የኮምቦልቻ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የቤተክርስቲያኑ የውስጥ ህንጻ እና ቤተመቅደሱ ሙሉ ለሙሉ ለሊቱን በእሳት ተቃጥሏል

Title:
የኮምቦልቻ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የቤተክርስቲያኑ የውስጥ ህንጻ እና ቤተመቅደሱ ሙሉ ለሙሉ ለሊቱን በእሳት ተቃጥሏል
Description:

የኮምቦልቻ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የቤተክርስቲያኑ የውስጥ ህንጻ እና ቤተመቅደሱ ሙሉ ለሙሉ ለሊቱን በእሳት ተቃጥሏል። ትናንት የመድሃኒዓለም ዓመታዊ ንግስ በዓል በርካታ ህዝብ በተገኘበት በደማቅ ሁኔታ መከበሩ እና በዓሉም በሰላም እንደተጠናቀቀ ይታወቃል። የቤተክርስቲያኑን ህንጻ በእሳት እንዳይወድም ለመታደግ የአካባቢው ህዝብ ከለሊቱ 10ሰዓት ጀምሮ ሲረባረብ አድሯል። በውስጥ የተቀጣጠለውን እና ቤተመቅደሱን ያወደመው እሳት ወደ ውጭ ወጥቶ የውጩን ህንጻ ቤተክርስቲያኑን እንዳያወድም የላይኛው ጣራው/ቆርቆሮውን በማንሳት እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ተደርጓል። እሳቱን ለማጥፋት በተደረገው ጥረት ሙስሊሞችም ውሃ በማቅረብ እና የሚችሉትን በማድረግ ተሳትፈዋል።

more » « less
Duration:
01:16
Format: Youtube Primary Original Synced