YouTube

Got a YouTube account?

New: enable viewer-created translations and captions on your YouTube channel!

Amharic subtitles

← The Last Reformation - The Beginning (2016) - FULL MOVIE

Get Embed Code
48 Languages

Showing Revision 2 created 06/23/2017 by Agape.

 1. ሐዋርያት ሥራ 19:5 ይህንም በሰሙ ጊዜ
 2. በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ
 3. ስጋ እና ሀጥያት ሙቱ
 4. ከክርስቶስ ጋር ሙች :: ከክርስቶስ ጋር ተነሽ ::
 5. መንፈስ ቅዱስ ሆይ ና:: መንፈስ ቅዱስ ሆይ ና እና ነፃ አውጣት ::
 6. ከክርስቶስ ጋር ሙች::
 7. ሐዋርያት ሥራ 19:6 ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ
 8. መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው
 9. ብልሳኖችም ተናገሩ ትንቢትም ተናገሩ::
 10. መንፈስ ቅዱስ ሆይ ይበልጥ
 11. ከመንፈስ ቅዱስህ ጋር ና ሙላኝም::
 12. ቃላት መውጣት ጀመሩ
 13. አመሰግናለው ጌታ ሆይ!
 14. ምን እያደረኩኝ ነበር? -ምን?
 15. ምን እያደረኩኝ ነበር?
 16. እያደረግህ የነበረው? በልሳን እየፀለይክ ነበር
 17. ሐዋርያት ሥራ 3:6-7 ጴጥሮስ እንዲህ አለው
 18. "...በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሳና ተመላለስ"
 19. ...በዚያን ጊዜም እግሩና ቁርጭምጭምጡ ፀና::
 20. ያማል? -አይ
 21. ፈፅሞ አያምም? - በጭራሽ
 22. በኢየሱስ ስም አመሰግናለው :: አሜን::
 23. ተፍፅሟል! ሃሌሉያ!
 24. ...ከአንድ ወር በላይ ሆኗታል እናም ተደንቃለች::
 25. ኢየሱስ ነው::
 26. እንዲህ ያሉ ነገሮች በቴሌቪዥን እመለከት ነበር
 27. አንዳንድ ጊዜ አላምንም ዛሬ ግን አመንኩኝ
 28. ምክንያቱም በራሴ ላይ ሆነ
 29. ህመም አሁን ተነስ
 30. እንዲህ አድርግ:. አሁን ቀና በል::
 31. ጥሩ ነው አይደለ? -አዎን::
 32. አባት ሆይ ተመስገን:: አሜን:: ራስሽን ለመፈተሽ ሞክሪ::
 33. ለውጡ ይታወቅሻል?
 34. የምሬን ነው ምንም ህመም አይሰማኝም::
 35. ዋው!
 36. እግዚአብሔር ሆይ ስለፈውስህ አመሰግናለው:: ህመሙ ስለሚነሳ አመሰግንሀለው
 37. ጭንቅላትሀን ፈትሸው::
 38. አይሆንም! ምንም አይነት ህመም አይሰማኝም ወዳጄ
 39. አሁን ህመሙ ሄዷል:: አዎን አሁን ህመሙ ሄዷል::
 40. እኛ እንደቤተክርስትያን በአዲስ ተሃድሶ ደጅ ላይ ቆመናል
 41. ይሄም ተሃድሶ የሚወስደን
 42. በሐዋርያት ሥራ እንደምናነበው ነው
 43. የዛሬይቱን ቤተክርስትያን ብትመለከቱ
 44. በሐዋርያት ሥራ ላይ ከምናያት ጋር ትልቅ ልዩነት አላት::
 45. ምክንያቱም ባለፈው የሁለት ሺ አመታት ታሪክ ውስጥ
 46. ቤተክርስትያን በተደጋገመ ለውጥ ውስጥ አልፋለች::
 47. በሐዋርያት ሥራ ላይ የነበረችው ቤተክርስትያን ሕያው አካል እንደነበረች እንመለከታለን::
 48. በመንፈስ ቅዱስ የሚመሩ የአማኞች አካል ነበረች::
 49. ቤተክርስትያን የደቀመዛሙርት እንቅሰቃሴ ነበረች
 50. ክርስትና ወደ ግሪስ ሲሄድ ፍልስፍና ሆነ
 51. ወደ ጣልያን በመጣ ጊዜ ተቁዓም ሆነ
 52. ወደ አውሮፓ ሲመጣ ባህል ሆነ
 53. ወደ አሜሪካ ሲመጣ ንግድ ሆነ
 54. አንድን አካል ወስድን የንግድ ዕቃ ያደረግነው እንደሆነ
 55. ይሄ አካልን ሽጦ ከማደር አይቆጠርምን?
 56. ዛሬ ቤተክርስትያን ላይ ይሄንን ነው ያደረግነው
 57. የክርስቶስን ቤተክርስትያን የክርስቶስን አካል ሸቅጠንባታል
 58. በዚህም ምክንያት ተሃድሶ ያስፈልገናል:-
 59. ጠለቅ ብለን የምንሄድበት ተሃድሶ.
 60. ስለ ዶክትሪን ስናወራ ስለ መንፈሱ እያወራን ጭምር ነው
 61. እንዲሁም ስለ አጠቃላይ የቤተክርስትያን ስረአት እያወራን ነው
 62. ስለምን የቤትክርስትያንን ሥርአት አሁን እንዳለው ለማድረግ ወደድን
 63. በሐዋርያት ሥራ ላይ ወደምናገኛት ቤተክርስትያን ለመመለስ አሁን ጊዜው ነው
 64. እግዚአብሔር አሁን ወደመጀመርያው እየመለሰን ነው
 65. እንዴት ያለ ሃያል አምላክ እናገለግላለን
 66. እንዴት ያለ ሃያል አምላክ እናገለግላለን
 67. መላእክት ይሰግዱለታል
 68. ሰማይና ምድር ያመልኩታል
 69. እንዴት ያለ ሃያል አምላክ እናገለግላለን
 70. እንዴት ያለ ሃያል አምላክ እናገለግላለን
 71. መላእክት ይሰግዱለታል
 72. ሰማይና ምድር ያመልኩታል
 73. የሐዋርያት ሥራን ከሌሎች የመፅሐፍ ቅዱስ መፃህፍት ለየት የሚያደርገው
 74. የሐዋርያት ሥራ ከመላው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ
 75. እንዲሁም ከሁሉም የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል
 76. ወጥተን ሰዎችን እንዴት ደቀመዛሙርት እንደምናደርግ ያሳየናል
 77. ወደ ሐዋርያት ሥራ የሚያዳርሱንን ወንጌላት ስናነብ
 78. የሚያስገርመው ነገር ምንም እንክዋን እነዚህ መፃህፍት
 79. በተፃፉበት ወቅት ብፃፉም
 80. ምናልባት ከመስቀሉ ሰላሳ አመታት በህዋላ ሊሆን ይችላል
 81. ነገር ግን መፃፍቱ የሚናገሩት ከመስቀሉ በፊት ስለሆኑ ጉዳዮች ነው
 82. ስለዚህ እነዚህ መፃህፍት ላይ የክርስትናን ሕይወት በሙላት አንመለከትም
 83. ምክንያቱም ያን ጊዜ ክርስቶስ አልሞተም ነበር አልተቀበረም ነበር
 84. ከሙታንም አልተነሳም መንፈሱንም አላከም ነበር
 85. ስለዚህ በወንጌላት ውስጥ
 86. በተግባር እንዴት መውጣትና ደቀመዛሙርትን ማፍራት እንደሚቻል አንመለከትም
 87. መንፈስ ቅዱስ ገና አልተሰጠም ነበር
 88. ከዚህም በላይ ለመውጣትና በዚህ አገልግሎት ስኬታማ ለመሆን
 89. ኃይሉ አልነበረንም
 90. የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ለማያውቁ ሰዎች
 91. ዛሬ ላላቸው ፍረሃት ይሄ አሉታዊ አስተዋፅዖ እንደሚያደርግ አስባለው
 92. ምክንያቱ እየሱስ ሄደው እንዲጠብቁ ነግሯቸዋል
 93. እንዲህ አላቸው:- "መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ
 94. ምስክሮቼ ትሆናላችሁ"
 95. ይሄ እውነታ ነው! በእርግጥም እውነታ ነው!
 96. አሜን ይህ እውነት ነው!
 97. ሃሌሉያ:: -እርሷ አሁን ተፈወሰች
 98. ድንቅ ነው እየሱስ:: - ተመስገን እየሱስ
 99. ተመልከቱ እየተራመደች ነው
 100. አውቃለው ብዙ ቤተክርስትያናት ውስጥ የሚገኝ አንድ ፅሁፍ አለ
 101. በግርግዳዎች ላይ የሚነበብ አንድ ጥቅስ አለ
 102. "እየሱስ ክርስቶስ ትላንትም ዛሬም እስከዘለዓለም ያው ነው"
 103. እንደ አማኝ ዛሬ እኛም ይሄንን እናምናለን
 104. እየሱስ ትላንትም ዛሬም ለዘለአለምም ያው ነው
 105. ነገር ግን እየሱስ ያው ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ያው ነው
 106. መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ያው ከሆነ
 107. በሐዋርያት ሥራ የምናነበውም ያው መሆን አለበት
 108. በክርስቶስ እየሱስ ኃይል እርሷ አሁን ተፈውሳለች
 109. ይሄ ሰው አሁን ይህችን ሴት ፈውሷል
 110. ስለዚህም በአድናቆት ተውጧል
 111. አለቀ:: - አለቀ:: ተፈፀመ::
 112. ከእንባው ጋር ተፈፅሟል
 113. ከዚህ ይበልጥ መፍጠን ስለማልችል እንደዚህ ነበር የምራመደው
 114. አሁን ምን ማድረግ ትችያለሽ?
 115. እህቴ እንደዚህ አድርጊ
 116. ይህንን ማድረግ አልችልም ነበር:: ይህንን አልችልም ነበር::
 117. ይሄንን ማድረግ አልችልም ነበር
 118. ይህ በመሆኑ አካባቢውን ሁሉ በጩሀት ላጥለቀልቀው እችላለው
 119. ክብር ሁሉ ለስሙ ይሁን
 120. በሐዋርያት ሥራ የቀደሙትን ክርስትያኖች እንመለከታለን
 121. የመጀመርያዎቹን የክርስቶስ ደቀመዛሙርት
 122. ይሄንን የደቀመዝሙርነት የሕይወት ዘይቤ ይኖሩት ነበር
 123. ሰዎችን በየቤቶቻቸው እና በየ አደባባዩ ይደርሱ ነበር
 124. ሰዎች ባሉበት ስፍራ ሄደው ያገኗቸው ነበር
 125. ስለዚህም ወንጌሉ በመላው ዓለም ይሰራጭ ነበር
 126. በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች
 127. በክርስቶስ እየሱስ ወዳለ እምነት ይመጡ ነበር
 128. ተጠምቀውም መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ነበር
 129. ነገር ግን በቤተክርስትያን ታሪክ ውስጥ በአንድ ወቅት ላይ
 130. ክርስትና ተቁዓም በመሆን የመንግስት ሃይማኖት ሆነ
 131. ይሄ ተዋረድ ያለው እና ተቁአማዊ አሰራር በቤተክርስትያን የተሃድሶ ዘመን ሁሉ ሲከተለን ቆይቷል
 132. ሉተር ካልቪን እና ዝዊንግሊ በመጡ ጊዜ
 133. ተሃድሶ ለማምጣት እና ወደ እውነተኛው ወንጌል ሊመልሱን ጥረዋል
 134. ወደ ሐዋርያት ሥራ ሊመልሱን
 135. ነገር ግን አልተሳካላቸውም
 136. አሁንም ህንፃው አለን:: አሁንም የተለዩ ካህናት አሉን::
 137. አሁንም ሰዎች በተለዩ ህንፃዎች ይሰበሰባሉ
 138. በተለዩ ቀናት ይሰበሰባሉ : የተዘረጋ ተዋረድም አለ
 139. ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያገኙ ዘንድ መባና መስዋዕታቸውን ያመጣሉ
 140. ሉተር ቤተክርስትያንን በሐዋርያት ሥራ ላይ ወደምናገኛት
 141. አካል ሊመልሳት አልቻለም
 142. መፅሐፍ ቅዱስ የሕይወት መፅሐፍ ነው
 143. ስላጠናነው ብቻ የሕይወት መፅሐፍ አይሆንም
 144. የሕይወት መፅሐፍ የሚሆነው ስንኖርበት ነው
 145. በኢየሱስ ስም በዚህ እጅ ውስጥ ያለውን ህመም እንዲሄድ አዛለው
 146. ደግመህ ለማድረግ ሞክር
 147. ሄዷል
 148. ይሄ ምንድን ነው?
 149. በኢየሱስ ስም አሁን ተፈወስ :: አሜን::
 150. ሞክረው
 151. ሄዷል
 152. አሜን
 153. በኢየሱስ ስም አሁን ተፈወሽ:: እንደገና ሞክሪው::
 154. እናንት አጥንቶች በኢየሱስ ስም አሁን እንድትጠገኑ አዛለው
 155. ሞክሪው
 156. ይህ ከ ሬይኪ እምነት ጋር ይመሳሰላል? - በፍፁም : ይህ እየሱስ ነው::
 157. እየሱስ ነው ሬይኪ አይደለም:: - የሆን ኃይል ነው ?
 158. እግዚአብሔር ነው:: ሌላ ኃይል አይደለም::
 159. አመሰግንሀለው እየሱስ
 160. አሁን ስለሆነው ነገር ምን ይመስላችሁአል?
 161. ደስ ያሰኛል:: - በጣም ደስ ያሰኛል?
 162. የተወለድነውና እዚህ ምድር ላይ የተቀመጥነው በአላማ ነው
 163. ይሄውም እግዚአብሔርን እንድንፈልገውና እንድናገኘው ነው
 164. ችግሩ ግን እኛ እርሱን አንፈልገውም
 165. ስለማንፈልገውም ልናገኘው አንችልም
 166. ስለ እየሱስ ሰምታቹሃል?
 167. የምንኖረው ከእየሱስ ክርስቶስ 2015 አመታት በሁአላ ነው
 168. እግዚአብሔር ሕያው ነው እኛም ደቀመዛሙርቱ እንድንሆን ጠርቶናል
 169. የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ሆነን እርሱ ሕያው እንደሆነ ለዓለም እናሳያለን
 170. አፕሪል አምስት 1995 ዓ.ም ንሰሃ ገባው
 171. ሃትያተኛ እንደሆንኩኝ ገባኝ ስለዚህም ሕይወቴን ለኢየሱስ ሰጠው
 172. ብርሃን በሰውነቴ ውስጥ ገባ እኔም መሬት ላይ ወደኩኝ እግዚአብሔርንም አገኘሁት
 173. ዳግም ስትወለዱ የእግዚአብሔር መንፈስ ይመጣና በእናንተ ውስጥ መኖር ይጀምራል
 174. ከዚያም እየሱስ ያደርጋቸው የነበራቸው ነገሮችን ታደርጋላችሁ
 175. መፅሐፍ ቅዱስ የቃሉ አድራጊዎች መሆን እንዳለብን
 176. እና ሰሚዎች ብቻ እንዳንሆን ይነግረናል
 177. የቃሉ ሰሚዎች ብቻ ሆነን ንገር ግን ባናደርገው እራሳችንን እያታለልን ነው
 178. ፊቱን በመስታወት የሚያይን ሰው እንመስላለን
 179. ከሄድን በሁአላ ወድያውም ምን እንዳየን እንረሳለን
 180. ዘወትር እሁድ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ክርስትያኖች
 181. በቤተክርስትያን ተቀምጠው የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማሉ
 182. ነገር ግን ከዝያ በሄዱ ጊዜ ወድያውም የሰሙትን ይረሳሉ
 183. ሁሉም ህመም አሁን በኢየሱስ ስም ይለቃል
 184. ከራስ እስከ እግር
 185. ይሄንን ከዚህ ቀደም ማድረግ አትችልም? - በፍፁም
 186. ከ 2005 ጀምሮ እንዲህ ነው
 187. ሕያው ነው!
 188. ከተራመድክ ምን ያህል ጊዜ ሆኖሃል? - ለአስር አመታት አልተራመድኩኝም
 189. ይህ ግሩም አይደለም ?
 190. ሲራመድ ያየሁት በጣም ትንሽ እያለው ነበር:: - ምን አልከኝ ?
 191. ከእርሱ ጋር አብሬው የተራመድኩት ትንሽ ሳለው ነበር
 192. አሁን አስራ ሶስት ይሞላዋል:: - ስለዚህ ያንጊዜ ሶስት ዓመቱ ነበር::
 193. የጡንቻ ህመም አለብኝ:: - ስለዝያ እንፀልያለን::
 194. የቱ ጋር ነው? በመላ ሰውነቴ ነው
 195. ይፀልዩልኝ ጀመር:: አራት ወይም አምስት ሰዎች ፀለዩልኝ::
 196. ጀርባዬ ሲንቃቃ ተሰማኝ ከዚያም ተነስቼ መራመድ ቻልኩኝ
 197. ጥቂት ጠበኩኝ ከዚያም ሀኪሙ መጣ
 198. "ሚስተር አክልቡም እንዴት ነህ?"
 199. "ደህና ነኝ" አልኩኝ:: - "የምሰማው ምንድን ነው?"
 200. ቀጥ ብዬ ቆምኩኝ
 201. እርሱም "ምን ተከሰተ?" አለኝ
 202. እኔን አትጠይቀኝ ይልቁንም እግዚአብሔርን ጠይቀው
 203. እርሱም "እንኩአን ደስ ያለህ::ተስፋ አደርጋለው ደህና ሆነህ ትቆያለህ" አለኝ
 204. እስከ አሁን ደህና ነኝ አሁን ኦክቶበር ነው
 205. ይህ የሆነው በጁን ስምንት ነው
 206. ምናልባት ወደ አራት ወር ይሆናል....ጁን ጁላይ
 207. አዎን አራት ወራት:: እናም በጣም ጥሩ ሆኖ ቀጥሏል
 208. ባለፉት ጥቂት አመታት መጋቢ እንደመሆኔ
 209. እጅግ በጣም መጠማት ጀመርኩኝ:: የሐዋርያት ስራን አነባለው
 210. ከዚያም ነገሮች በሃውርያት ሥራ በሚሆኑበት መንገድ
 211. ሲሆኑ ስለማላይ አዘንኩኝ
 212. በቤተክርስትያኔ ወይንም በእራሴ ሕይወት
 213. በሽማግሌዎች ወይም በአጠቃላይ የቤተክርስትያኒቱ መዋቅር
 214. ወደ ውጪ ወጥተን ሰዎችን እየፈወስን አልነበረም
 215. በሰዎች ላይ እጆቻችንን እንጭናለን ከዝያም ወደቤት እንዲሄዱ እንነግራቸዋለን
 216. ምንአልባት ወደፊት ይሻላቸው ይሆናል ምናልባትም አይሆንም
 217. ነገር ግን በሐዋርያት ሥራ ያነበብኩት ሐዋርያቱ
 218. ወጥተው ይሄንን በየዕለቱ ያደርጉ እንደነበር ነው
 219. ይሄ ይሰማኝ ነበር የምፈልገውም ይሄንኑ ነበር::
 220. ስለዚህ ለሁለት አመታት ይሄን ስጠማ ቆየው
 221. የተጠራሁትም ይሄንኑ ለማድረግ እንደሆነ አምኘ ነበር
 222. ነገር ግን ላደርገው አልቻልኩኝም
 223. የቤተክርስትያን ሥርአት መለወጥ አለበት
 224. ህንፃ ተኮር እና የሰንበት ክፍለጊዜ ታዳሚ ተቁዓም ብቻ መሆናችን ማብቃት አለበት
 225. ሰዎች ከአመት ወደ ዓመት ቤተክርስትያን ውስጥ ተቀምጠው
 226. ያ ልዩ አገልጋይ መጥቶ እንዲፀልይላቸው ይጠብቃሉ
 227. አሁን ቅባቱን ተቀብላቹሃል
 228. ሄዳችሁ ይሄንን እና ያንን ለጌታ ማድረግ ትችላላችሁ እንዲላቸው ይጠብቃሉ
 229. ወይም በዚያ ተቀምጠው አንድ ሰው
 230. እንዲመለከታቸውን እና ስጦታቸውን እንዲያይ ይመኛሉ
 231. መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ እንድናደርግ አይነግረንም
 232. እየሱስ ይሄንን ሲነግረን አንመለከትም
 233. በ 1995 ዳቦ ጋጋሪ ሆኘ እሰራ ነበር: ስለ እግዚአብሔር ምንም አላውቅም ነበር
 234. ስለ መፅሐፍ ቅዱስ አንዳች አላውቅም ነበር
 235. በዴንማርክ የምኖር እና በሉተራን ቤተክርስትያን የተጠመኩኝ ወጣት ነበርኩኝ
 236. በ አስራ አራት አመቴ በሉተራን ቤተክርስትያን እምነቴን አፀናው
 237. ይሄ ግን ሥርአት ብቻ ነበር:: ዛሬም ብዙ ሰዎች የሚያደርጉት ሥርአት ነው::
 238. አንድ ቀን ወደ አየሩ አንጋጥቼ "እግዚአብሔር አለህ ወይ?
 239. በዚያ ካለህ ና እና ውሰደኝ:: ላውቅህ እፈልጋለው" አልኩኝ::
 240. ከጥቂት ጊዜያት በሁአላ ወንጌል ሰማው
 241. በ አፕሪል አምስት 1995 ከምሽቱ 9:30 ላይ
 242. ንሰሃ ገባው
 243. ሁሉን ለክርስቶስ ሰጠው
 244. ከዚህ በሁአላ ወደ ቤተክርስትያን መሄድ ጀመርኩኝ
 245. ቤተክርስትያን ውስጥ እንዳሉ ስዎች መሆን ጀመርኩኝ
 246. እናም ክርስትና እግዚአብሔርን ማወቅ
 247. ቀጥሎም ወደ ቤተክርስትያን መሄድ እና ዘወትር እሁድ በዚያ መቀመጥ መሰለኝ
 248. ነገር ግን በሂደት ይበልጥ መሰላቸት ጀመርኩኝ
 249. ምክንያቱም እንዲህ አሰብኩኝ :- "ቤትክርስትያን ከመሄድ
 250. ዘውትር እሁድ ለሁለት ሰዓታት ከመቀመጥ እና
 251. የሆነ ሰው ሲሰብክ ከመስማት ያለፈ ነገር መኖር አለበት"
 252. በአንድ ወቅት የሐዋርያት ስራን ማንበብ ጀመርኩኝ
 253. ስለመጀመርያዎቹ ክርስትያኖች አኗኗር ማንበብ ጀመርኩኝ
 254. እነርሱ ከእኔ የተለየ አካሄድ ነበራቸው
 255. በየሄዱበት የሰዎች ህይወት ሲለወጥ ያዩ ነበር
 256. ይሄን ሳስብ እጅግ አዘንኩኝ ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ
 257. ክርስትያን ሆኘ ብቆይም
 258. የታመሙትን ፈውሼም ሆነ አጋንንትን አስወጥቼ አላውቅም
 259. አንድም ሰው ወደ ጌታ አላመጣውም:: በመጀመርያዋ ቤተክርስትያን የነበረውን
 260. አይነት ሕይወት አልተለማመድኩኝም::
 261. ስለዚህ ከለታት አንድ ቀን እንዲህ አልኩኝ:-
 262. " እግዚአብሔር ሆይ ሁሉ ነገሬን እሰጥሃለው አንተ ግን ይሄንን ሕይወት አሳየኝ"
 263. ከዝያ በሁአላ ይሄንን ሕይወት በብዙ ማየት ጀመርኩኝ
 264. ነገር ግን በመጀመርያ አንድ ችግር ነበር ይሄውም
 265. እኔን ደቀመዝሙር የሚያደርገኝ ሰው አልነበረም
 266. እንደ እየሱስ ክርስቶስ
 267. "ኑ ተከተሉኝ እኔም የሰው አጥማጅ አደርጋቹሃለው" የሚለኝ አልነበረም
 268. ና እና ተከተለኝ አሳይሀለው
 269. እንዴት በሽተኞችን እንደምትፈውስ እንዴት ወንጌል እንደምትሰብክ
 270. በእግዚአብሔር መንግስት እንዴት ውጤታማ እንደምትሆን መንገድ አሳይሀለው
 271. ያለኝ ማንም አልነበረም
 272. ነገር ግን አሁን የተለየ ሁኔታ አለ
 273. አሁን እኛ ሰዎችን ደቀመዛሙርት ማድረግ ጀምረናል
 274. እኛ የተማርነውን ወስደን ብናስተላልፍ
 275. የሚቀጥለው የደቀመዛሙርት ትውልድ ከዝያ ቢቀጥሉ
 276. እነርሱም ይሄን ወስደው ለሚቀጥለው ትውልድ ቢሰጡ
 277. በአጭር ጊዜ ውስጥ በምድር ሁሉ ላይ
 278. እየሱስን የሚመስሉ ደቀመዛሙርት ይኖራሉ
 279. እኚህም እየሱስ ያደርግ የነበረውን እና ከዝያም በላይ የሚያደርጉ ይሆናሉ
 280. ምክንያቱም እርሱ ወደ አባቱ ሄዷልና::
 281. የተሻለውን አዘጋጅቼላቹሃለው
 282. አዎን የእረፍት ስፍራ አዘጋጅቼላቹሃለው
 283. የተሻለውን አዘጋጅቼላቹሃለው
 284. አዎን የእረፍት ስፍራ አዘጋጅቼላቹሃለው
 285. በዚያም ስፍራ ሕይወት በሙላት አለ
 286. በዝያ የቃልኪዳን ስፍራ ...
 287. አሁን አንድ ወዳጃችንን እንሰማለን ሳይመን ኦዳህል ይባላል
 288. ስዊድንኛ
 289. ስዊደን ትቅደም!
 290. አባት ሆይ አውሮፓን አስወርሰን
 291. ዴንማርክን ኖርዌይን እንዲሁም መላው ዓለም ለአንተ ይሁን
 292. ክርስትያን የሆንኩት ከአስራአንድ ዓመት በፊት ነው
 293. በ ስውድሽ ቤተክርስትያን ውስጥ ነበር የገባሁት
 294. አመጣጤ ፈፅሞ ክርስትያን ካልሆነ ሕይወት ነው
 295. ከጊዜ በሁአላ ከባለቤቴ ጋር ወደ ሌላ ከተማ ተዛወርን
 296. በዚያም አንድ ትልቅ ቤተክርስትያን አባል ሆንን
 297. የቤተክርስትያንቱን የወንጌል የስርጭት ሥራ መምራት ጀመርን
 298. ምሳሌ መሆን ቢገባንም አንድም ሰው እንኩአ ወደ ክርስቶስ መምራት አልቻልኩኝም
 299. አንድም ሰው አጥምቄ አላውቅም ነበር
 300. አንድም ሰው ከበሽታ ሲፈወስ በአካል አላየሁም ነበር
 301. ከእለታት አንድ ምሽት በውጭ ሳለን
 302. አንድ ሰው ወደ እኔ ቀርቦ ጥያቄ አቀረበልኝ
 303. "ስራህን አያለው እናም እኔ ክርስትያን መሆን እፈልጋለው
 304. ምን ማድረግ አለብኝ" አለኝ
 305. እኔም "መልካም ነገ እንገናኝ እና
 306. ወደ ቤተክርስትያን እወስድሃለው" አልኩት
 307. ስለዚህ ይህንኑ አደረኩኝ ወደ ቤተክርስትያን ወሰድኩት
 308. ወደ መጋቢው ወሰድኩት መጋቢውም ወደ ደህንነት መራው
 309. ነገር ግን ይሄ በውስጤ ጥያቄ ፈጠረ የሆነ ችግር እንዳለ ተሰማኝ
 310. ከመፅሐፍ ቅዱሴን እና በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ካገኘሁት እውቀት አንፃር
 311. መፅሐፍ ቅዱስ እንድምያስተምረው እኔ ነበርኩኝ
 312. ይሄንን የመምራት ሥራ መስራት የነበረብኝ
 313. እኔ ነበርኩኝ በበሽተኞች ላይ እጄን መጫን የነበረብኝ
 314. እነርሱም ይፈወሳሉ:: እኔ ነበርኩኝ
 315. ሰዎችን ማጥመቅ የነበረብኝ ነገር ግን አላደረኩትም
 316. አንድ ችግር አለ ማለት ነው
 317. ምናልባት ሰዎች እየዋሹ ይሆናል ብዬ ማሰብ ጀመርኩኝ
 318. ሰዎች የሚነግሩኝ ምናልባት እውነት ላይሆን ይችላል
 319. ስለዚህ መውጣት ጀመርኩኝ
 320. ዘወትር ማለዳ ተነሽቼ ወደ ጌታ እፀልያለው
 321. አንዳንድ ጊዜ ይዘንባል አየሩም ጥሩ አይሆንም
 322. እየወጣው ከልቤ ወደ ጌታ እጮህ ነበር
 323. ላውቅህ እፈልጋለው:: እውነተኛው ሕይወት እንዲኖረኝ እፈልጋለው::
 324. አንድ ቀን በሥራ ቦታዬ ላይ የክርስትያን ጋዜጣ አነብ ነበር
 325. ስለ አንድ ዴንማርካዊ ሰው የሚያወራ አጭር ፅሁፍ አየው
 326. ይህ ሰው በገበያ አዳራሽ ውስጥ
 327. ለሰዎች እንደሚፀልይና እንደሚፈወሱ አነበብኩኝ
 328. "ምን?" እንዲህ ያሉ ፅሁፎች ከዚህ ቀደም አይቻለው
 329. ነገር ግን ይሄኛው ልቤን ማረከው የእግዚአብሔር ሥራ እንደሆነም ተሰማኝ
 330. ስለዚህ ደወልኩለት እና መለሰልኝ::እንደኔ ያለ ተራ ሰው ነው
 331. አወራን እናም ስለ ሕይወት ጉዞዬ አጫወትኩት
 332. አስገራሚ ነው መገናኘት አለብን አለ
 333. ስለዚህ ከጥቂት ጉደኞቼ ጋር ሆነን እርሱ ወዳለበት ወደ ዴንማርክ ሄድን
 334. "ለምን ወደ ደንማርክ መጣችሁ" ብሎ ጠየቀን
 335. "ሰዎች ሲፈወሱ ማየት እንፈልጋለን" አልነው
 336. እርሱም "ጥሩ በአስራ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ
 337. የመጀመርያው ሰው ሲፈወስ ታያላችሁ" አለን
 338. እኔም ይሄን ለማመን ተቸገርኩኝ
 339. ይህ ልምምድ እንዴት የሕይወቴ አካል ሊሆን ይችላል
 340. ወደ አደባባይ ስንወጣ የተሰበሰቡ ሰዎች አየን
 341. 25 እስከ 30 እድሜ ያክል ይሆናሉ
 342. ከሴቶቹ አንዷ ጉልበቷ ለብዙ አመታት ይታመማል
 343. እጆቼን ጉልበቷ ላይ እንድጭን እና
 344. ህመሙ እንዲለቃት እንዳዝ ነገረኝ
 345. በወቅቱ ራሴን የመሳት ያክል ነበር የፈራሁት
 346. ይመስለኛል ምንም እምነት አልነበረኝም:: እሺ አደርጋለው አልኩት::
 347. ያለኝ አደረኩኝ እርሷም ዘለለች "ምን!"
 348. እርሷም ተፈወሰች
 349. ሰዎቹ ሁሉ እጅግ ተደነቁ እኔም ነገር አለሜ ተነቃነቀ
 350. ይህ እውነት እንደሆነ ተረዳው:: ይህ እውነት ነው::
 351. ለኔ ይሄ በቂ ነበር
 352. ለአንድ ሰው ከፀለይኩኝ በሁአላ ለብቻዬ ይህንን ማድረግ ቀጠልኩኝ
 353. እኛ እንደ ክርስትያኖች ደቀመዛሙርት እንድናፈራ ተጠርተናል
 354. አንድ ሌላ ቃል መጠቀም ጀምረናል ይህም "ማነሳሳት" የሚል ነው
 355. እንበልና ሞተር ብስክሌት ቢኖርህ እና
 356. ሞተሩን ለማስጀመር ቢያስፈልግ ልናስነሳው ይገባል
 357. ሞተር ብስክሌቱ በተነሳ ጊዜ በስፍራ ሁሉ መንዳት ይቻላል
 358. ልክ እንደዚሁ እኛም እንደክርስትያን ልንቀሰቀስ ያስፈልጋል
 359. ክርስቶስ እንድንሰራ የጠራንን እንድንሰራ
 360. ለምሳሌ አንድን ክርስትያን በሽተኞችን እንዲፈውስ ስናነሳሳው
 361. ወደ አደባብይ እንወስድውና "እኛን ተከተለን" እንለዋለን
 362. እንዴት መደረግ እንዳለበት እናሳየዋለን
 363. አንድጊዜ ማድረግ ከቻሉ ደግመው ማድረግ ይችላሉ
 364. በመላ ሰውነትህ ህመም ይሰማሃል በተልይ እግሮችህ ውስጥ?
 365. አዎን:: እንፀልይልሃለን ውጤቱን ታያለህ::
 366. ህመም ሁሉ እንዲነሳ አዛለው
 367. አሁን በመላ ሰውነትህ ፈውስ ይሁን
 368. ህመም ሁሉ ሰውነቱን ለቀህ ሂድ
 369. መላ ሰውነቱን
 370. በኢየሱስ ስም አሁን ፈውስ እንዲሆን ፀልያለው
 371. ለማንቀሳቀስ ሞክር
 372. ራስህን ፈትሽ
 373. ጥሩ ይሰማኛል:: - ጥሩ ይሰማሃል አይደል?
 374. አሁን ህመም ይሰማሃል?
 375. አይሰማኝም:: - ሄዷል አይደለ?
 376. ሰዎች ይገረማሉ
 377. ይህ ጀርባ አሁን ሙሉበሙሉ እንዲፈወስ አዛለው
 378. እንደዚህ አጎንብሽ እና ፈትሺው
 379. እንደገና ወደላይ:: - በእውነት ሄዷል::
 380. በእርግጥ:: - ምን?
 381. እምላለው:: - እየዋሸው አይደለም::
 382. ይታወቀኛል:: አሁን ሄደ:: - ኦ አዎን ኦ አምላኬ::
 383. ይህ በዓለም ሁሉ እየተስፋፋ ነው
 384. ባለፉት አመታት
 385. መቶ ሺዎች ተፈውሰዋል
 386. ይህም የሆነው እኛ ባነሳሳናቸው እና
 387. ወጥተው መፈወስ በጀመሩ አማኞች ነው
 388. እነዝያም ሰዎች ቀጥለው ሌሎችን ወደ ክርስቶስ መምራት ይጀምራሉ
 389. ስለዚህ ባለፉት አመታት ሺዎች ወደ ክርስቶስ መጥተዋል
 390. ይህ እጅግ ታላቅ ነው
 391. ወደ ስቶኮልም መጥቼ ይሄንን ወንድም አገኘሁት
 392. እርሱም ከሚስቱና ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ ነበር
 393. ከዝያም አብረን ወጣን
 394. መጀመርያ አንድ ህመም የነበረውን ሰው አስቆመው
 395. እጁንም ጫነበት እና ይህ ሰው ተፈወሰ
 396. እኔም እጅግ ተደነቅኩኝ
 397. ይህ ሰው ተፈወሰ እናም እንዲህ አሰብኩኝ
 398. ለካስ ዩትዩብ ላይ ብቻ አይደለም
 399. አሁን ይህን የማየው በዩትዩብ አይደለም እዚሁ ፍትለፊቴ ነው
 400. የተፈወሰውን ሰው ምላሽ ማየቱ ራሱ ያስገርማል
 401. ከዚህ በሁአላ አንድ ሴት መጣች
 402. በሆዷ ውስጥ ህመም ነበረባት
 403. ከጎኔ ሆኖ የሚመራኝ ሰው እንዲህ አለኝ:-
 404. አሁን ያንተ ተራ ነው እጅህን ጫንባት እና
 405. ህመሙ እንዲለቃት እዘዘው:: ስለዚህ እጄን ጫንኩኝ
 406. እያመነታው እጄን ጫንኩኝ
 407. እናም አዘዝኩኝ "በኢየሱስ ስም ህመም ልቀቅ"
 408. እጄን ባነሳው ጊዜ የሴትየዋ ፊት ላይ አግራሞት ሞላ
 409. እንዴት ልታደርገው ቻልክ ? የምትል ትመስላለች
 410. ምን?
 411. እየቀለድቅ ነው? - አይደለም እየቀለድን አይደለም
 412. ይህ እውነት ነው ለዚህም ነው እኛ ይህን የምናደርገው
 413. አይደረግም
 414. ይሄስ ጉድ ነው
 415. እየሱስ ነው የፈወሰሽ እኔ አይደለሁም
 416. በእንዲህ ያለ ሁኔታ ገብቼ አላውቅም
 417. ህልሜ ሁሉ ዛሬ ተፈፀመ
 418. ይህ የሕይወቴ ምርጡ ቀን ነው
 419. ለረጅም ጊዜ ስናፍቀው የነበርኩት ነገር ነው
 420. ወደ ቤተ ስመለስ በታላቅ ደስታ ተሞልቼ ነበር
 421. በአውቶቡስ ሆኘ ወደ ቤቴ መሄድ ጀመርኩኝ
 422. በደረስኩኝ ጊዜ ቤተ መቀመጥ አልቻልኩኝም
 423. ስለዚህ መሃል ከተማ ሄጄ ለሰዎች መፀለይ ጀመርኩኝ
 424. የዛን እለት ጥቂት ሴቶች በመንገድ አገኘሁ
 425. በፀለይኩላቸው ጊዜ ወድያውኑ ተፈወሱ
 426. ወይ ጉድ አልኩኝ
 427. ይሄ በስቶክሆልም የተፈፀመ እና እዛው የሚቀር ብቻ አይደለም
 428. ከዝያም አልፎ ይቀጥላል
 429. ከዚያን ቀን በሁአላ እለት በእለት እወጣለው
 430. አሁን ተጠምቀሽ በመንፈስ ቅዱስ ተሞላሽ::
 431. እርሱ እዛ ነው፣ እርሱ እዛ ነው::