 --> 00:00:46.466 ዛፍ አንድ የተፈጥሯዊ የአየር ንብረት መፍትሄ ምሣሌ ነው፡፡ 00:00:46.576 --> 00:00:47.929 ውሃ አካባቢ የሚበቅሉ ዕጽዋቶች፣ በእጽዋት ብስባሽ የተሞሉ ረግራጋ መሬቶች፣ ደኖች፣ 00:00:47.929 --> 00:00:48.872 ረግረጎች፣ የባሕር ወለሎች፣ የኬልፕ ጫካዎች፣ እና የኮራል ሪፎች 00:00:48.952 --> 00:00:53.692 ካርቦንን ከአየር ውስጥ በማስወጣት እንዳይመለስ ያደርጉታል፡፡ 00:00:53.692 --> 00:00:56.502 በእጅጉ የተበላሸውን የአየር ንብረታችንን ለማከም ተፈጥሮ መሣሪያ ነው፡፡ 00:00:56.502 --> 00:00:58.772 እነዚህ የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎች እጅግ ከፍተኛ ልዩነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ናቸው፡፡ 00:00:58.772 --> 00:01:02.692 እጅግ መልካም ነው፣ አይደል? 00:01:03.212 --> 00:01:05.957 ሆኖም የቅሪተ አካል ነዳጆችን በከርሰ ምድር ውስጥ እንዳሉ ስንተዋቸው ብቻ ነው፡፡ 00:01:05.957 --> 00:01:08.093 የሚያናድደው ነገር ግን ይህ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ ትኩረት ነፍገናቸዋል ፡፡ 00:01:08.502 --> 00:01:12.325 ከተፈጥሯዊ መፍትሄዎች ይልቅ በአለም አቀፍ ደረጃ ለቅሪተ አካል ነዳጅ የምንሰጠው ድጎማ ከአንድ ሺህ እጥፍ በላይ ነው፡፡ 00:01:12.325 --> 00:01:14.012 የአየር ንብረት መበላሸትን ለመቋቋም ከሚሰጠው ድጋፍ የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎች የሚያገኙት ድጎማ 00:01:14.222 --> 00:01:17.622 2% የሚሆነው ብቻ ነው፡፡ 00:01:19.702 --> 00:01:21.892 00:01:21.892 --> 00:01:24.402 ይህ የእናንተ ገንዘብ፣ የእናንተ የግብር ክፍያ፣ የእናንተ የቁጠባ ገንዘብ ነው፡፡ 00:01:25.744 --> 00:01:30.548 ሌላው ዕብደት ደሞ ተፈጥሮን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በእጅጉ በምንፈልጋት በአሁኑ ወቅት 00:01:30.548 --> 00:01:32.842 ከምንጊዜውም በላይ በፍጥነት እያወደምናት ነው፡፡ 00:01:32.842 --> 00:01:35.377 በእያንዳንዱ ቀን እስከ 200 የሚደርሱ የተፈጥሮ ዝርያዎች ከምድረ-ገጽ እየጠፉ ነው፡፡ 00:01:35.377 --> 00:01:37.095 አብዛኛው የአርክቲክ በረዶ ጠፍቷል፡፡ 00:01:37.095 --> 00:01:39.453 አብዛኛዎቹ የዱር እንስሳቶቻችን የሉም፡፡ 00:01:39.453 --> 00:01:41.021 አብዛኛው አፈራችን የለም፡፡ 00:01:41.021 --> 00:01:43.468 እና ምን ማድረግ ይኖርብናል? 00:01:43.773 --> 00:01:44.958 እናንተ ምን ማድረግ አለባችሁ? 00:01:44.958 --> 00:01:47.211 ቀላል ነው … መከላከል፣ እንደገና መመለስ፣ እና በገንዘብ መደገፍ ያስፈልገናል፡፡ 00:01:47.211 --> 00:01:50.094 መከላከል 00:01:50.094 --> 00:01:54.228 የሐሩር አውራጃ (ትሮፒካል) ደኖች 00:01:54.462 --> 00:01:57.050 30 የእግር ኳስ ሜዳ የሚያህሉት በአንድ ደቂቃ ውስጥ እየተመነጠሩ ይገኛሉ፡፡ 00:01:57.050 --> 00:01:59.029 ተፈጥሮ በጣም አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ሁሉ ልንጠብቀው ወይም ልንከላከለው ይገባል፡፡ 00:01:59.029 --> 00:02:01.012 እንደገና መመለስ 00:02:01.012 --> 00:02:02.813 አብዛኛው የዓለማችን ክፍል ተጎድቷል፡፡ 00:02:02.813 --> 00:02:04.374 ሆኖም ተፈጥሮ ራሷን መልሳ ማቋቋም የምትችል ሲሆን 00:02:04.374 --> 00:02:05.458 እኛም ሥርዓተ-ምህዳሩ ወደነበረበት እንዲመለስ መርዳት እንችላለን፡፡ 00:02:05.458 --> 00:02:06.225 በገንዘብ መደገፍ 00:02:06.225 --> 00:02:07.429 ተፈጥሮን የሚያጠፉ ነገሮችን በገንዘብ ከመደገፍ 00:02:07.429 --> 00:02:08.501 እና ይህንንም ለሚረዱ ነገሮች ክፍያ ከመፈጸም መቆጠብ ይኖርብናል፡፡ 00:02:08.501 --> 00:02:09.513 ይህን ያህል ቀላል ነው፡፡ 00:02:10.084 --> 00:02:11.198 መከላከል፣ እንደገና መመለስ፣ እና በገንዘብ መደገፍ፡፡ 00:02:11.198 --> 00:02:13.325 ይህ የትም ሥፍራ ሊፈጸም የሚቻል ነው፡፡ 00:02:13.325 --> 00:02:16.153 በርካታ ሰዎች የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን መጠቀም ጀምረዋል፡፡ 00:02:16.153 --> 00:02:18.679 ይህንን እጅግ ከፍተኛ በሆነ መጠን ልንተገብረው ይገባል፡፡ 00:02:18.679 --> 00:02:20.505 እናንተም የዚህ አንድ አካል መሆን ትችላላችሁ፡፡ 00:02:20.505 --> 00:02:21.878 ተፈጥሮን ለሚከላከሉ ሰዎች የምርጫ ድምጸችሁን ስጡ፡፡ 00:02:21.878 --> 00:02:24.581 ይህንን ቪዲዮ ለሌሎችም አጋሩ፡፡ 00:02:24.581 --> 00:02:26.581 በዚህ ርዕስ ላይ ተወያዩ፡፡ 00:02:26.581 --> 00:02:30.042 በመላው ዓለም ላይ ለተፈጥሮ አስገራሚ ትግሎች እየተደረጉ ነው፡፡ 00:02:31.051 --> 00:02:31.881 ተቀላቀሏቸው! 00:02:32.702 --> 00:02:36.172 ሁሉም ነገር ዋጋ አለው፡፡ 00:02:36.172 --> 00:02:38.412 እናንተም የምታደርጉት ዋጋ አለው፡፡