1 00:00:01,560 --> 00:00:04,135 ይህ መልእክት እንደዋዛ መታየት ያለበት አደለም፡፡ 2 00:00:04,375 --> 00:00:06,651 እኔ ስሜ ግሬታ ቱንበርግ ነው፡፡ 3 00:00:06,852 --> 00:00:10,212 እኛ አሁን እየኖርን ያለነው በጅምላ በምንጠፋበት ሁኔታ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ነው፡፡ 4 00:00:11,171 --> 00:00:13,612 የአየር ንብረታችን በእጅጉ እየተበላሸ ነው፡፡ 5 00:00:14,022 --> 00:00:18,217 እንደ እኔ ያሉ ሕጻናት ይህንን ለመቃወም ትምህርታቸውን እያቆሙ ነው፡፡ 6 00:00:18,561 --> 00:00:20,897 ነገር ግን ይህንን አሁንም ማስተካከል እንችላለን፡፡ 7 00:00:20,897 --> 00:00:22,963 እናንተም ይህንን ለማስተካከል አሁንም ትችላላችሁ፡፡ 8 00:00:23,372 --> 00:00:26,577 በሕይወት ለመኖር መቀጠል እንችል ዘንድ የቅሪተ አካል ነዳጅን ማቃጠል ማቆም ይኖርብናል፤ ይሁንና ይህ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ 9 00:00:27,217 --> 00:00:29,822 ብዙ መፍትሄዎች ስለመኖራቸው እየተነገረ ይገኛል፤ ነገር ግን ከፊት ለፊታችን ስለሚገኘው መፍትሄ ምን ያህል 10 00:00:30,112 --> 00:00:32,692 እናውቃለን? 11 00:00:32,692 --> 00:00:35,412 የእኔ ጓደኛ ጆርጅ ስለዚህ ጉዳይ እንዲያስረዳ እተዋለሁ፡፡ 12 00:00:35,682 --> 00:00:38,112 ካርቦንን ከአየር ውስጥ ስቦ የሚያስወጣ፣ ወጭው አነስተኛ የሆነና ራሱን የሚገነባ ተዐምረኛ ማሽን 13 00:00:38,211 --> 00:00:42,721 አለ፡፡ 14 00:00:42,721 --> 00:00:44,418 ይህም … ዛፍ ተብሎ ይጠራል፡፡ 15 00:00:44,418 --> 00:00:46,466 ዛፍ አንድ የተፈጥሯዊ የአየር ንብረት መፍትሄ ምሣሌ ነው፡፡ 16 00:00:46,576 --> 00:00:47,929 ውሃ አካባቢ የሚበቅሉ ዕጽዋቶች፣ በእጽዋት ብስባሽ የተሞሉ ረግራጋ መሬቶች፣ ደኖች፣ 17 00:00:47,929 --> 00:00:48,872 ረግረጎች፣ የባሕር ወለሎች፣ የኬልፕ ጫካዎች፣ እና የኮራል ሪፎች 18 00:00:48,952 --> 00:00:53,692 ካርቦንን ከአየር ውስጥ በማስወጣት እንዳይመለስ ያደርጉታል፡፡ 19 00:00:53,692 --> 00:00:56,502 በእጅጉ የተበላሸውን የአየር ንብረታችንን ለማከም ተፈጥሮ መሣሪያ ነው፡፡ 20 00:00:56,502 --> 00:00:58,772 እነዚህ የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎች እጅግ ከፍተኛ ልዩነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ናቸው፡፡ 21 00:00:58,772 --> 00:01:02,692 እጅግ መልካም ነው፣ አይደል? 22 00:01:03,212 --> 00:01:05,957 ሆኖም የቅሪተ አካል ነዳጆችን በከርሰ ምድር ውስጥ እንዳሉ ስንተዋቸው ብቻ ነው፡፡ 23 00:01:05,957 --> 00:01:08,093 የሚያናድደው ነገር ግን ይህ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ ትኩረት ነፍገናቸዋል ፡፡ 24 00:01:08,502 --> 00:01:12,325 ከተፈጥሯዊ መፍትሄዎች ይልቅ በአለም አቀፍ ደረጃ ለቅሪተ አካል ነዳጅ የምንሰጠው ድጎማ ከአንድ ሺህ እጥፍ በላይ ነው፡፡ 25 00:01:12,325 --> 00:01:14,012 የአየር ንብረት መበላሸትን ለመቋቋም ከሚሰጠው ድጋፍ የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎች የሚያገኙት ድጎማ 26 00:01:14,222 --> 00:01:17,622 2% የሚሆነው ብቻ ነው፡፡ 27 00:01:19,702 --> 00:01:21,892 28 00:01:21,892 --> 00:01:24,402 ይህ የእናንተ ገንዘብ፣ የእናንተ የግብር ክፍያ፣ የእናንተ የቁጠባ ገንዘብ ነው፡፡ 29 00:01:25,744 --> 00:01:30,548 ሌላው ዕብደት ደሞ ተፈጥሮን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በእጅጉ በምንፈልጋት በአሁኑ ወቅት 30 00:01:30,548 --> 00:01:32,842 ከምንጊዜውም በላይ በፍጥነት እያወደምናት ነው፡፡ 31 00:01:32,842 --> 00:01:35,377 በእያንዳንዱ ቀን እስከ 200 የሚደርሱ የተፈጥሮ ዝርያዎች ከምድረ-ገጽ እየጠፉ ነው፡፡ 32 00:01:35,377 --> 00:01:37,095 አብዛኛው የአርክቲክ በረዶ ጠፍቷል፡፡ 33 00:01:37,095 --> 00:01:39,453 አብዛኛዎቹ የዱር እንስሳቶቻችን የሉም፡፡ 34 00:01:39,453 --> 00:01:41,021 አብዛኛው አፈራችን የለም፡፡ 35 00:01:41,021 --> 00:01:43,468 እና ምን ማድረግ ይኖርብናል? 36 00:01:43,773 --> 00:01:44,958 እናንተ ምን ማድረግ አለባችሁ? 37 00:01:44,958 --> 00:01:47,211 ቀላል ነው … መከላከል፣ እንደገና መመለስ፣ እና በገንዘብ መደገፍ ያስፈልገናል፡፡ 38 00:01:47,211 --> 00:01:50,094 መከላከል 39 00:01:50,094 --> 00:01:54,228 የሐሩር አውራጃ (ትሮፒካል) ደኖች 40 00:01:54,462 --> 00:01:57,050 30 የእግር ኳስ ሜዳ የሚያህሉት በአንድ ደቂቃ ውስጥ እየተመነጠሩ ይገኛሉ፡፡ 41 00:01:57,050 --> 00:01:59,029 ተፈጥሮ በጣም አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ሁሉ ልንጠብቀው ወይም ልንከላከለው ይገባል፡፡ 42 00:01:59,029 --> 00:02:01,012 እንደገና መመለስ 43 00:02:01,012 --> 00:02:02,813 አብዛኛው የዓለማችን ክፍል ተጎድቷል፡፡ 44 00:02:02,813 --> 00:02:04,374 ሆኖም ተፈጥሮ ራሷን መልሳ ማቋቋም የምትችል ሲሆን 45 00:02:04,374 --> 00:02:05,458 እኛም ሥርዓተ-ምህዳሩ ወደነበረበት እንዲመለስ መርዳት እንችላለን፡፡ 46 00:02:05,458 --> 00:02:06,225 በገንዘብ መደገፍ 47 00:02:06,225 --> 00:02:07,429 ተፈጥሮን የሚያጠፉ ነገሮችን በገንዘብ ከመደገፍ 48 00:02:07,429 --> 00:02:08,501 እና ይህንንም ለሚረዱ ነገሮች ክፍያ ከመፈጸም መቆጠብ ይኖርብናል፡፡ 49 00:02:08,501 --> 00:02:09,513 ይህን ያህል ቀላል ነው፡፡ 50 00:02:10,084 --> 00:02:11,198 መከላከል፣ እንደገና መመለስ፣ እና በገንዘብ መደገፍ፡፡ 51 00:02:11,198 --> 00:02:13,325 ይህ የትም ሥፍራ ሊፈጸም የሚቻል ነው፡፡ 52 00:02:13,325 --> 00:02:16,153 በርካታ ሰዎች የተፈጥሮ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን መጠቀም ጀምረዋል፡፡ 53 00:02:16,153 --> 00:02:18,679 ይህንን እጅግ ከፍተኛ በሆነ መጠን ልንተገብረው ይገባል፡፡ 54 00:02:18,679 --> 00:02:20,505 እናንተም የዚህ አንድ አካል መሆን ትችላላችሁ፡፡ 55 00:02:20,505 --> 00:02:21,878 ተፈጥሮን ለሚከላከሉ ሰዎች የምርጫ ድምጸችሁን ስጡ፡፡ 56 00:02:21,878 --> 00:02:24,581 ይህንን ቪዲዮ ለሌሎችም አጋሩ፡፡ 57 00:02:24,581 --> 00:02:26,581 በዚህ ርዕስ ላይ ተወያዩ፡፡ 58 00:02:26,581 --> 00:02:30,042 በመላው ዓለም ላይ ለተፈጥሮ አስገራሚ ትግሎች እየተደረጉ ነው፡፡ 59 00:02:31,051 --> 00:02:31,881 ተቀላቀሏቸው! 60 00:02:32,702 --> 00:02:36,172 ሁሉም ነገር ዋጋ አለው፡፡ 61 00:02:36,172 --> 00:02:38,412 እናንተም የምታደርጉት ዋጋ አለው፡፡